የግዮን ወረዳ ማእከል ሰብሳቢ አቶ ማረልኝ ዳኛው በመልእክታቸው የቤተክርስታያን ጠባይ ሕብረታዊነት በመሆኑ ሁላችንም ብንሆን በተናጥል ሰርተን ውጤት አናመጣም፤ ልክ ዛሬ ለዚህ መርሐ ግብር መሳካት ሰ/ት/ቤቶች እና ወጣቶች ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በአንድነት፣ በትብብር እንደሠራነው ሁሉ ወደፊትም በሌሎች ትላልቅ የቤተክርስቲያኗ ጉዳዮች ላይ በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
አክለውም ይህ ታላቅ በጎ ሥራ እንደሆነ ገልጸው በዚህ መርሐ ግብር የተሳተፉትን በቁስም፣ በተሽከርካሪ፣ በጉልበትና በእውቀት የተሳተፉትን አመስግነዋል።
በመጨረሻም የቤተክርስቲያኑ ስብከተ ወንጌል ኃላፊ የሆኑት መጋቢ ሃይማኖት ቀሲስ ማሩ አላምራው ለነድያን አባታዊ ምክር ከሰጡ በኋላ ለነዳያን የምገባና አልባሳት ስጦታ ተበርክቶላቸው በጸሎት ተፈጽሟል።