የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ውድቅ የተደረገበት ተከሳሽ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ? (ጠበቃ ካሊድ ከበደ)
***
ፍ/ቤቱ ከሳሽ ያቀረበውን ክስ እና ተከሳሽ ያቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት በአንድ ላይ ሲያከራክር:-
👉ተከሳሽ ያቀረበውን የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ከሳሽ ባቀርበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያ መሰረት ውድቅ አድርጎ ከሳሽ ወዳቀረበው ክስ ፍሬ ነገር ጉዳይ በማለፍ ግራ ቀኙን ለአንድ ዓመት ያክል ካከራከረ እና መዝገቡን ከመረመረ በኋላ ውሳኔ ሰጠ ብንል፤
"👉ተከሳሽ ፍ/ቤቱ ከአንድ ዓመት በፊት በሰጠው ብይን ውድቅ ባደረገበት የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ (ጉዳይ) ላይ ለበላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ማቅረብ የነበረበት/ያለበት ጊዜ መቸ ነው?"
ሀ/ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ውድቅ በማድረግ ብይን በተሰጠ እንደ ጉዳዩ ዓይነት በ2 ወር ወይም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ?
ለ/ ፍ/ቤቱ ከሳሽ ባቀረበው የፍሬ ነገር ጉዳይ ላይ ውሳኔ በሰጠ እንደ ጉዳዩ ዓይነት በ2 ወር ወይም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ?
መልሱ:- "ለ" ነው። (የፌ/ጠ/ፍ/ሰ/ሰ/ ችሎት በመ/ቁ. 231324 በቀን 26/03/2015 ዓ.ም የሠጠውን አስገዳጅ የህግ ትርጉም ይመልከቱ)