❗#ገብርሔር_የአብይ_ፆም ❗
🔴#ስድስተኛ ሳምንት
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ገብርሔር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው። ገብርሄር የዓብይ ጾም ሥድስተኛ ሳምንት መጠሪያ ሲሆን ትርጉሙም ታማኝ አገለጋይ ማለት ነው።
🔴👉 በዚህ ሳምንት ሥለ ገብርሄር ( ታማኝ አገለጋይ)እና ገብርሃካይ (ክፉ አገለጋይ) መክሊት ማለትም ሥለ፦
~ባለ አምሥት መክሊት፤የተሰጠው
~ ባለ ሁለት መልክት፤ የተሰጠው እና
~ አንድ መክሊት፤ ሥለተሰጠው ባለ መክሊቶች ከነ ምስጢራቸው በሰፊው ይነገራል።
🔴 ማቴ፡፳፭፦
"ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ እንደሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ አቅሙ ለአንዱ አምሥት መክሊት፣ለአንዱም ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ኼደ።
🔵👉 አምሥት መክሊት የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላ አምሥት መክሊትም አተረፈ፣ እንዲሁ ሁለት የተቀበለውም ሌላ ሁለት አተረፈ፤ አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቆፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረው።
🔴👉 ከብዙ ዘመንም በሁዋላ የእነዚያ ባሪዎች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው ፤ አምሥት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምሥት መክሊት አስረክቦ ጌታ ሆይ አምሥት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር እንሆ ሌላ አምሥት መክሊት አተረፍኹበት አለው።
🔵👉 ጌታውም መልካም አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፡ በጥቂቱ ታምነኻልና በብዙ እሾምኻለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው። ሁለት መክሊት የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ ጌታ ሆይ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እንሆ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍኹበት አለው ። ጌታውም መልካም አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፡ በጥቂቱ ታምነኻልና በብዙ እሾምኻለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።
🔴👉 አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ ጌታ ሆይ: ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንኽባትም የምትሰበስብ ክፋ ሰው መሆንህን አውቃለሁ። ፈራሁም ኼጀም መክሊትህን በምድር ላይ ቀበርኩት። እንሆ መክሊትህ አለህ አለው። ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው :አንተ ክፋ እና ሀኬተኛ ባሪያ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንኹባትም እንድሰበስብ ታውቃልህን? ሥለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር።እኔም መጥቼ ያለ,ኝን ከትርፉ ጋር እወስድ ነበር። ሥለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት።
🔵👉 ላለው ሁሉ ይ,ሰጠዋልና ይበዛለትማል ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳን ይወሰድበታል። የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት በዚያ ልቅሶና ጥር,ስ ማፋጨት ይሆናል " ማቴ ፳፭፦፲፬-፴
❗👉 ውድ ክርስቲያኖች የጨዋይቱ የሳራ የቅድሥት ኦርቶዶክ,ስ ተዋህዶ ልጆች መክሊታችንን እንወቅ በተሰጠን ጸጋ ቤተክ/ን እናገልግል፤ ሁላችንም የየድርሻች እንወጣ መክሊቱን ቆፍሮ እንደቀበረው ክፍ አገልጋይ በውጭ እንዳንጣል እንትጋ። "እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም" ፪ኛቆሮ፱፦፯ "ክፉ ሰው በከንፈሩ ኃጢአት ይጠመዳል፤ ጻድቅ ግን
ከመከራ ያመልጣል።
🔴👉 የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥ ሰውም እንደ እጁ ሥራ ዋጋውን ይቀበላል። የሰነፍ መንገድ በዓይኑ የቀናች ናት፤ ጠቢብ ግን ምክርን ይሰማል ። የሰነፍ ቍጣ ቶሎ ይታወቃል፤ ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል። እውነተኛን ነገር የሚናገር ቅን ነገርን ያወራል፤ የሐሰት ምስክር ግን ተንኰልን ያወራል።" ምሳ ፲፪፦፲፫
🔵👉 " ከሁሉ በሚያንስ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ ነው፥ ከሁሉ በሚያንስም የሚያምፅ በብዙ ደግሞ ዓመፀኛ
ነው።"ሉቃ፲፮፦፲ " እንግዲያስ በዓመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ እውነተኛውን ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኋል?"
ሉቃ፲፮፦፲
🔴👉 ጌታችን ያዘዘንን ሁሉ እናድርግ ሰዎችን ሁሉ እንውደድ ከዘረኝነት አዙሪት እንውጣ ክርስትና ቃላት መደርደር ሳይሆን ተግባርና ስራ ነውእና። ልጄ ሆይ ኃይማኖትህ በስራህ ይገለጥ"እንዳለ ጠቢቡ። "በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ…ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
🔵👉 ሥለ ኢትዮጵያ እንፀልይ፤ ሥለ ቤተክርስቲያንም እንፀልይ፤ ጾሙን ጾመን ፀልየን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም ያድርሰን ፤በመንፈስ ጀምረን በሥጋ
እንዳንጨርሰው የመድኃኒታችን ቸርነቱ አባትነቱ የድንግ እናትነትና ምላጃ ይርዳን አሜን ❗
የ100 ብር ቻሌንጃችን ተጀምሯል
ሁላችሁም ተሳተፉ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ። ሐዋ, 20፥35
🔴👉 ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች መፅሐፍ እንደሚለው ስንቶቻችን ከመቀበል ይልቅ ለመስጠት ዝግጁዎች ነን ? ስንቶቻችንስ በምፅዓት ቀን ለምንጠየቀው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሳይመሽብን ተዘጋጅተን ይሆን ?
🔵👉 በውኑ በምፅዓት ቀን ምንድን ነው የምንጠየው ትሉኝ ይሆናል እስቲ ከነ ፍርዱ መፅሐፍ የሚለውን እንመልከት 👇👇
🔴👉 ማቴዎስ 25
³⁴ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
³⁵ ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥
³⁶ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።
³⁷ ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?
³⁸ እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?
³⁹ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
⁴⁰ ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።
🔴👉 ⁴¹ በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
⁴² ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥
⁴³ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።
⁴⁴ እነርሱ ደግሞ ይመልሱና፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።
⁴⁵ ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።
⁴⁶ እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።
🔴👉 ወዳጆቼ እኛ የትኛውን ይሆን የምንፈልገው ? የአባቴ ብሩካን ኑ የሚለውን ነው ወይስ እናንተ ርጉማን ከኔ ሂዱ የሚለውን ነው ? እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም የአባቴ ብሩካን ኑ መባልን መንግስቱን መውረስን ነው የምንፈልገው !
🔵👉 ታዲያ ይህንን እንድንባል የተራበ አብልተን ይሆን የተጠማ አጠጥተን ይሆን የታረዘ አልብሰን ይሆን የታሰረ ጠይቀን ይሆን ? የታመመ ጠይቀን ይሆን ? መቼስ ነው ይህንን የምናደርገው ? ወዳጆቼ መጠሪያችን አይታወቅምና ሳይመሽብን ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንስራ !