ደብተራዎቻችን Vs Psychiatry
Psychiatry ከህክምና ዘርፎች አንዱ ሲሆን ትኩረት አድርጎ የሚሰራው የአእምሮ በሽታዎች ላይ ነው። ይህ የህክምና ዘርፍ ለመፈወስ ከሚሰራባቸው በሽታዎች መካከል፦ የመርሳት ችግር ፣ ከእውነታ ማፈንገጥ ፣ አስከፊ የፀባይ መለዋወጥ እና ከአስተሳሰብ ጋር ተዛማጅ የሆኑ በሽታዎች ተጠቃሽ ናቸው።
የምእራቡ አለም ምሁራን ይህን የህክምና አገልግሎት እንደ አንድ ዘርፍ ተቀብለው በዘመናዊ መንገድ መስጠት የጀመሩት ወደ ሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ነበር። በተለይ በጣም አስቸጋሪ ለሆኑ የአእምሮ በሽታዎች መድሃኒት ማግኘት የጀመሩት 21 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ቢሆንም አሁን ድረስ ፈዋሽ መድሃኒት ያላገኙላቸው በሽታዎች አሉ።
ወደኛ ስንመለስ ደብተራ (ሊቃውንት) አያቶቻችን የአእምሮ በሽታዎችን መፈወስ የጀመሩት ከአምስት ሺህ ዘመናት በፊት አንስቶ ነው። አያቶቻችን ይህን የአእምሮ በሽታዎችን የመፈወስ ጥበብ ያገኙት ከኖህ አባታቸው ነው። በመፅሐፈ ኩፋሌ ላይ እንደተፃፈው የኖህ ልጆች የአእምሮ በሽታ አጥቅቷቸው ነበር። ኖህም ልጆቹን የሚፈውስበትን ጥበብ በፀሎት ጠየቀ። እግዚአብሔርም መለሰ! መድሃኒት የሚቀምምበትን እና ለዚሁ ህክምና አገልግሎት የሚውሉትን እፅዋትና ማዕድናትን ገለፀለት። ኖህ ያገኘውን ጥበብ በመጠቀም ልጆቹን ፈወሰ። ጥበቡ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሻገር ዘንድ በመፅሐፍ ፅፎ አለፈ።
ይህን መፅሐፍ መሰረት አርገው ኢትዮጵያውያን ደብተራዎች መፅሐፍቱን በሁለት መልኩ ከፍለው ፃፏቸው።
1. የመጀመርያ እፀ ደብዳቤ ይሰኛል። 2. ሁለተኛው እንቁ አእባን ይሰኛል።
እፀ ደብዳቤ፦ የሰባት መቶዎቹን እፅዋት ዝርዝር ፣ አቀማመማቸው፣ ለምን በሽታ ፈውስ እንደሚሰጡና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን የያዘ ነው። እንቁ አእባን፦ እርሱ ደግሞ የማዕድናት ዝርዝሮችን የያዘ ሲሆን ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ ማእድናትን ዝርዝር መረጃ የያዘ ነው።
ደብተራ አያቶቻችን በዚህ አላቆሙም ከላይ የጠቀስኳቸውን መፅሐፍት መሰረት አርገው የራሳቸውን ጥናትም በማካተት የተለያዩ የአእምሮ በሽታ መፈወሻ ጥበብ የያዙ የህክምና መፅሐፍትን አዘጋጁ።
ከነኚህ መፅሐፍት መካከል ዋንኛዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦
፩ኛ. መፍትሔ ሥራይ ( በስሩ ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ መፅሐፍትን አካቷል) ፪ኛ. መፅሐፈ አፍልሆ ፫ኛ. መፅሐፈ ነድራ ፬ኛ. መፅሔተ ሠለሞን
፭ኛ.መርበብተ ሠለሞን
፮ኛ.መጽሓፈ ባርቶስ..ወዘተ ናቸው።
እነዚህ ሁሉ ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደተዘጋጁ አሁን ድረስ ያሉ ደብተራዎች ይናገራሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት እነኚህ የህክምና መፅሐፍት የማይፈውሱት የአእምሮ በሽታዎች የሉም። ዛሬ ድረስ ሳይንስ መድሃኒት ያላገኘላቸው የአእምሮ በሽታዎች በነኚህ መፅሐፍት ይፈወሳሉ።
ያሳዝናል … እውነታው ይህ ቢሆንም ግን ይህን በደብተራ አያቶቻችን ጥረት ከዚህ ዘመን የደረሰው ይህ አገራዊ ህክምና በአገራችን “ዘመናዊ” ሀኪሞች “ባህላዊ” ተብሎ የተናቀ በማህበረሰቡም ” ጥንቆላ” ተብሎ ገሸሽ የተደረገ በመንግሥት ትኩረት ያልተሰጠው ጥበብ ነው።
እውነታው ግን ከላይ የጠቀስኳቸው መፅሐፍት እንዳለ በጀርመን ፣ በእንግሊዝ እና ፈረንሳይ ውስጥ በሚገኙ የህክምና የትምህርት ተቋማት ውስጥ ጥናት ይደረግባቸዋል። ከዚህም አልፎ በፈረንሳይኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተተርጉመው በትላልቅ ጥራዞችም ታትመዋል። ለማስረጃም በእጄ ላይ የሚገኙ አሉ።
የዚህ ፅሁፍ መልእክት ሁለት ነው።
፩ኛ. ለበርካታ ሺህ ዘመናት አገራዊ የሆነውን ጥበብ ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሻገር ታላቅ መስዋእትነት ለከፈሉት ደብተራ አያቶቻችን እውቅና መስጠት ሲሆን …
፪ኛ. በአገራዊ እውቀት ዙሪያ መነቃቃትን መፍጠር ነው። አገራዊ የሆኑ እውቀቶችን ከዘመኑ ጋር አስታርቀን ብንገለገልባቸው ምክሬ ነው።
መርጌታ አምደብርሃን !