💬በመፍጠርም ሆነ በማዳን ስራ ውስጥ የሆነውና የሚሆነው ሁሉ ከ ሥሉስ አምላክ ጋር ተቆራኝቷል። የድነት ዕቅድ ብቻ ሳይሆን ክዋኔዉም በዚሁ መስመር ይጓዛል። አለም ሳይፈጠር አብ እኛን በ ክርስቶስ በመምረጥ የ ድህነታችን ሂደት አስጀመረ። የ ዘመኑ ፍፃሜ ሲደርስ ደግሞ እግዚብሔር ወልድ ሰው ሆኖ በ መካከላችን በ መኖር፣ በ መስቀል በ መሞት ና ከ ሙታን በ መነሳት ከዚያም በአብ ቀኝ በመቀመጥ አለም ሳይፈጠር የ ታቀደውን በተግባር ፈፀመ። ከወልድ የምድር ስራ መጠናቀቅ በኋላ ደግሞ የክርስቶስን ፍቅር እንድናውቅ ና ድነትን እንድንቀበል ለመረዳት መንፈስቅዱስ ወደ ምድር ተላከ። አብ ልጆቹ ሊያደርገን ልጁን ላከ፤ ልጆቹም በመሆናችን መንፈሱን በ ልባችን አኖረ።
ገላትያ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤
⁵ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ።
⁶ ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።
⁷ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።
🔴አብ የድነት አቃጅ፣ወልድ የድነት ከዋኝ እና መንፈስቅዱስ ደግሞ የድነት ተግባሪ!!!!