ትናንት አንተ ማለት…! ሚሉ ሁላ ዛሬ ላይ የልባቸውን ያወሩብሃል። ንግግርህ፣ ሃሳብህ ሁለመናህ ይዘገንናቸዋል። በቃ ይቺ ነች ዱንያ፣ ደህና ወዳጅነት ጀመርኩ ስትል ረጅም የምሬት ጊዜ ታወርስሃለች።ሲጀምርስ ለሷ የተባለ ነገር መች ያምርና!
ከሰው ጋር የሚኖረን ወዳጅነት መሰረቱ ለ አሏህ እስካልሆነ ድረስ መጨረሻው አያምርም። ተጀምሮ የሚቆም ወዳጅነት ከጅምሩም ስሜትን፣ ጥቅምን መሰረት ያደረገ እንጂ ለ አሏህ የተባለ አልነበረም። ለ አሏህ በነበረማ ባልቆመ ነበር።
ደስ የሚለው ነገር ያ የተቋረጠው ወዳጅነት የቆመው የ አሏህን ትእዛዝ ከማስከበር ጋር ተያይዞ ከሆነ፤ ብቻ ወደሱ ትእዛዝ እንመለስ እንጂ ያ የቀድሞ ፍቅራችንን እንደሚመልስልን ይህን በማድረግ ላይ ደግሞ ቻይ እንደሆነ በግልፅ ነገሮናል።
﴿عَسَى اللَّهُ أَن يَجْعَلَ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَ الَّذِينَ عَادَيْتُم مِّنْهُم مَّوَدَّةً ۚ وَاللَّهُ قَدِيرٌ﴾ الممتحنة 7
ባይሆን ስላለፈው ማሰቡን ትተን ለሱ ብለን ያጣነውን ነገር እስኪመልስልን በጉጉት መጠበቅ ነው ያለብን!