❗#ታህሳስ 19 #የቅዱስ_ገብርኤል❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ታህሳስ 19 ብርሃናዊው መልዓክ ቅዱስ ገብርኤል ሰለስቱ ደቂቅን ከዕቶን እሳት ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ቤተክርስቲያን በፀሎትና በምስጋና በደማቅ ሁኔታ ታከብራለች፡፡
🔷👉#ታሪኩም_ከብዙ_በጥቂቱ :-
🔴👉 ባቢሎንን ይመራ የነበረው ናቡክደነፆር በእግዚአብሔር የማያምን ጣዖትን የሚያመልክ ንጉስ ነበር፡፡ በወቅቱም ቁመቱ ስልሳ ወርዱ ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቅ ምስል በማሰራት ሕዝቡ እንዲሰበብ በማዘዝ ሁሉም ሰው ላሰራው ጣዖት መስገድ እንዳለባቸው ይህን በማይፈፅሙት ላይ ቅጣቱ ከባድ እንደሆነ አዋጅ አሳወጀ፡፡
🔷👉 የንጉሱ አስተሳሰብ ለእግዚአብሔር ወዳጆች ከባድ ፈተና ቢሆንም እውነተኛዎቹን አማኞች ግን በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው እምነት ሊቀይረው አልቻለም፡፡ ቅጣቱንም በማሰብ እና በመፍራት ሁሉም እግዚአብሔርን በመካድ ለጣዖቱ ሰገዱ አረበረቡ፡፡
🔵👉 በዚህ ፈታኝ ዘመን ነበር አናንያ ፣ አዛርያን እና ሚሳኤል የተባሉ ሶስት ወጣቶች ግን ለእግዚአብሔር ያላቸውን መታመን አሳዩ፡፡
🔷👉 ለጣዖቱ ያልሰገደ ወደ እቶን እሳት ተጥሎ እንደሚሞት ቁርጥ ያለ ወሳኔ እንደሆነ ቢያውቁም ያለምንም ፍርሃት በአንሰግድም አቋማቸው በመፅናት "ንጉስ ሆይ የፈጠረንን አምላካችንን ክደን አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም !" አሉት፡፡
🔵👉 በሶስቱ ወጣቶች ድርጊትና ድፍረት በጣም የተቆጣው ንጉስ ናቡክደነፆር አገልጋዮቹን ጠርቶ እሳቱ ሰባት እጥፍ እንዲነድ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ወደ እሳቱም እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ የንጉሱ አገልጋዮች ሶስቱን ወጣቶች አናንያን ፣ አዛርያን ፣ ሚሳኤልን እያንከበከቡ ወደ እቶን እሳቱ ወረወሯቸው፡፡
🔴👉 እሳቱ ከነበረው ኃይል የተነሳ ወላፈኑ አገልጋዮቹን እዛው እንደ ማገዶ አነደዳቸው፡፡ ሠለስቱ ደቂቅ ግን ከየት እንደመጣ ካልታወቀ እንግዳ ጋር በመሆን በዕቶን እሳቱ ውስጥ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በደስታ ይመላለሱ ጀመር፡፡ ይህም ተዓምር ንጉሱን እና መኳንንቶቹን እንዴት ሊሆን ቻለ ብለው ተገረሙ፡፡
🔷👉 ንጉሱም በዚህ ወቅት በመደነቅ
" እነሆ እኔ በእሳቱ መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች ይታዩኛል፡፡ እሳቱ ምንም አልጎዳቸውም ፡፡ አራተኛው ግን የአማልክትን(የእግዚአብሔርን) ልጅ ይመስላል፡፡ " አለ፡፡
🔶👉 ንጉስ ናቡክደነጾር በግልፅ ተመልክቶ እንደመሰከረው የነደደውን እሳት በማብረድ ለሠለስቱ ደቂቅ ቤዛ የሆናቸው ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ስለ ሃይማኖታቸው መከራ የተቀበሉን የአግዚአብሔር ወዳጆችን በእምነት የሚያፀና ታላቅ መልዓክ ነው፡፡
❗የመልዓኩ የቅዱስ ገብርኤል ረድኤት በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን❗
❗ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ❗
።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ታህሳስ 18 /2017 ዓ.ም
ሆለታ
ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ
🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom
🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w
🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube
🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16