1. ሕፃናት በፍ/ቤት ለማስረጃነት የሚውል የዘረ መል (DNA) ምርመራ ለማድረግ አይገደዱም፤ ምርመራውን ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ብቻውንም እንደ በቂ ማስረጃ ተቆጥሮ "ሕፃኑን DNA ለማስመርመር ፈቃደኛ ያልተሆነው ልጁ የባልዬው ባይሆን ነው" የሚል የሕግ ግምት [የፍ/ሕ/ቁ. 22ን ልብ ይሏል] በመያዝ ባልዬው የልጁ አባት አይደለም ብሎ መወሰን ሕገ መንግሥቱን የሚቃረን ነው::
2. በጋብቻ ውስጥ የተወለደን ልጅ ልጄ አይደለም በማለት (አባትነትን ለመካድ) የሚቀርብ ክስ በጠባቡ ሊታይ የሚገባና የክስ ማቅረቢያ ጊዜውም ባልዬው የልጁን መወለደ ካወቀበት ወይም ማወቅ ከሚገባው ቀን ጀምሮ ባሉት 180 ቀናት ውስጥ የመሆኑ ይርጋ የሕፃናትን ሕገ መንግሥታዊ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ከሌሎች ይርጋዎች የተለየ ስለሆነ በአንድነት ሊታይ የማይገባ እና ተከራካሪ ወገኖች ባያነሡትም እንኳን ፍ/ቤቶች በራሳቸው አንሥተው ብይን ሊሰጡበት የሚገባ ነው::
ፌደሬሽን ም/ቤት መ/ቁ. 94/13
ግንቦት 30/2013 ዓ.ም
=================
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
https://t.me/judgeoffed