ከአልቦ ቅዝምዝም መባተት
(እኔ ሙዚቀኛ ነኝ)
ደራሲ ያዕቆብ ብርሃኑ
የሆነ ሰው ድንገት የሆነ
ቦታ አስቁሞ «ይሄንሁ
ሉ ዘመን ምን ስታደርግነበር ?» ብሎ ቢጠይቀኝ እላለሁ....
«እንደ እብዶች ጉባኤ በታወከች ከተማ፣ሀገር እና ዓለም መሃል ነፍሴን የማስጠልልባት የሆነች የፅሞና ጥጋት ሳስስ ነበር፡፡»
በእርግጥ ይህ ሀሰሳ ትርጉም ያለው፣ ሊኖሩለትስ የሚገባ ግብ ይሁን አይሁን አላውቅም፡፡ ግን በዘመኔ ሙሉ ከዚህ የሚልቅ ዓላማ ነበረኝ ለማለት አልችልም፡፡ መጀመሪያ በዚህች ግራ ገብ ከተማ መሃል መሸሸጊያ ሳጣ ወደ ተተው መካነ መቃብሮች ፣ ወደ ፈራረሱ መንደሮች ፣ ወደ ተራሮች በማቅናት ጽሞናዬን ሙጥኝ አልኳት፡፡
Art work Evening on Karl Johan Street by Edvard Munch