አራቱ ተግባቦቶች!
ከሰዎች ጋር ዕለት ተዕለት በሚኖረን ግንኙነት ወቅት የሚኖረንን የተግባቦት አይነቶች በአራት ከፍለን ማየት እንችላለን።
1- Aggressive (ቁጡ/ሃይለኝነት ያጠላበት):-
እነዚህ ሰዎች ሃሳባቸውን በሃይለ ቃል እና በስሜታዊነት በመግለጽ ይታወቃሉ። ሲያወሩ ጠረጴዛ እየደበደቡ፣ ደምስራቸው ተገታትሮ፣ በከፍተኛ የንዴት ስሜት ውስጥ ሆነው፣ ቡጢ ጨብጠው ነው። የራሳቸውን ሃሳብ ሌሎችን በሚጎዳ መልኩ መግለጻቸው ችግር ይፈጥራል።
2- Passive:-
ሁሉን በጸጋ የሚቀበሉ፣ ሽቁጥቁጥ፣ ሃሳባቸውን ለመግለጽ ፈራ ተባ የሚሉ አይነት ናቸው። እነዚህ ሰዎች ችግር ቢከሰት ባይከሰት የማይደንቃቸው፣ ለስሜታዊነት ሩቅ የሆኑ፣ ነገር በሩቅ የሚሸሹ ናቸው። የራሳቸውን ጥቅም ለሌሎች በማሳለፋቸው ምክንያት ለብዝበዛ ሊጋለጡ ይችላሉ።
3- Passive-Aggressive:-
እነዚህ ሰዎች የታመቀ ሃይለኝነት ቢኖራቸውም ሃሳብ አስተያየታቸውን ፊት ለፊት ለማቅረብ ይፈራሉ። ይልቁንስ ብስጭት እና ቅሬታቸውን በህቡዕ መፈጸም ይቀናቸዋል። ማለትም ስም በማጥፋት፣ ስራን በማበላሸት፣ በመለገም እና በመሳሰሉት ንዴታቸውን ሲገልጹ ይስተዋላሉ። እነዚህ ሰዎች ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች አደገኞች ናቸው።
4- Assertive:-
ሃሳብ አስተያየታቸውን ሚዛናዊ በሆነ ሁኔታ በቀጥታ መግለጽን የተካኑ ናቸው። እንደነዚህ አይነት ሰዎች የሚፈጠሩ ቅራኔዎችን በጥበብ መፍታት መለያቸው ነው። በዚህም መሰረት ሁለቱንም ወገን የሚጠቅም መፍትሄ ላይ ይደርሳሉ።
እናንተስ ከሰዎች ጋር ስታወሩ፣ ስታወጉ፣ ስትወያዩ አልያም ስትከራከሩ የትኛውን አይነት ተግባቦት ትጠቀማላችሁ?
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
@melkam_enaseb