የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር አባል የሆኑት ሊቀ ትጉኀን ቀሲስ ሙሉጌታ በበኩላቸው ሥልጠናው ከየካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መጋቢት 21 ቀን ጀምሮ ለሠላሳ ቀናት ትምህርተ ሃይማኖት ፣ ነገረ እግዚአብሔርና ሥነ-ፍጥረት) ፣ አምስቱ አእማደ ምስጢር ፣ ሐዋርያዊ ተልእኮ እና የስብከት ዘዴ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፣ ነገረ ማርያም እና ነገረ ቅዱሳን ፣ ነገረ ቤተ ክርስቲያን እና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ፣ የቤተ ክርስቲያን ምስጢራት እና ሥርዓት ፣ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር እና መንፈሳዊነት ፣ ባሕል እና ክርስትና ፣ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ቃለ አዋዲ ፣ የአገልግሎት መሪነት (አስተባባሪነት) ፣ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር እና ኪነ-ጥበብ ፣ የአሕዛብና መናፍቃን ጥያቄዎቻቸውና መልሶቻቸው የሚሉ ሥልጠናዎችን መውሰዳቸውን ገልጸዋል።
ለተተኪ መምህራኑ ”የዚህ ሥልጠና ስኬታማነት የሚለካው በቆይታችሁ ባገኛችሁት ዕውቀት ብቻ ሳይሆን በምትሰማሩበት የሐዋርያዊና የእረኝነት አገልግሎት የድካምና የመሰልቸት መንፈስ ሳይሰማችሁ ስታገለግሉና ነፍሳትን ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትቀላቅሉ ብሎም ወደ ቅድስና ሕይወት ስትመሩ ነው“ በማለት ምክር ለግሰዋል ፡፡
በመጨረሻም ለተተኪ መምህራኑ የምስክር ወረቀት የመሥጠት መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን የደብሩ አስተዳዳሪ ”ከጠረፋማ አካባቢ ተተኪ መምህራንን አምጥቶ ማሠልጠን አዲስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ መመሥረት ነው የሚቆጠረው“ ብለው በመግለጽ መልእክትና አባታዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።