Репост из: ስለ ህግ
መ/ቁጥር 236316
መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም
ዳግም ዳኝነት - ይግባኝ ሊቀርብ ስለሚችልበት አግባብ
___///____
ዳግም ዳኝነት ተጠይቆ አቤቱታው የቀረበለት ፍርድ ቤት ወደ ፍሬ ጉዳይ ክርክሩ ከመግባቱ በፊት ዳኝነቱ እንደገና ሊታይ ይገባዋል ወይም አይገባውም በሚለው ነጥብ ላይ አስቀድሞ ውሳኔ መስጠት የሚገባው ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 6/4 አነጋገር መገንዘብ ይቻላል፡፡በዚህ መሰረት ዳኝነቱ እንደገና ሊታይ ይገባዋል ወይም አይገባዉም ሲል አዲስ ተገኘ የተባለዉን ማስረጃ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 6(1 እና 2) መመዘኛዎችን የሚያሟላ መሆን አለመሆኑን አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ በሚሰጠዉ ዉሳኔ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ እንደማይቻል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 6/4 ስር ተደንግጓል፡፡በዚህ አግባብ የተሰጠ ዉሳኔ ይግባኝ ሊባልበት የማይችል እንደመሆኑ እንደመጨረሻ ዉሳኔ ተቆጥሮ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ከሆነ ለሚመለከተዉ ሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ሊታይ የሚችል ነዉ፡፡
በሌላ በኩል የቀረበዉን የዳግም ዳኝነት አቤቱታ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 6(1 እና 2) መስፈርቶች አንጻር አይቶ ዳኝነቱ እንደገና ሊታይ ይገባዋል በሚል ፍርድ ቤቱ ዉሳኔ ወይም ትእዛዝ ከሰጠ በኋላ ዋናዉን ጉዳይ በተመለከተ የቀረበ ክርክር አዲስ ተገኘ ከተባለዉ ማስረጃ እና አስቀድሞ የቀረቡትን ማስረጃዎች በመመርመር እና በመመዘን አስቀድሞ የሰጠዉን ዉሳኔ በማሻሻል ወይም በመለወጥ ከተወሰነ የይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ሥልጣን የሚሆነዉ ዳግም ዳኝነት ጥያቄ ለማቅረብ መሟላት ስላለባቸዉ ቅድመ ሁኔታዎች መመርመር ሳይሆን በዋናዉ ጉዳይ ላይ የተሰጠዉን ዉሳኔ ተገቢነት እና/ወይም ሕጋዊነት መመርመር ላይ የተወሰነ ስለሚሆን ከዚህ አኳያ የተሰጠ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 6/4 ስር በተደነገገዉ መሰረት ይግባኝ የማይባልበት ነዉ ሊባል የሚችል አይደለም፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 42871 ፣75243 እና በሌሎች መዛግብት ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ተሰጥቷል