ኢስላም የጀግና ልብ እምነት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ልክ እንደ ፀሀይ ሁን‼️
=============
«አታያትም ፀሀይን የማንንም ምስጋና አትጠብቅም ነገር ግን ሁሌም ጠዋት ላይ እየፈነጠቀች ለአለም ታበራለች አንተም ለሰወች መልካም ዋል ከአንዳቸውም ምስጋናንና ውዳሴን አትጠብቅ»
«ዛሬ ለሌሎች የምትፈጥራት ደስታ የሆነ ጊዜ ላይ ተመልሳ ላንተ ትመጣለች እርግጠኛ ሁን»
አላህ እንዲህ ብሏል:-«የመልካም ስራ ምንዳ መልካም እንጂ ሌላ ይሆናልን»

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


አንዱኮ ነው
‘በቃ ሸይጧን ተፈታ ማለት ነው ’አለ

ሌላው ‘ምነው ናፍቆህ ነበርዴ’

‘አይ ብዙም አይደል’


تقبل الله منا ومنكم صالح الاعمال

ሀፊዝ ኢብኑ ሐጀር رحمه الله እንዲህ አለ👇

በዒዶች ውስጥ ደስታን ማንፀባረቅ ከዲን መግለጫ ነው።

#ምንጭ
፤(فتح الباري ٢/٤٤٢)


@islam_is_truez


አይከብድም❓

ا ب ت ث
እያለ ድንን ያስተማረን አቅፎ ያሳደገን ኡስታዝ ከሱ ተለይቶ በዓልን መዋል ስሜቱ
ግንኮ በጣም ከባድ ነው ረሂመሁሏህ ኡስታዙና


عيد مبارك جعله الله عيد مبارك علينا وعليكم وعلى جميع المسلمين وجعل الله جميع أيامنا أعيادًا وفرحاً وسروراً

.نسأل الله أن يتقبل منا ومنكم صالح الأعمال

من بنت علي


ረመዳን ቀን 30
ደስተኛ ህይወት
ሁለት ዱአዎች


ድሬ ትናንት የጎዳና ኢፍጧር
♠️
የፍቅር ሀገር ለየት ያሉ ፍጡሮች
እዝነታቸው
ፍቅራቸው
እውነተኝነታቸው
ግልፅነታቸው
የዋህነታቸው
ኧረ ስንቱ አቦ በቃ ወሎዬ በሏቸው ምፅ¡


ከርሞ አመቱን ዙሮ

ሰላም መጣህ ብለን ደሥታውን ሣንጨርሥ፡
መሔጃህ ፈጠነ ረመዷን ታገሥ??
ከውሥጥህ ላይ ሆነን ትናፍቀናለህ፡
የኸይር መፍለቂያ በረከት አይደለህ?
አንሰለችህም ትናፍቀናለህ!
ታላቁም ታናሹም ሙሥሊም ሙሥሊማቱ፡
በፆም በኢባዳ ፀንተው ሲበረቱ፡

የቁርዐኑ ወር በረከት መፍለቂ፡
የእሥልምናችን ታላቅ መታወቂያ፡
የአላህ አደራ በመላው ህዝብ ላይ፡
ለሰውም ለጂንም የታዘዘ ከላይ፡
ሚን ፈውቂ ሰማዋት ከአንዱ ፈጣሪያችን፡
የቁርዐን መውረጃ  ንፁህ መመሪያችን፡
ውብ የታሪክ አዲማሥ የኢሥላም አሻራ፡
ዲንቅ ተምሣሌት ነህ ውብ የፀሀይ ጮራ፡
ለኛም ለቀደምቶች የተሰጠ አደራ፡

እናም ረመዷን
ማን ተጠቀመብህ ማንሥ ተዋረደ፡
የትኛው ከሰረ የትኛው ነገደ፡
ማንሥ ነፃ ወጣ ማንኛው ዘቀጠ፡
አንተን ተጠቅሞብህ ማን ማን በለጠ፡
ማን ይሆን የፆመህ መሥፈርቱን ጠብቆ፡
ከሽርክ ከቢዲዐ ከወንጀል ርቆ፡
ማን ባንተ  ሰመጠ ከዱንያ ተላቆ፡
ሀሣብን ሒሣብን ሁሉን ተጠብቆ፡
ማን ተጠቀመበት ያንተን ታላቅነት፡
ማን ሆነ እዲለኛ የተጠቀመበት፡
ከጀሀነብ እሣት ማንሥ ነፃ ወጣ፡
ማንሥ በኢባዳ ነፍሥያውን ቀጣ፡

ማን ይሆን??
ማን ይሆን በአንተ ላይ የተበሰረበት፡
አንተን ተጠቅሞብህ ጀነት የገባበት፡
ማንሥ አሣለፈው በቀልዲ ጨዋታ፡
መልካም ሥራ ሰርቶ ሣያገኝ እርካታ፡
ለመጣው ለሔደው እየለፈለፈ፡
በማያውቀው ገብቶ ሰው እየዘለፈ፡

ማን ነው
ረመዷን ባንተ «ማን ማን ተጠቀመ፡
ወንጀልን አብዝቶ ማንሥ ተረገመ፡
አወ በቃ እርሙን ያውጣ ባመፅ ያሣለፈ፡
ይበሰር ይደሰት በፆም በኢባዳ የተቀላጠፈ፡

ምንም ባልፆምህም ሀቅህን ሞልቸ፡
ተቀብየሀለሁ በናፍቆት በፍቅር ረክቸ፡
አሁን በማለቅህ ውሥጤ ይረበሻል፡
በናፍቆት በሀዘን አንጀቴ ይጓሻል፡
ታላቅ እንግዳ ነህ ለምንሥ ይዋሻል፡

ባንተ የተጠቀመ ያንተን ክብር አውቋል፡
ያመፀህም ደግሞ ከደሥታ እርቋል፡
መጥፎን ነገር ትቶ መልካሙን የያዘ፡
ከረመዷን ውጭም በዚያው የተጓዘ፡
በልቡም  በአካሉ ሀቅን ያረገዘ፡
ከተውሒዲ ከሱና ያልተጠመዘዘ፡
በሰለፎች ፈለግ በፍቅር የተያዘ፡
በኸይር ቸኩሎ ላይ ታች የናወዘ፡
 በእርግጥም  ይሔ ሰው አንተን ተጠቅሞሀል፡
ደረጃህን አውቆ ክብርህን ሰጥቶሀል፡

አልሐምዱ ሊላሒ በሀሣብ ተውጠን፡
ውሥጣችን ተከፍቶ በናፍቆት ተንጠን፡
እንዲህ እንላለን!
የረጋው ልባችን በሀሣብ ሊበተን?
ፍቅር አሥይዘኸን ልትሰናበተን?
ለማንኛውም… ……>
እንጠብቅሀለን በአላህ እገዛ፡
ታጥቀን በኢባዳ ወሬ ሣናበዛ፡
ምናልባት ጌታችን ያቆየን እንደሆን፡
እንፆምሀለን አርገን እንደሚሆን፡
ኢንሻ አሏህ
ተመላለሥብን የጌታችን እዝነት፡
የሙሥሊሞች ደሥታ አመታዊ ፍኖት፡
እንደተቀበልንህ በደሥታ ዘንዲሮ፡
አላህ ያገናኘን ከርሞ አመቱን ዙሮ፡

በኑረዲን አል←አረቢ
🔙 1441 H.C


በቃ ልትሄድ ነው?!
__
ያ"ሁሉ ድባብህ አድማስ የዘረጋው
ያ"ሁሉ ሰላምህ ሁሉን የማረከው
ከልጅ እስካዋቂ አጃኢብ ያሰኘው
ቅንዝንዙን ሁሉ ምርኮኛ ያረከው
ርቆ የነበረን ከመስጅድ አኩርፎ
ጎትተህ የዶልከው
ሆደ በሻሻውን በንባ ያራጨኸው
ለካ ለትንሽ ቀን ለአንድ ወር ብቻ ነው?
//////////////////////////////////////////
ትናት መምጣትህን በጉጉት ስንጠብቅ
ናፍቆትህ ሳይለቀን
አግኝትን ሳንጠግብህ በሀይባህ ተውጠን
ብዙን ሳንደግስ ሳናስተናግድህ ሀቅህን ዘንግተን
ይሄው ዛሬ ድንገት መህጃህ ቀርቦ አየነው ሽርጉድ ስትል አራግፈህን ልትሄድ ልትወጣ ጥለኸን።
\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\\
በቃ ልትሄድ ነው ወሰንክ ጨክነህ?
ቀጠሮህ ደረሰ ይሄው ነው ቆይታህ
የተሰጠህ እድሜ አላህ የለገሰህ??
በቃ መልካም ይሆን።
አላህ እድል ሰጥቶን በደህና አቆይቶን
በሙሉ ጤንነተ አፊያ ለግሶን
ከዘንድሮ ይበልጥ መልካም ሰው አድርጎን
ይሄንን በሽታ"ቀሀሩ"አንስቶልን
በሙሉ ጤንነት ምንገናኝ ያርገን።

አቡ ዑበይዳ

🔙 1441 H.C


Репост из: قناة عبدالعزيز إبن مصطفا ابو فـوزان
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ውድ የአሏህ ባሮች አንድ ታላቅ ድግስ
ላይ ልጋብዛቹህ በጣም ደስ የሚል
ወሏሂ ደስ ሚሉ ጀመዓ ተቀላቀሏቸው


የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጀመአ
የተጀመረውን ሙሀጂር መስጅድ
የማስጨረስ የኒያህ ፕሮግራም
(ጫረታ) የኸይር ስራ ርብርብ!

"#በ200 ብር ብቻ#"

--የኸይር ዘመቻ
-- በ200 ብር ብቻ

------እንስጥ እንዲሰጠን
-----አጅሩ እንዳያመልጠን

የረመዳን በረካ
ቁጥር ስፍር የለውም ሲለካ

በሉ እንጠናከር
ይገንባ ሙሃጅር---

ያ አላህ አድረግን የሚሰጥ
በበጎ ስራ እንዳንበለጥ--

--የኸይር ዘመቻ
--በ200 ብር ብቻ
---

ደስ ሚል እንቅስቃሴ
ተሳተፉበት ⤵️⤵️⤵️
https://t.me/muhajrinmesjid
https://t.me/muhajrinmesjid
https://t.me/muhajrinmesjid


#ሶደቀተል_ፊጥርን_በተመለከተ__!!
-------------------------------------------
ታላላቅ የኢኢስላም ሊቃውንቶች ስለ ሶደቀተል ፊጥር ምን አሉ!!?
------------------------------------------------

ከዐብደላህ ኢብኑ ዑመር#ረዲየላሁ_ዐንሁማ ተይዞ «የአላህ መልእክተኛ #ሶለላሁ_ዐለይሂ_ወሰለም) ሶደቀተል ፊጥር #በወንድም
#በሴትም፣
#በጨዋም
#በባሪያም፣ ከተምር አንድ ቁና ወይም ከገብስ አንድ ቁና (መስጠትን) ግዴታ አድርገዋል ብለዋል።

ኢማሙል ቡኻሪ 1503 ላይ በዘገበው

#በሌላ_ዘገባም_እንደዚሁ__!! ነቢዩ#ሶለላሁ_ዐለይሂ_ወሰለም) «ሰዎች ወደ (ዒድ) ሶላት ቦታ ከመውጣታቸው በፊት እንዲሰጡ» አዘዋል የሚል ዘገባ አለ።

#ወደ_ዑለማወቹ_ዝርዝር_ፈተዋ_ስንገባ!!
----------------------------------------------------

1⃣ዘካተል ፊጥር ፍርዱ ምንድነው?
~>ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:–
“የፊጥር ዘካህ በሁሉም ሙስሊም በትልቁም በትንሹም፣ በሴቱም በወንዱም፣ በጫዋውም ሰው ሆነ በባሪያው፣ ግዴታ ነው።” [አልፈታዋ 14/197]
2⃣ዘካተል ፊጥር የሚሰጠው በምንድነው?
~>ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:–
“ከምግም፣ ከተምር፣ ከገብስ፣ ከስንዴ፣ ከዘቢብ፣ አልያም በአመዛኙ የዑለማዎች ንግግር ከሌሎች ይህን ከመሳሰሉ፣ ሰዎች እንደ ሀገራቸው ከሚመገቡት ነገር (ለአንድ ሰው) አንድ ቁና ትሰጣለች።”
3⃣የዘካተል ፊጥር መስጫው (ማውጪያ) ጊዜው መቼ ነው ሊሆን የሚችለው?
~>ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:–
“የማውጫ (የመስጫ) ጊዜዋ ከረመዷን በ28ኛው፣ በ29ኛው፣ በ30ኛው፣ ቀንና በዒዱ ንጋት ከሶላት በፊት ነው።” [አልፈታዋ 32/14–33]
4⃣የዘካተል ፊጥር ማውጫ ምክንያት ምንድነው?
~>ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል:–
“ባሪያው አላህ በሰላም ስላስፈጠረውና ሙሉ ፆሙን (በህይወት እያለ) ስላስጨረሰው ምስጋናውን ይፋ ማድረጊያ ነው።” [አልፈታዋ 18/257]
5⃣ዘካተል ፊጥር ግዴታ የማትሆንበት ምን አይነት ሰው ነው?
~>ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል:–
“ከአንድ አካል በስተቀር ግዴታ የማትሆንበት የለም!፣ እነርሱም ምንም የሌላቸው ድሆች ናቸው።” [አልፈታዋ 18/259]
6⃣ልጅን ዘካተል ፊጥር እንዲሰጥ ውክልና መስጠት ፍርዱ (ብይኑ) ምንድነው?
~>ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል:–
“ማንኛውም ሰው ለልጆቹ በጊዜው እንዲከፍሉለት ውክልና መስጠት ይፈቀድለታል። በጊዜው በስራና በመሳሰሉ ጉዳዮች ከሚኖርበት ሀገር ውጪ ሆኖ ውጥረት ውስጥ ቢሆን (በጊዜዋ እንዲሰጥለት ውክልና መስጠት ይችላል)።” [አልፈታዋ 18/262]
7⃣ድሃና ዘካተል ፊጥር መቀበል የሚገባው ሰው፣ ዘካተል ፊጥርን እንዲቀበልለት ለሌላ ሰው ውክልና መስጠት ይችላልን?
~>ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል:–
“ይህ ይፈቀድለታል” [18/268]
8⃣ዘካተል ፊጥር በሚሰጥ ጊዜ የተለየ የሚባል ዱዓ አለን?
~>“ዘካተል ፊጥር በሚሰጥበት ጊዜ የሚባል የተለየ ዱዓ አናውቅም።” [ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ 9/387]
9⃣የዛከተል ፊጥርን ዋጋ በገንዘብ ማውጣት ይፈቀዳልን?
~>ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:–
“በአብዘሃኛው የእውቀት ባለቤቶች ንግግር የዘካተል ፊጥርን ዋጋ በብር ቀይሮ ማውጣት አይፈቀድም። ምክንያቱም ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እና ሶሀባዎች ከሚሰጡት ከነበረው ተቃራኒ ስለሆነ ነው።” [አልፈታዋ 14/32]

~>ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል:–
“ከምግብ እህል (ምግብ ነክ) ነገር ካልሆነ ነገር ማውጣቱ አያብቃቃውም። ምክንያቱም ግዴታ የሆነችው ከምግብ ነውና።” [አልፈታዋ 18/265]
1⃣0⃣ዘካተል ፊጥር ለመስጠት እንደሌላው ዘካ፣ ግዴታ የሚሆንበት መጠን አለውን?(ኒሷብ)
~>ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:–
“ይህን ያህል ካልደረስ ግዴታ አይሆንበትም የሚባል ገደብ የለውም። ይልቅ ሙስሊም በሆነ ሁሉ ላይ ለራሱ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለሚስቱና ለልጆቹ እንዲሁም በሱ ሀላፍትና ስር ላሉት፣ አንድ ቀን ለሊቱን ጨምሮ ከሚመገበውና ከሚመገቡት ምግብ ከተረፈ፣ ማውጣቱ ግዴታ ይሆንበታል።” [አልፈታዋ 14/197]
1⃣1⃣ዘካተል ፊጥር የሚሰጠው መጠን ስንት ነው?
~>ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:–
“ግዴታው ሰዎች ሀገራቸው ላይ ለምግብነት ከሚጠቀሙት ነገር አንድ ቁና ነው። በኪሎ በአማካኝ 3ኪሎ ነው።” [አልፈታዋ 14/203]
1⃣2⃣ዘካተል ፊጥርን፣ ዘካተል ፊጥር የሚሰጠው ሰው ከሚኖርበት ሀገር ውጪ ለሌላ ሀገር መስጠት ይፈቀዳልን?
~>ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:–
“ሱንናው ዘካተል ፊጥር የሚሰጠው ሰው በሚኖርበት ሀገር ውስጥ ለሚገኙ ድሆች ዘካውን መስጠትና ወደሌላ ሀገር አለመውሰዱ ነው።” [አልፈታዋ 14/213]
1⃣3⃣ዘካተል ፊጥር ማህፀን ውስጥ ላለ (ላልተወለደ) ልጅ ማውጣቱ ግዴታ ይሆናልን?

~>ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል:–
“ዘካተል ፊጥር መህፀን ውስጥ ላለ ልጅ በግዴታነት አይሰጥም፣ ነገር ግን በተወዳጅነት መንገድ መስጠት ይቻላል (ተወዳጅ ነው)።” [አልፈታዋ 18/263]
1⃣4⃣ዘካተል ፊጥር ሙስሊም ላልሆኑ ሰራተኞች መስጠት ይፈቀዳልን?
~>ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል:–
“ዘካተል ፊጥርን ሙስሊም ለሆኑ ድሆች ካልሆነ በስተቀር ለሌላ መስጠት አይፈቀድም።” [አልፈታዋ 18/285]
1⃣5⃣የአንድ ሰው ዘካተል ፊጥር ለአንድ ሰው ብቻ ነው የምትሰጠው ወይስ ለተለያዩ ሰዎች ትከፋፈላለች?

~>“የብዙ ሰዎችን ዘካተል ፊጥር ለአንድ ሰው ብቻ መስጠት ይፈቀዳል፣ ልክ ለተለያዩ ሰዎች በታትኖ መስጠት እንደሚቻለው።” [ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ: 9/377]

1⃣6⃣ዘካተል ፊጥርን ተቀብሎ የሚሸጥ ሰው ፍርዱ (ብይኑ) ምንድነው?
~>“የወሰደው ሰው ለመውሰድ ተገቢ ከሆነ ከወሰደ በኋላ መሸጡም ይፈቀድለታል።” [ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ: 9/380]

1⃣7⃣ዘካተል ፊጥርን ያለ ምክንያት የዒድ ሶላት ተሰግዶ እስኪያበቃ ድረስ ማዘግየት ፍርዱ (ብይኑ) ምንድነው?
▪️ ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል:–
“የዒድ ሶላት ተሰግዶ እስኪያበቃ ድረስ ማዘግየቱ ክልክል (ሀራም) ነው። ከዘካተል ፊጥርም አታብቃቃውም።” [አልፈታዋ 18/266]
#ወላሁ________አዕለም!!

@nuredinal_arebi
@nuredinal_arebi
@nuredinal_arebi


የቀድሞዋ የታሪክ አሻራ
ሀላባ የምርጦቼ ትውልድ ልዩ ነው አልኳችሁኮ ያሰላም


ወሎ
ትለያለች ¡ ማለቴ ደስ ብሎኛል


የአዳማዎች ድምቀት! ስወዳችሁኮ
ዘንድሮ ደግሞ ጨምሮበታል ኣይ


ﻗﺎﻝ ﻳﺤﻴﻰ ﺑﻦ ﻣﻌﺎﺫ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ:
ﻣﺴﻜﻴﻦ ﺃﺑﻦ ﺁﺩﻡ !! ﻟﻮ ﺧﺎﻑ ﺍﻟﻨﺎﺭ ﻛﻤﺎ ﻳﺨﺎﻑ ﺍﻟﻔﻘﺮ ‏( ﻟﺪﺧﻞ ﺍﻟﺠﻨﻪ )

የህያ ኢብኑ ሙዓዝ ረድየላሁ አንሁ እንዲህ ይላሉ፦

«ምስኪን የአደም ልጅ!! ድህነትን እንደሚፈራው እሳትን ቢፈራ ኖሮ ጀነት በገባ ነበር።»

@islam_is_truez






🌐ኹጥባ

🔹የወረመዷን ወር ስንብት እና የዘካተል ፊጥር ብይኖች

🕌ደሴ አል አዝሓር መስጂድ

🎙 አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢማም

t.me/abu_reyyis_arreyyis/2555
t.me/abu_reyyis_arreyyis/2555


🌺🌺👇

✍ الشيخ ‏صالح الفوزان حفظه الله ⁩ :

.. والحجاب فيها طهارة، لقلوب الرجال وقلوب النساء ...

..ሒጃብ በውስጧ ጥራት አለ ለወንዶች ቀልብ ለሴቶችም ቀልብ (ጥራት ነው (ሒጃብ))

⁧ ‎#حفظ_الأعراض_موقع_الشيخ ⁩


➴የቦረናው ሸህ

~ክፍል⓶

🎙Ūstâz Sâdãt Kĕmāl
(حفظه الله)
~
☟ ☟ ☟
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/3005



Показано 20 последних публикаций.

458

подписчиков
Статистика канала