የባለትዳሮችን ግንኙነት የሚያጠናክሩ ነጥቦች!
በፍቅር ጓደኝነት የተጀመረ ወዳጅነት ወደ ትዳር ከፍ ሲል ተቋማዊ መልክን ይይዛል፡፡ በዚህ ጊዜ በሁለት ጥንዶች መካከል ከህይወት ውጣ ውረድ፣ ከልማድ፣ ከፍላጎት መለያየት እና ከሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ ጥል እና መጨቃጨቅ ይከሰታል፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ውጤታማ ልማዶች ታዲያ በትዳር አጋሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚያግዙ ባለሙያዎች ይመክራሉ።
1.የጋራ ፍላጎቶችን መፍጠር
ባለትዳሮች በጋራ የሚዝናኑባቸውን እና አብረው ጊዜ የሚያሳልፉባቸውን ለሁለቱም ተስማሚ የሆኑ ቦታዎች እና ሁነቶችን ሊፈጥሩ ይገባል፡፡ እነዚህ ተደጋጋሚ ልማዶች ጤናማ እና ደስተኛ ግንኙነት ለመገንባት አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፤ በተጨማሪም የመተዋወቅ እና ስሜትን የመጋራት ሁኔታን ይፈጥራሉ፡፡
2. አብሮ መመገብ
ማዕድ መጋራት ወይም አብሮ መመገብ ምንም እንኳን ቀላል ነገር ቢመስልም በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ በጋራ ገበታ ላይ መቀመጥ የባለትዳሮችን አብሮነት ከፍ የሚያደርግ ነው፡፡ ምንም እንኳን በቀን ውስጥ ሁሉንም ሰአት አብሮ መመገብ የማይቻል ቢሆንም በተገኘው አጋጣሚ በምግብ ዙርያ የሚወሩ ወሬዎች ስለ ቀን ውሎ ለመነጋገርና ሀሳብ አሰተያየት ለመጋራት እድል ይሰጣሉ።
3.ከዘመድ እና ወዳጅ ጋር በቤት ውስጥ አብሮ ማሳለፍ
በተቻለ አቅም ከቤተሰብ እና ከጓደኛ ጋር የጋራ ጊዜን ማሳለፍ፣ የህይወትን አጋጣሚዎች፣ በጋራ ማጣጣም እና ማክበር ቢቻል በጥንዶች መካከል የእኔነት ስሜትን ይፈጥራል፡፡ እንደ ባልና ሚስት የመግባባት ስሜት ከማሳደጉም ባለፈ ከጓደኞች እና ቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ውብ ትውስታዎችን በመፍጠር ግንኙነቱን ያጠናክራል፡፡
4. ከግጭት በኋላ ስሜትን መገላለጽ
በጥንዶች መካከል መዋደድ እና መፋቀር እንዲሁም ጥሩ ጊዜዎች እንዳሉ ሁሉ መጣላት፣ መጨቃጨቅ፣ በሀሳቦች ያለመስማማትም በግንኙነት ውስጥ የሚያጋጥም ነው፡፡ ግጭት ተፈጥሯዊ ቢሆንም ጥሉን ለመፍታት ሰዎች የሚከተሉት መንገድ ጤናማነት ግንኙነቱን ለማስቀጠል እና መግባባትን ለመፍጠር ወሳኝ ነው፡፡ ለዚህም ግጭቱን ስለፈጠረው ምክንያት በእርጋታ መመካከር ስለመፍትሄው መወያየት እና ከማንኛውም አለመግባባት በኋላ ሁለቱም ወገኖች ይቅርታ በመጠየቅ ህይወታቸውን ሊቀጥሉ ይገባል፡፡
በተጨማሪ: ባህላዊ እና ሀይማኖታዊ ሁነቶች ላይ በጋራ መታደም፣ የስፖርት እና የዳንስ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ፣ ስነጥበባዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ልምድን ማዳበር የባለትዳሮችን ጥምረት ለማጠናከር ይረዳሉ ተብለው ከተጠቀሱ ነጥቦች መካከል ናቸው፡፡ Via: Alain
@melkam_enaseb