ከእግዚአብሔር ጋር መታገል
ዘፍጥረት 32
22፤ በዚያች ሌሊትም ተነሣ፥ ሁለቱን ሚስቶቹንና ሁለቱን ባሪያዎቹን አሥራ አንዱንም ልጆቹን ወስዶ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ።
23፤ ወሰዳቸውም ወንዙንም አሻገራቸው፥ ከብቱንም ሁሉ አሻገረ።
24፤ ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር።
25፤ እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ ነካው፤ ያዕቆብም የጭኑ ሹልዳ ሲታገለው ደነዘዘ።
26፤ እንዲህም አለው፡— ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። እርሱም፡— ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም፡ አለው።
27፤ እንዲህም አለው፡— ስምህ ማን ነው? እርሱም፡— ያዕቆብ ነኝ፡ አለው።
28፤ አለውም፡— ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና።
29፤ ያዕቆብም፡— ስምህን ንገረኝ፡ ብሎ ጠየቀው። እርሱም፡— ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? አለው። በዚያም ስፍራ ባረከው።
30፤ ያዕቆብም፡— እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች፡ ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው። (* ጵኒኤል የሚለውን ቃል የግእዝ መጽሐፍ ራእየ እግዚአብሔር ይለዋል።)
ያዕቆብ ከምድራዊ አባቱ ምድራዊ በረከትን ፈልጋ ማንነቱን ካደ አቅሙ የደከመው ይስሀቅ ያዕቆብን አምስቱ የስሜት ህዋሱን ቢጠቀምም ሊለየው አልቻለም ነበር::
-አይኖቹ ስለፈዘዙ አላወቀውም አይቶት ኤሳው እንዳልሆነ አለየውም
-ቢዳስሰውም የጠቦቶችን ለምድ በእጆቹና በአንገቱ ላይ ስላደረገ አሁንም አለየውም ነበር::
-የለበሰውም የወንድሙን መልካሙን ልብስ ስለነበር ጠረኑም የራሱ የኤሳው ነበር ::
-በድምፁ ኤሳው እንዳልሆነ ቢያውቅም እርግጠኛ አልሆንም ነበር::
-ምግቡንም ርብቃ ይስሀቅ እንደሚወደው አደርጋ ስለሰራችው ኤሳው እንዳልሰራው አላወቀውም ነበር ::
እግዚአብሔር ግን ልቦናን እና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነው በፊቱ ምንም የተሰወረ ነገር የለም ታዲያ ያእቆብም አሁን በእውነተኛ ማንነቱ በእግዚአብሔር ፊት እውነተኛ ውስጣዊ ለውጥን ፈልጎ ቀረበ ያዕቆብ ከኢየሱስ ጋር እስከ ንጋት ይታገል ነበር ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ ሲለው ያእቆብ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም ” አለ-እጅግ በህይወታችን የሚያስፈልገን ድንቅ ውሳኔ እና ጸሎት ያእቆብ ለመጀመሪያ ጊዜ እውነተኛ ማንነቱን ተናገረ ኢየሱስ ስምህ ማን ነው? ሲለው ያእቆብ ነኝ አለ::
ያእቆብ ከዚህ መንፈሳዊ ትግል የተነሳ ስሙ ተለወጠ እስራኤል ተባለ እስራኤል ማለት “ከእግዚአብሔር ታግሎ ያሸነፈ” ማለት ነው ከዚያ አስደናቂ ትግል በውኋላ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁት ሰውነቴም ድና ቀረች”ብሎ ውጤቱን ተናገረ ያእቆብ የወሰዳቸው እርምጃዎች እግዚአብሔርን በህይወቱ ፊት ለፊት እንዲያይ አድርገውታል እናንተዬ ያለ እውነተኛ መንፈሳዊ ትግል ለውጥ የለም፡፡
በእርሱ ፊት እራሳችንን ባዶ የምናደርግበት ብቻችንን የምንቀርበት በፊቱ ወድቀን እውነተኛ መዳሰስ እንዲመጣ ፊቱን ከምር የምንፈልግባቸው ጊዜያት ያስፈልጉናል ያእቆብ ከእግዚአብሔር ጋር ታግሎ አሸነፈ የሚለው ሀሳብ እግዚአብሔርን ማሸነፉ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ መሰጠቱ እና እውነተኛ መንፈሳዊ ለውጥን መፈለጉ እንደ ማሸነፍ የተቆጠሮለታል እግዚአብሔር በህይወታችን የበላይ በመሆኑ የአሸናፊነታችን ሁሉ ምንጭ ነውና ያእቆብ ከሰውም ከእግዚአብሔርም ጋር ታግለህ አሸነፍክ ተባለ፡፡
የወሰዳቸው እርምጃዎቹ እና ያሳለፈው ያ ድንቅ የትግል ሌሊት እግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንዲያይ አድርጎታል እኛም በእንደዚህ አይነት ውሳኔና ረሀብ በፊቱ ብንሆን እና ሳናቅማማ እራሳችንን በፊቱ ብንጥል እናየውና ተለውጠን እንቀራለን ያእቆብ ካደረጋቸው እርምጃዎች እጅግ የሚያስደስተኝ “ያእቆብም ለብቻው ቀረ” የሚለው ሀሳብ ነው በዛች አመሻሽ ቀን በሀሳብ እና በጉልበት ሊረዱት የሚችሉ ሰዎችን ሁሉ አሻግሮ ለብቻው ሆነ እውነተኛ ውስጣዊ ለውጥን ፈልጎአልና ውጫዊ ከበባን አስወገደ፡፡
አዎ በዚህ ግርግር በበዛበት እና የሰውን ቀልብ በተለያየ መልኩ የሚስቡ ነገሮች በበዙበት አለም ለብቻ በመሆን ለጌታ መገኘት የሚቻልባቸው አጋጣሚዎች የጠበቡ ቢሆንም እንደ እንደዚህ አይነት ጊዜዎችን አሳደን መፈለግ ግድ ይለናል በእነዚህ ጊዜዎች የምናሳልፋቸው በርከት ያሉ ሰአታት ወደ ፊት የሚኖረን ህይወትና አገልግሎት በእጅጉ ይወስኑታልና ያለመሰሰት እራሳችንን እግሩ ስር እንጣል የታሪኩ አስደናቂ ክፍል ኃያሉ እግዚአብሔር ያእቆብ እንዲያሸንፈው መፍቀዱ ነበር "ስንታገለው "እግዚአብሔር አይከፋውም ምክንያቱም ትግል መጠጋጋትን ይጠይቃል ወደ እግዚአብሔር በጣም ያቀርበናል እኛ ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብም እሱም ወደ እኛ እጥፍ ይቀርባል እኛም ተሀድሶ ያስፈልገናልና እንደ ያእቆብ በእውነተኛ ማንነታችን ከእግዚአብሔር ጋር እንታገል ወደ እርሱም እንቅረብ!
እንደ እግዚአብሔር ቃል እንዲህ ልባርካችሁ!
👉 ያዕቆብ ስሙ ወደ እስራኤል እንደተለወጠ እግዚአብሔር የማይከበርበት የማጭበርበር ሕይወታችሁ ክፍል ከእናንተ ላይ ይወገድ!
👉 እግዚአብሔር ብቻችሁን ለራሱ ሐሳብ ያግኛችሁ!
👉 እግዚአብሔር የእናንተን አልሰበር ያለ ማንነት የቱ ጋር ቢነካችሁ እንደምትለወጡ ስለሚያውቅ ሹልዳችሁን ይንካችሁ!
👉 ለራሳችሁ ሐሳብ አስነክሶ ለራሱ ፈቃድ ያስሩጣችሁ!
👉 የሚቀር የትላንት ጠባሳ የትላንት ፅፅት ሳያገኛችሁ ድናችሁ ቅሩ
👉 ጵኒኤል ይሁንላችሁ
👉ሰው በባህሪው በሕይወታችን ለሊት ይርቀናል ይተወናል እግዚአብሔር ደግሞ በባህሪው በሕይወታችን ለሊት እኛን ማግኘት ይጀምራል የሕይወታችን ለሊት አንድ ሆነን ገብተን ሕዝብ ሆነን የምንወጣበት ጊዜ እንደሆነ ከባዱን ሁኔታ ብቻንን ተጋፍጠን በረከቱ ግን ለትውልድ ሁሉ የሚሆንበት ምሽት እንደሆነ እንደዛ ብቻችሁን የምታሳልፉት የሕይወታችሁ ምእራፍ እግዚአብሔር ለትውልድ እንድትተርፉ አድርጎ ያሻግራችሁ!
👉የነገርኩህን እስካደርግልህ ድረስ አልተውህም ብሎ ለያእቆብ ሰማይ ቃል ኪዳን እንደገባለት እንዲሁ የነገራችሁን እስኪያደርግላችሁ ድረስ የማይተዋችሁ አምላክ ፍፃሜያችሁን በድል ይቋጨው!
👉እኔ እኔ ነኝ እኔ አልለወጥም ያለ እግዚአብሔር በሚለወጥ ሰውና ሁኔታ መሃል ሌላ አጋዥ ሌላ አበርቺ እስከማያስፈልጋችሁ ድርስ እያበረታ ከግብ ያድርሳችሁ!.