በማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል የነድያን ጉባኤ ተካሄደ
መጋቢት ፲፮/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል ከየግዮን ወረዳ ማእከል ስብከተ ወንጌልና ከዜማ ክፍል አስተባባሪነት በባሕር ዳር ከተማ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ከጽዋ ማኅበራት፣ ከቤተ ክርስቲያን ወጣቶች እና ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ ጋር በመሆን በአብይ ጾም ፭ኛ ሳምንት በእለተ ደብረ ዘይት የነድያን ጉባኤ ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ከ300 በላይ ነድያንና ከ150 በላይ የአብነት ደቀ መዛሙርት የተገኙ ሲሆን የደ/ም/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ አባ ገብረ ማርያም ተጠምቀ መድኅን "ይህ በጎ ነገር ተጠናክሮ እንዲቀጥል እኛም እንደ ቤተ ክርስቲያን መሪ የሚጠበቅብንን እናደርጋለን" የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።
በስፍራው ተገኝተው መርሐ ግብሩ እንዲሳካ ትልቅ ድርሻ የነበራቸው የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች እና የቤተክርስቲያኗ ወጣቶችም እንዲህ ከፍ ወዳለ ሥራ እና አገልግሎት መሸጋገር እጅግ እንደ ሚያስደስት ገልጸው ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህ ባለ በጎ ተግባር ልምዱን ስላካፈላቸውም አመስግነው ወደፊትም በተመሳሳይ አገልግሎት አብረው ለማገልገል ፈቃደኞች መሆናቸውንም ገልጸዋል።
የወረዳ ማእከሉ ስብከተ ወንጌልና ዜማ ክፍል ኃላፊ አቶ አራጋው ፈጠነ እንደተናገሩት እንዲህ ዓይነቱን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ሁላችንም ዓላማውን መረዳት የሚጠበቅብን ሲሆን ይሄ ጉዳይ ለተወሰኑ አካላት የሚተው ሳይሆን የቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌልም አቅዶ መስራት እንዳለበት ገልጸዋል።