👋እንዴት ናችሁ ካቦዶች
‼️ጥር 24 የ ቅዳሜ ፕሮግራም
በግብፅ ሀገር የተወለደ አንድ ሙሴ የተባለ ሰው ነበር።እርሱም ከጌታ ጋር እጅግ የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው ልክ ወዳጅ እንደሚያናግር ነበር ያወራው የነበረው።
ታዲያ ሙሴም በአንድ ወቅት ከሰፈር ትንሽ ራቅ ብሎ ትንሽዬ ቤት ተከለ ስሙንም “የመገናኛው ድንኩዋን”ብሎ ጠራው እዛም ማንም ጌታን ማናገር (መጠየቅ) የፈለገ ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኩዋን ይሄድ ነበር።እርሱም በገባ ጊዜ ከሰማይ ደመና ይወርድና ይከልለው ነበር።እንዲሁም ሙሴ በእያንዳንዱ እርምጃው ላይ እ/ርን እየጠየቀ ነበር ይሄድ የነበረው እናም እስራኤላውያንን ከግብፅ በሚያወጣ ጊዜ ቅድምያ እ/ርን ያማክር ነበር።በአንድ ወቅት ሙሴ ህዝቡን ባህር ከፍሎ ሲያሻግራቸው በቅድሚያ እ/ር አውረቶት ነበር።
ከላይ ያለውን 👆👆አጠር ያለ ታሪክ መሰረት በማድረግ
በነዚህ ጥያቄዎች 👇 👇
°እንዴት ወደ እ/ር እንቅረብ ወይም ወደ እርሱ ለመቅረብ ምን ማረግ አለብን?
◦ Devotion time (የጥሞና ሰአት) አሏችሁ ምን ምን ሰአት ነው?
◦ ጠይቃቹ (ነግራቹት) ከተደረገላቹ ነገሮች መካከል ቢያንስ 2 ጥቀሱ
📝summary's point( የ ማጠቃለያ ነጥቦች)
በ እግዚአብሔር ፊት ስንቀርብ:-
◆ እንደ እግዚአብሔር ቃል ማለትም በ ፅድቅ፣ በቅድስና ፣ እግዚአብሔርን በመፋራት፣ በተሰበረ ልብ እና በንስሐ መንፈስ
◆ በ ሙሉ እምነትና በ ማወቅ
◆ በ ሁኔታዎች መለዋወጥ ሣንሰናከል በ ትጋት ( ቢመችም ባይመችም) ለምሣሌ:- ዳንኤል / ፊቱ የመቅረብ ፍላጎቱ ከከበበው ሁኔታ በልጦ ነበር
➱ ሙሴ ራሱን ሰጥቶ እንደቀረበ እኛም እራሣችን ሰጥተን መቅረብ ይኖርብናል
ተባረኩ እንወዳችዋለን💛
#በፊቱ_መቅረብ
@jtfgcyouth@jtfgcyouth