🔖 ሸይኽ ኢብን ባዝ ተጠየቁ:-
አንድ ሰው ልጃኣገረድ አግብቶ ቢክራ (ድንግል) ሆና ካላገኛት ምን ማድረግ ነው ያለበት??
የሸይኽ መልስ፦ይሄ ብዙ ምክኒያቶች ይኖሩታል፡ ቢክራዋ (ድንግሏ) ያለ ዝሙትም ሊፈርስ ይችላል፡፡ የልጅቷ ውጫዊ ስብዕናዋ መልካም ከሆነ እናም በዲኗ የተስተካከለች ከሆነች በሷ ላይ ጥሩ ግምትና መልካም ጥርጣሬን ማሳደር የግድ ነው፡፡
✔ወይንም አፀያፊውን ዝሙት ሰርታ ከዚያ አላህ መርቷት ከሰራችው መጥፎ ተግባር ተፀፅታና ቶብታም ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚያም ወደጥሩነትና መልካምነት ከተቀየረች(ቢክራ)ድንግል አለመሆኗ እሱን አይጎዳውም፡፡
✔ምናልባትም ድንግሏ በወር አበባ ብርታት ምክንያት ፈርሶ ሊሆን ይችላል፡፡ ጠንካራ (ሀይድ)የወር አበባ (ቢክራ)ድንግልን ያፈርሳል፡፡ይህንንም ብዙ ዑለሞች አውስተዋል፡፡
✔ልክ እንደዚሁም በአንዳንድ ዝላዮች ድንግል ሊፈርስ ይችላል፡፡ ከሆነ ቦታ ወደ ሆነ ቦታ ስትዘል ወይም ከከፍተኛ ቦታ ወደ ዝቅተኛ ቦታ በምትወርድበት ጊዜ በዚህ አጋጣሚ ድንግል ሊፈርስ ይችላል፡፡
✔ስለዚህ የድንግል መፍረስ የግድ በአፀያፊው ዝሙት ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡ በጭራሽ ከዝሙት ውጪ በሆነ ክስተት ነው ድንግሌ የፈረሰው ካለች ወይንም በዝሙት ነው ድንግሌ የፈረሰው ግን ተገድጄ እና ተደፍሬ ነው ካለች ይሄ እሱን አይጎዳውም፡፡
✔ወይም በፍላጎቷ ዝሙት ሰርታ ከሆነ ድንግሏ የፈረሰው ግን ያንን ያደረገችው በማታውቅበትና በመሀይምነቷ እንደሆነም እና አሁን ከዚህ ቶብታና ተፀፅታ ከሆነ ይሄም እሱን አይጎዳውም፡፡
✔ይህን የሷን ሚስጥር ሊበትንባትና ሊያሰራጭባ አይገባም ይልቁንስ ሊደብቅላት ይገባል፡፡ በእርሱ ግምት እውነተኛነቷንና ቅንነቷን እናም ማስተካከሏን ካመነበት ከእርሱ ጋር ያቆያታል፡፡ ካሎነ ግን በሷ ላይ ያደረበት ግምት ጥሩ ካልሆነ ይፈታታል ይህም የሚሆነው ግን የሷን ሚስጥር ከመደበቅና ከመጠበቅ ጋር ነው፡፡
📚ምንጭ መጅሙዕ አል ፈታዋ ሊብኒ ባዝ
(287/286-30)