ከርሞ አመቱን ዙሮ
ሰላም መጣህ ብለን ደሥታውን ሣንጨርሥ፡
መሔጃህ ፈጠነ ረመዷን ታገሥ??
ከውሥጥህ ላይ ሆነን ትናፍቀናለህ፡
የኸይር መፍለቂያ በረከት አይደለህ?
አንሰለችህም ትናፍቀናለህ!
ታላቁም ታናሹም ሙሥሊም ሙሥሊማቱ፡
በፆም በኢባዳ ፀንተው ሲበረቱ፡
የቁርዐኑ ወር በረከት መፍለቂ፡
የእሥልምናችን ታላቅ መታወቂያ፡
የአላህ አደራ በመላው ህዝብ ላይ፡
ለሰውም ለጂንም የታዘዘ ከላይ፡
ሚን ፈውቂ ሰማዋት ከአንዱ ፈጣሪያችን፡
የቁርዐን መውረጃ ንፁህ መመሪያችን፡
ውብ የታሪክ አዲማሥ የኢሥላም አሻራ፡
ዲንቅ ተምሣሌት ነህ ውብ የፀሀይ ጮራ፡
ለኛም ለቀደምቶች የተሰጠ አደራ፡
እናም ረመዷን
ማን ተጠቀመብህ ማንሥ ተዋረደ፡
የትኛው ከሰረ የትኛው ነገደ፡
ማንሥ ነፃ ወጣ ማንኛው ዘቀጠ፡
አንተን ተጠቅሞብህ ማን ማን በለጠ፡
ማን ይሆን የፆመህ መሥፈርቱን ጠብቆ፡
ከሽርክ ከቢዲዐ ከወንጀል ርቆ፡
ማን ባንተ ሰመጠ ከዱንያ ተላቆ፡
ሀሣብን ሒሣብን ሁሉን ተጠብቆ፡
ማን ተጠቀመበት ያንተን ታላቅነት፡
ማን ሆነ እዲለኛ የተጠቀመበት፡
ከጀሀነብ እሣት ማንሥ ነፃ ወጣ፡
ማንሥ በኢባዳ ነፍሥያውን ቀጣ፡
ማን ይሆን??
ማን ይሆን በአንተ ላይ የተበሰረበት፡
አንተን ተጠቅሞብህ ጀነት የገባበት፡
ማንሥ አሣለፈው በቀልዲ ጨዋታ፡
መልካም ሥራ ሰርቶ ሣያገኝ እርካታ፡
ለመጣው ለሔደው እየለፈለፈ፡
በማያውቀው ገብቶ ሰው እየዘለፈ፡
ማን ነው
ረመዷን ባንተ «ማን ማን ተጠቀመ፡
ወንጀልን አብዝቶ ማንሥ ተረገመ፡
አወ በቃ እርሙን ያውጣ ባመፅ ያሣለፈ፡
ይበሰር ይደሰት በፆም በኢባዳ የተቀላጠፈ፡
ምንም ባልፆምህም ሀቅህን ሞልቸ፡
ተቀብየሀለሁ በናፍቆት በፍቅር ረክቸ፡
አሁን በማለቅህ ውሥጤ ይረበሻል፡
በናፍቆት በሀዘን አንጀቴ ይጓሻል፡
ታላቅ እንግዳ ነህ ለምንሥ ይዋሻል፡
ባንተ የተጠቀመ ያንተን ክብር አውቋል፡
ያመፀህም ደግሞ ከደሥታ እርቋል፡
መጥፎን ነገር ትቶ መልካሙን የያዘ፡
ከረመዷን ውጭም በዚያው የተጓዘ፡
በልቡም በአካሉ ሀቅን ያረገዘ፡
ከተውሒዲ ከሱና ያልተጠመዘዘ፡
በሰለፎች ፈለግ በፍቅር የተያዘ፡
በኸይር ቸኩሎ ላይ ታች የናወዘ፡
በእርግጥም ይሔ ሰው አንተን ተጠቅሞሀል፡
ደረጃህን አውቆ ክብርህን ሰጥቶሀል፡
አልሐምዱ ሊላሒ በሀሣብ ተውጠን፡
ውሥጣችን ተከፍቶ በናፍቆት ተንጠን፡
እንዲህ እንላለን!
የረጋው ልባችን በሀሣብ ሊበተን?
ፍቅር አሥይዘኸን ልትሰናበተን?
ለማንኛውም… ……>
እንጠብቅሀለን በአላህ እገዛ፡
ታጥቀን በኢባዳ ወሬ ሣናበዛ፡
ምናልባት ጌታችን ያቆየን እንደሆን፡
እንፆምሀለን አርገን እንደሚሆን፡
ኢንሻ አሏህ
ተመላለሥብን የጌታችን እዝነት፡
የሙሥሊሞች ደሥታ አመታዊ ፍኖት፡
እንደተቀበልንህ በደሥታ ዘንዲሮ፡
አላህ ያገናኘን ከርሞ አመቱን ዙሮ፡
በኑረዲን አል←አረቢ
🔙 1441 H.C
ሰላም መጣህ ብለን ደሥታውን ሣንጨርሥ፡
መሔጃህ ፈጠነ ረመዷን ታገሥ??
ከውሥጥህ ላይ ሆነን ትናፍቀናለህ፡
የኸይር መፍለቂያ በረከት አይደለህ?
አንሰለችህም ትናፍቀናለህ!
ታላቁም ታናሹም ሙሥሊም ሙሥሊማቱ፡
በፆም በኢባዳ ፀንተው ሲበረቱ፡
የቁርዐኑ ወር በረከት መፍለቂ፡
የእሥልምናችን ታላቅ መታወቂያ፡
የአላህ አደራ በመላው ህዝብ ላይ፡
ለሰውም ለጂንም የታዘዘ ከላይ፡
ሚን ፈውቂ ሰማዋት ከአንዱ ፈጣሪያችን፡
የቁርዐን መውረጃ ንፁህ መመሪያችን፡
ውብ የታሪክ አዲማሥ የኢሥላም አሻራ፡
ዲንቅ ተምሣሌት ነህ ውብ የፀሀይ ጮራ፡
ለኛም ለቀደምቶች የተሰጠ አደራ፡
እናም ረመዷን
ማን ተጠቀመብህ ማንሥ ተዋረደ፡
የትኛው ከሰረ የትኛው ነገደ፡
ማንሥ ነፃ ወጣ ማንኛው ዘቀጠ፡
አንተን ተጠቅሞብህ ማን ማን በለጠ፡
ማን ይሆን የፆመህ መሥፈርቱን ጠብቆ፡
ከሽርክ ከቢዲዐ ከወንጀል ርቆ፡
ማን ባንተ ሰመጠ ከዱንያ ተላቆ፡
ሀሣብን ሒሣብን ሁሉን ተጠብቆ፡
ማን ተጠቀመበት ያንተን ታላቅነት፡
ማን ሆነ እዲለኛ የተጠቀመበት፡
ከጀሀነብ እሣት ማንሥ ነፃ ወጣ፡
ማንሥ በኢባዳ ነፍሥያውን ቀጣ፡
ማን ይሆን??
ማን ይሆን በአንተ ላይ የተበሰረበት፡
አንተን ተጠቅሞብህ ጀነት የገባበት፡
ማንሥ አሣለፈው በቀልዲ ጨዋታ፡
መልካም ሥራ ሰርቶ ሣያገኝ እርካታ፡
ለመጣው ለሔደው እየለፈለፈ፡
በማያውቀው ገብቶ ሰው እየዘለፈ፡
ማን ነው
ረመዷን ባንተ «ማን ማን ተጠቀመ፡
ወንጀልን አብዝቶ ማንሥ ተረገመ፡
አወ በቃ እርሙን ያውጣ ባመፅ ያሣለፈ፡
ይበሰር ይደሰት በፆም በኢባዳ የተቀላጠፈ፡
ምንም ባልፆምህም ሀቅህን ሞልቸ፡
ተቀብየሀለሁ በናፍቆት በፍቅር ረክቸ፡
አሁን በማለቅህ ውሥጤ ይረበሻል፡
በናፍቆት በሀዘን አንጀቴ ይጓሻል፡
ታላቅ እንግዳ ነህ ለምንሥ ይዋሻል፡
ባንተ የተጠቀመ ያንተን ክብር አውቋል፡
ያመፀህም ደግሞ ከደሥታ እርቋል፡
መጥፎን ነገር ትቶ መልካሙን የያዘ፡
ከረመዷን ውጭም በዚያው የተጓዘ፡
በልቡም በአካሉ ሀቅን ያረገዘ፡
ከተውሒዲ ከሱና ያልተጠመዘዘ፡
በሰለፎች ፈለግ በፍቅር የተያዘ፡
በኸይር ቸኩሎ ላይ ታች የናወዘ፡
በእርግጥም ይሔ ሰው አንተን ተጠቅሞሀል፡
ደረጃህን አውቆ ክብርህን ሰጥቶሀል፡
አልሐምዱ ሊላሒ በሀሣብ ተውጠን፡
ውሥጣችን ተከፍቶ በናፍቆት ተንጠን፡
እንዲህ እንላለን!
የረጋው ልባችን በሀሣብ ሊበተን?
ፍቅር አሥይዘኸን ልትሰናበተን?
ለማንኛውም… ……>
እንጠብቅሀለን በአላህ እገዛ፡
ታጥቀን በኢባዳ ወሬ ሣናበዛ፡
ምናልባት ጌታችን ያቆየን እንደሆን፡
እንፆምሀለን አርገን እንደሚሆን፡
ኢንሻ አሏህ
ተመላለሥብን የጌታችን እዝነት፡
የሙሥሊሞች ደሥታ አመታዊ ፍኖት፡
እንደተቀበልንህ በደሥታ ዘንዲሮ፡
አላህ ያገናኘን ከርሞ አመቱን ዙሮ፡
በኑረዲን አል←አረቢ
🔙 1441 H.C