የ “trauma” ትርጉም
'trauma' ለሚለው ቃል እቅጩን የሆነ የአማርኛ መተኪያ ቃል ለማግኘት ቢያስቸግርም፣ “የስሜት ቀውስ”፣ “የስ-ልቦና ስቃይ”፣ እና የመሳሰሉትን ገላጭ ሃሳቦች መጠቀም እንችላለን፡፡
• “trauma” ማለት “ለአሰቃቂ ክስተት የሚሰጥ ስሜታዊ ምላሽ” ማለት ነው፡፡
• ሰዎች ባጋጠማቸው “ይጎዳኛል” ወይም “ያስፈራል” ብለው በሚያስቡት የአካል ወይም የስሜት አስቸጋሪ ሁኔታ የተነሳ የ “trauma” ልምምድ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡
• አንድ ሰው በ “trauma” ልምምድ ውስጥ ካለፈ በኋል የጉዳት ስሜቱና ምልክቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወይም ከረጅም ጊዜ በኋላ ሊከሰት ይችላል፡፡
• ከዚህ ልምምድ በኋላ ሰዎች ከአቅም በላይ የሆነ ነገር እንደተከሰተ የመሰማት ሁኔታ፣ አቅመ-ቢስነት ወይም ድንጋጤ ሊሰማቸው ይችላል።
• አንድ ሰው የደረሰበትን “trauma” በሚገባ መፍትሄ ካላገኘለትና ሁኔታው ከተባባሰ የአእምሮ ጤንነትን ወደማወክ ደረጃ ሊደርስ ይችላል፣ ወይም ደግሞ post-traumatic stress disorder (PTSD) ወደተሰኘው ደረጃ ሊደርስ ይችላል፡፡
የ “trauma” መነሻ የሚሆኑ ልምምዶች
ከዚህ በታች በሁለት ክፍል ተለይተው የተዘረዘሩትን የ “trauma” አይነቶች ለመንደርደሪያነት በመጠቀም ሌሎች ለዚህ ስሜት ተጋላጭ እንድንሆን የዳረጉንን ሁኔታዎች መለየት እንችላለን፡፡
የልጅነት “trauma” ምሳሌዎች
- ለእድሜ የማይመጥን ስራን ሰርቶ ማደግ፣ ጨዋታን ተከልክሎ ማደግ፣ በቤተሰብ (በአሳዳጊ) ስድብንና የቃላት ጥቃትን አስተናግዶ ማደግ፣ ከፍተኛ አደጋ አይቶ ማደግ፣ የወሲብ ጥቃትን ወይም ሙከራን አስተናግዶ ማደግ፣ አካላዊ ድብደባን አስተናግዶ ማደግ፣ ጉልበተኝነት (bullying) አስተናግዶ ማደግ ይጠቀሳሉ።
የአዋቂነት “trauma”
- የዘረኝነት ጥቃት፣ ጦርነት አካባቢ መኖር ወይም መገኘት፣ የአስገድዶ መደፈር ጥቃት፣ አሰቃቂ የትራፊክ ወይም የተፈጥሮ አደጋ፣ ለሕይወት አስጊ የሆኑ የጤና ሁኔታዎች፣ የሚወዱትን ሰው በድንገት ማጣት፣ የሽብርተኝነት ድርጊቶች ይጠቀሳሉ።
(ዶ/ር እዮብ ማሞ)
@melkam_enaseb