ከንቱ መመካት ያሳልፍባቸዋል፡፡ እንዲህ ያሉ መራጮችን እግዚአብሔር ‹‹ነገር ግን በውበትሽ ታምነሻል›› ይላቸዋል፡፡ /ሕዝ 16÷15/ አንዳንዶቹን በመልካቸው የተፈላጊነት ስሜት እንዲሰማቸው በማድረግ አመንዝራ ያደርጋቸዋል፡፡ ውበታቸው ፍቅራቸው እየሰመላቸው ለማመንዘር ቅርብ ናቸው፡፡ ‹‹ውበትሽን በጊዜ ተጠቀሚ›› በሚል ዓይነ ጥላዊ ፈሊጥ በዝሙት መርመርመጥ ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ እንደዚህ የሚሆኑትን ሴቶች ነብዩ ሕዝቅኤል ‹‹በየመንገዱ ራስ ከፍ ያለውን ቦታሽን ሠራሽ፣ውበትሽንም አረከስሽ፣ለመንገድ አላፊም ሁሉ እግርሽን ገለጥሽ ግልሙትናሽንም አበዛሽ›› በማለት ይወቅሳል፡፡ /ሕዝ 16÷25/
ወዳጆቼ ዓይነ ጥላው ውበታቸውን ለትዳር ሕይወት ሳይሆን ለዝሙት ያደርግባቸዋል፡፡ ዝነኞችንና ታዋቂዎችን ደግሞ ዓይነ ጥላቸው መልካቸውን ለትዳር ሳይሆን ለከንቱ ነገር እንዲያውሉት ያደርጋቸዋል፡፡ ስምና ዝናቸውን ተጠቅመው በትዳር ከመኖር ይልቅ የማመንዘር ሕይወትን እያዳበሩ በውበት እና በዝናቸው እየኮሩ እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡ እነዚህም ‹‹ስለ ዝናሽ አመንዝረሻል፣ምንዝርናሽንም ከመንገድ አላፊ ሁሉ ጋር አበዛሽ›› ተብለዋል፡፡ /ሕዝ 16÷15/
ዓይነ ጥላ ያለባት መልከኛ ሴት ምናልባት አንድ ወንድ ወድዋት ተግባብቷት፣ተቀራርቧት ማውራት ሲጀምሩ ዓይነ ጥላው ፊትዋ ላይ፣ዓይኗ ላይ ግንባርዋ ላይ ጠቀምጦ ለሚወዳት ወንድ ኃይለኛ፣ነገረኛ፣ቁጡ ሴት አድርጎ ያሳየዋል፡፡ የሚገርመው እሷ ግን ጤናማ ፊት ይዛ የምታወራው ነው የሚመስላት፡፡ ወንዱ ነገ ቢያገባት ሊመጣበት የሚችውን የትዳ ተግዳሮት በማሰብ ይርቃታል፡፡ ደግሞ ከአንዱ ጋር የጓደኝነት ሕይወት ትጀምራለት፣የፍቅር ሕይወት ውስጥ ከገባች በኃላ የወደደችው ወንድ ያለ ምንም ምክንያት ይርቃታል፡፡
አንዳንዱ ወንድ ደግሞ አንሶላ ከተጋፈፋት በኃላ ይሸሻታል፡፡ በዚህም ወንድ መጥላት ይጀምራሉ፣ወንድ አያምኑም በዚህ የተነሳ ሳያገቡ ይቀራሉ፡፡ እጅግ የሚገርመው ደግሞ ለሴቶች ለትዳር መልካምና መንፈሳዊ ናቸው የተባሉ ወንዶች በአንድም በሌላም ይመጣላቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላው ግን የመገርገር ሥራ እየሠራ የሚመጡትን ወንዶች ከሕይወት መንገዳቸው ላይ ይመልስባቸዋል፡፡ ወንዶች ለትዳር ይመጣሉ ቁም ነገሩ ላይ ግን ባዶ ይሆናሉ፡፡
ዓይነ ጥላው የሴትችን የትዳር እድላቸውን በተለያየ መንገድ ማጨናገፉ ምን ዓይነ ጥላዊ የክፋት ጥቅም ያገኛል? ካልን፡፡ አንደኛ ከትዳር ዓለም ያርቃቸዋል፡፡ ሁለት ካገቡ ዘር ይተካሉ ስለዚህ የልጅ ጸጋ እንዳይኖራቸው ያደርጋቸዋል፡፡ ሦስት የቤተሰባቸው ጥገኛ እና ተጧሪ ያደርጋቸዋል፡፡ አራት የሰውን ሕይወት እያዩ በቅናት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡ አምስት ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ ስድስት ተስፋ ስለሚቆርጡ ለዝሙት ሕይወት ይዳርጋቸዋል፡፡ ሰባት በእግዚአብሔር እና በእምነታቸው ተስፋ የማስቆረጥ ሥራ ይሰራባቸዋል፡፡ ስምንት ወንድ ጠል ያደርጋቸዋል፡፡ ዘጠኝ ሕይወታቸውን የቀን ጨለማ አድርጎ በማሳየት በሥራቸው ውጣታማ እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ አስር ለምን እና ለማን እንደሚኖር ግራ እያጋባቸው ከራሳቸው፣ከቤተሰባቸው እያጣላቸው ያኖራቸዋል፡፡
ተወዳጆች ሆይ ትዳር ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ በረከት ነው፡፡ ከእግዚአብሔር መልካም ስጦታዎች ውስጥ አንዱ ትዳር ነው፡፡ የትዳር ሕይወት በምድር ሳይሆን በሰማይ ቤት በእግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃድ የተጀመረ የቅድስና ሕይወት ነው፡፡ አዳም እና ሔዋን የተጋቡት በምድር ሳይሆን በሰማይ ነው፡፡ አዳምና ሔዋን በሰማይ የጀመሩትን የበረከት የቅድስና ሕይወት ነው እኛ በምድር የምንኖረው፡፡
ስለዚህ ይህንን የቅድስናና የበረከት ሕይወት ዓይነ ጥላው ስለሚጠላ የትዳር መልካም አጋጣሚያችንን፣ጥሩ እድላችንን የራሳችን ሐሳብ በሚመስል ውስጣዊ ተንኮል ሲከላከል ይኖራል፡፡ እኛም ወደ እኛ የሚመጡትን የትዳር ፈቃዶችን በራሳችን ምዘና ‹‹አይሆነኝም፣አይመጥነኝም›› በማለት በመግፋት እንኖራለን፡፡ በመጨረሻ የመራጭ ነገር ተመራጭም የመሆን እድል ስለማይኖረው ዓይነ ጥላው የእሱን ፍላጎት በእኛ ሕይወት በማጎልበት የባዶነት ኑሮን ያስታቅፈናል፡፡
አንዳንዶችን ደግሞ ለትዳር ሲጠየቁ ዓይነ ጥላቸው ከትዳራቸው ትምህርታቸውን እያስቀደመ ‹‹ቆይ የጀመርኩትን ትምህርት ዳር ላድርስ ልጨርስ፣ማስተርሴን ልያዝ›› እያሉ የወጣትነት ዘመናቸውን በትምህርት ያሳልፉና ትዳር በሚፈልጉበት ጊዜ ዓይነ ጥላው ለሚፈልጋቸው ሰው ትልቅ ሰው፣ጎልማሳ በማስመሰል እያሳየ ወንድ እንዲርቃቸውና ትዳር እንዳይዙ ያደርጋቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላው አግብተው መማር እንደማይችሉ እያሳሰባቸው ለፍቅር፣ለትዳር ሕይወታቸው ሳይሆን ለትምህርታቸው ቅድሚያ እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል፡፡ ተምረው ጥሩ ደገጃ ከደረሱ በኃላ ያለ ፍቅር፣ያለ ትዳር መኖር ባዶነት መሆኑን ሲረዱ ሞራላቸው እየከሰመ፣የመኖር ትርጉሙ እየመነመነ ሲመጣ ‹‹ለማን ነው የምለፋው፣ለማነው የምኖረው፣ለአንድ ራሴ ምን አስጨነቀኝ›› በማለት የሕይወት ውድቀት ውስጥ ይገባሉ፡፡
ይህ የሴቶች ብቻ ሳይሆን የወንዶችም ትልቅ ችግር ነው፡፡ ወንዶቹ ‹‹ተምሬ፣ሠርቼ ከብሬ፣አንድ ነገር ይዤ ነው የማገባው›› እያሉ እድሜአቸውን ያለ ትዳር እንዲገፉ ያደርጋቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላው የኑሮን ውድነት እያሳሰባቸው፣ገና ለገና በቤት ኪራይ ልኖር ነው እያስባላቸው ከትዳር በማዘግየት፣የትዳር ሕይወታቸውን መቅጨት፣ እድሜአቸውን ማሳለፍ ይጀምራል፡፡
በተለይ በዚህ ዘመን የተጠናወተን ዓይነ ጥላ በዘር በብሔር ከለላ ግብቶብን ‹‹የራሴ ዘርና ብሔር ካልሆነ አላገባም›› እያስባለን ሰውን ሳይሆን እንደ ገበሬ ዘርን እንድንመርጥ ያደርገናል፡፡ ገነት በየብሔራችን የምንገባ ይመስል መንፈሳዊ ነን የምንለውም ከትዳር መሠርት ውስጥ ሃይማትን ሳይሆን ዘርን መርጠን ትዳር አልባ እንሆናለን፡፡
ተወዳጆች ሆይ ከዚህ ቀደም የጠፋው ጠፍቷል ከዚህ በኃላ ትዳር እና ልጅ ጠል በሆነው በዓይነ ጥላ መንፈስ፣የነገ ሕይወታችን እንዳይቃወስ ቆም ብለን እናስብ፡፡ በአንድም በሌላም ወደ እኛ የሚመጡትን የትዳር መልካም አጋጣሚዎችን ዓይነ ጥላችን እየገፋ፣የሚመጡትን እያስከፋ ከሚኖሩት በታች ከሞቱት በላይ አድርጎ እንዳያስቀረን ተንኮሉን ልንነቃበት እና ልናውቅበት ይገባል፡፡
ደግሞ ገና ለገና የትዳር እድሌን ዓይነ ጥላ ሳያበላሽብኝ ብላችሁ ዘው ብሎ ከመግባት ሁነኛውን ሰው በጸሎት መለየት ያስፈልጋል፡፡ ግን ‹‹በውበትም ፋንታ ጠባሳ ይሆናል›› እንደተባለው ውበታችን የሕይወት መጥፎ ጠበሳ እንዳይሆን ልናስብበት ይገባል፡፡ / ኢሳ 3÷24/
ክፍል ሦስት
ከሰው የማያግባባ ዓይነ ጥላ
/ሰው አልባ፣ሕይወት አልባ የሚያደርግ/
ይቀጥላል ….