ለአንድ ወር ያህል ሲሰለጥኑ የቆዩ ሠላሳ ተተኪ መምህራን በሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም መመረቃቸው ተገለጸ
መጋቢት ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም
የሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ትምህርት ቤት ከሰበካ ጉባኤውና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ለአንድ ወር ያህል ያሠለጠናቸውን ሠላሳ ተተኪ መምህራን በትናትናው ዕለት መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ማስመረቁ ተገልጿል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ የሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም አባ ሀብተ ማርያም ወልደ ጊዮርጊስ፣ የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር አባል ሊቀ ትጉኀን ቀሲስ ሙሉጌታ ስዩም (ዶ/ር) ፣ በሰሜን አሜሪካ በዴንቨር ኮሎራዶ ሀገረ ስብከት የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው ፣ የማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት ም/ሥራ አስኪያጅ ዲያቆን ሲሳይ ብርሃኑ፣ የበገና ዘማርያንና ምእመናን ተገኝተዋል።
መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው እንደገለጹት መምህርነት ማለት አደራና ጸጋ በመሆኑ መመረጥ፣ መቀደስ፣ ማስተማርን ይጠይቃል ያሉ ሲሆን ከጠረፋማ ና ከገጠራማ አካባቢ የመጡ ተመራቂ ተተኪ መምህራንን በኀላፊነት አከባቢያቸውን በቋንቋቸው እንዲያገለግሉ መክረዋል።
የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሰብሳቢ መምህር እንዳለ ጸጋዬ ለሥልጠናው የበኩላቸውን ድርሻ ላደረጉ ተቋማት፣ ማኅበራት፣ ጉባኤያት፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሚገኙ አባላት እንዲሁም ምእመናንን አመስግነዋል።