የተጎዳ ስሜትና የተዛባ ስነ-ልቦና ምልክቶች!
የስሜት ጉዳት ወይም የስነ-ልቦና መቃወስ መንስኤዎችና ምልክቶቹ በርካታ ናቸው፡፡ የስሜት ጉዳት እና የስነ-ልቦና መቃወስ ስር ሳይሰድ በጊዜ መፍትሄ ካላገኘ የሚያስከትለው ችግር ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ መፍትሄ ለመፈለግ ከሚረዱን ምልክቶች መካከል አንዱን እንጥቀስ፡፡ ይህ ምልክት ከአንዱ ጥግ ወደ ሌላው ጥግ የሚወዛወዝ ሁኔታ ጉዳይ ነው፡፡
1. በሆነ ባልሆነ ማልቀስ፣ ወይም ደግሞ ትርጉም በማይሰጥ ነገር በጣም መሳቅና የተደሰቱ ማስመሰል፡፡
2. ዝም ማለትን ማዘውተር፣ ወይም ደግሞ ብዙ የማውራት ዝንባሌ፡፡
3. ካለልክና ብዙ መመገብ፣ ወይም ደግሞ ምግብን መመገብ አለመቻል፡፡
4. ከልክ በላይ ብዙ መተኛት፣ ወይም ደግሞ እንቅልፍ በማጣት መቸገር፡፡
5. በትንሹም በትልቁም ለሁሉም ነገር መጨነቅና አጉል መጠንቀቅ፣ ወይም ደግሞ ለሁሉም ነገር ግድ የለሽ መሆንና ራስን መጣል፡፡
6. ከሰዎች ጋር ካለልክ መጣበቅና ትኩረትንና አብሮነትን መፈለግ፣ ወይም ከሰዎች ሁሉ መራቅና ለብቻ መሆንን ማዘውተር፡፡
7. ሰዎች ስለእኛ ምን እያሰቡ እንደሆነ መገመትና መጨናነቅ፣ ወይም ስለማንም ሰው ምንም ግድ ያለመስጠትና ፀረ-ማህበራዊ ባህሪያትን መግለጽ፡፡
ሁላችንም ብንሆን አልፎ አልፎ እንደዚህ አይነት ልምምዶችን ልንለማመድና መለስ ልንል እንችላለን፡፡ ሆኖም፣ ሁኔታው ለሳምንታትና ለወራት ከቆየና የማይቀንስ ከሆነ ችግሩ በራሱ ይሄዳል ብሎ ከማሰብና ለመቀልበስ አስቸጋሪ የሚሆንበት ደረጃ ላይ እስከሚደርስ ከመጠበቅ የራስ በራስ እርምጃና ማስተካከያ መውሰድ፣ አልሆን ካለ ደግሞ የባለሞያ እገዛ ማግኘት አስፈላጊ ነው፡፡
(ዶ/ር እዮብ ማሞ)
@melkam_enaseb