የሳምንቱ ባርኮት❤️
📖 ትንቢተ ኢሳይያስ 54 17
በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር።
🖐 እግዚአብሔር ይባርካችሁ፥ ስራችሁ ላይ፤ ጤንነታችሁ ላይ፤ ትምህርታችሁ ላይ፤ እግዚአብሔር የከፈተላችሁ በር ላይ፤ ከፍቶ ወጥታችሁ እንድትሠማሩ በፈቀደላችሁ ምንም ነገር የቀና፤ አይኑ የቀላ የትኛውም የጠላት ምክር በህይወታችሁ አይፈጸም፣ ምክራቸውን ከንቱ ያድርግላችሁ
🖐 እስከዛሬ ከብዙ ወጥመድ እያዳነ፤ ከብዙ ቀስት እያስመለጠ ከተለጠጠባችሁ ጦር፤ ከተሰበቀባችሁ ጦር እያዳነ እዚህ ያደረሳችሁ እግዚአብሔር አሁንም ከክፉ፤ አሁንም ከሚመከርባችሁ የትኛውም ከንቱ ምክር፤ ደግሞ ፈገግ ብለው ፊታችሁ ከሳቁ፤ ከጀርባችሁ ክፉ ከሚያስቡና ክፉ ከሚመክሩ ክፉዎችና ሀኬተኞች፤ ተንኮለኞች ሰዎች እጅ እግዚአብሔር ከእነሱ ምላስና ከንቱ ንግግር ጭምር እግዚአብሔር ያድናችሁ
🖐 ከክፉ መካር ያድናችሁ፣ ከዲያብሎስ ያድናችሁ ሞታችሁን ከሚፈልጉ ጠላቶቻችሁ እግዚአብሔር አሁንም ያድናችሁ፣ ምክራቸውን እንዳይፈጽሙ የተንኮለኞችንና የክፉ ሠዎችን ምክር እግዚአብሔር በላያችሁ ከንቱ ያድርግ
🖐 መውደቃችሁን ከሚናፍቁና ከሚጠባበቁ፤ ካሁን አሁኔ አቃተው፤ ወደቀ፤ ደከመው ብለው ከሚመክሩ ክፉ ሰዎች ምክርና ሀሳብ ሁሉ እግዚአብሔር የያድናችሁ፤ ይጠብቃችሁ፤ ደግነቱ በላያችሁ ይሁን፣ እግዚአብሔር እያወጣ ያስገባችሁ፣ ይንከባከባችሁ፣ በእነዛ ሰፊ እጆቹ ይያዛችሁ፣ እግዚአብሔር ከጠላቶቻችሁ አሁንም ያድናችሁ
🖐 እንዲህም ብዬ ባረኳችሁ፥ ምክራቸውን እንዳይፈጽሙ እግዚአብሔር የጠላቶቻችሁን ሀሳብና ምክር ከንቱ ያድርግላችሁ 🙏
🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐
በኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን ሀልዎት አጥቢያ
አድራሻ፦ ወሎ ሰፈር ጎርጎሪዮስ አደባባይ ፊውቸር ታለንት
ት/ት ቤት አጠገብ