TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
Russian
Язык сайта
Russian
English
Uzbek
Вход на сайт
Каталог
Каталог каналов и чатов
Поиск каналов
Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов
Рейтинг чатов
Рейтинг публикаций
Рейтинги брендов и персон
Аналитика
Поиск по публикациям
Мониторинг Telegram
©Legal details center© :የህግ ማብራሪያ ማዕከል©
12 Jan, 12:28
Открыть в Telegram
Поделиться
Пожаловаться
ዛሬ የፀደቀው የንብረት ማስመለስ አዋጅ
ያካተታቸው አንኳር ነጥቦች።
~> ይህ አዋጅ ተፈፃሚ ከመሆኑ በፊት ባሉት አስር ዓመት ውስጥ ወይም
ተፈፃሚ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ የተገኘ ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን
ለማስመለስ በዚህ አዋጅ መሰረት ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ክስ ሊቀርብ
ይችላል፤
~> የንብረቱን ምንጭ እንዲያስረዳ የተጠየቀው ሰው የንብረቱን ምንጭ
ለማስረዳት የወንጀል ሃላፊነት የሚያመጣበት ማስረጃ ቢሰጥም በወንጀል
ችሎት በራሱ ላይ ማስረጃ ሆኖ አይቀርብም፤
~> ዐቃቤ ሕግ ምንጩ ያልታወቀ ነው ብሎ የጠረጠረውን ማንኛውንም ንብረት ዝርዝር
እና የተገኘበትን አግባብ የሚያሳይ መግለጫ እንዲያቀርብ በፅሁፍ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል
~> የንብረቱን ምንጭ እንዲያስረዳ የተጠየቀው ሰው የንብረቱን ምንጭ ለማስረዳት
የሚያቀርበው ማስረጃ ህጋዊ መሆን አለበት፤
~> ማንኛውም ሰው ጥያቄው በደረሰው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለዐቃቤ ህግ ዝርዝር
ማስረጃዎችን በማያያዝ በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርበታል፤
~> ዐቃቤ ሕግ ወይም መርማሪ ንብረቱ እንዲታገድ ወይም እንዲያዝ ለፍርድ ቤት
ማመልከቻ ማቅረብ ይችላል፤
~> በንብረቱ ላይ የእግድ ወይም የመያዝ
ትዕዛዝ የተሰጠ እንደሆነ፥ ትዕዛዙ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ሶስት ዓመት
ጊዜ ውስጥ በተጠርጣሪው ላይ ከንብረቱ ጋር በተያያዘ የተጠረጠረበት የወንጀል ክስ
ወይም ንብረቱን የማስወረስ ክስ ካልቀረበ የተሰጠው የመያዝ ወይም የእግድ ትዕዛዝ
ቀሪ እንዲሆን ባለንብረቱ ወይም ተጠርጣሪው ለፍርድ ቤት ሊያመለክት ይችላል፥
~> በዚህ አዋጅ ስለንብረት ማገድና መያዝ የተደነገገው ድንጋጌ ቢኖርም፡-
ሀ/ የተጠርጣሪው፣ የተከሳሹ፤ የፍርደኛው ወይም በስሩ ለሚተዳደሩ የቤተሰብ
አባላት የእለት መተዳደሪያ ወይም ሙያዊ ስራ ለመስራት አስፈላጊ የሆኑ
ቁሳቁሶች እና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች፤
~> ለ/ ለተጠርጣሪው፣ ለተከሳሹ፥ ለፍርደኛው ወይም በስሩ ለሚተዳደሩ
የቤተሰብ አባላት የዕለት ኑሮ ጠቃሚ የሚሆኑ እና ከስድስት ወር ላልበለጠ
ጊዜ ወይም ፍርድ ቤቱ በልዩ ሁኔታ ለሚወስነው ጊዜ የሚሆን ስንቅ፤
እንዳይታገድ ወይም እንዳይያዝ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል፤
~> በሌሎች ሕጎች በሚወጡ ድንጋጌዎች መሰረት ከክስ ነጻ የሚደረግ እና
በወንጀል ክርክር ሂደቱ ወደ ምስክር የዞረ የወንጀል ተካፋይ የሆነ ሰው
በወንጀል ድርጊቱ ያገኘው ንብረት እንዲመልስ ወይም ያደረሰው ጉዳት
እንዲክስ ይደረጋል፤
ተጨማሪ መረዳት ለማግኘት ከላይ በ pdf የተያያዘውን የአዋጁን ሙሉ ክፍል ያንብቡ
226
0
1
×