በአየር መንገድ ግቢ ውስጥ ከአመራሮች እውቅና ውጪ ተነሳ የተባለው ፎቶ በእውቅና መደረጉን የሚያሳይ ደብዳቤ ወጣ
(መሠረት ሚድያ)- ከቀናት በፊት ሲያነጋግር የነበረው የአየር መንገድ ግቢ ውስጥ የተነሳው ፎቶ እንደተባለው "ከተቋሙ አመራሮች እውቅና ውጪ" ሳይሆን በእውቅና መደረጉን የሚያሳይ ደብዳቤ ለመሠረት ሚድያ ደርሷል።
የአየር መንገዱ የአዲስ አበባ ሽያጭ ክፍል ዳይሬክተር አቶ ግሩም አበበ ለሲቪል አቪዬሽን ደህንነት ዋና መምሪያ ዳይሬክተር ታህሳስ 25/2017 ዓ/ም በፃፉት ደብዳቤ አርቲስት ምህረት ታደሰ በአየር መንገድ የአየር ክልል ውስጥ የፎቶ ፕሮግራም እንድታደርግ መጠየቋን ያሳያል።
ደብዳቤው አክሎም የፎቶ ፕሮግራሙ ለአየር መንገዱ ማስታወቂያነት ስለሚጠቅም ታህሳስ 27/2017 ዓ/ም ቅጥር ግቢ ውስጥ ገብተው ፎቶ እንዲነሱ ይጠይቃል።
የፎቶ ፕሮግራሙ በዚህ ሁኔታ በተቋሙ እውቅና ቢካሄድም ተቋሙ ከትናንት በስቲያ በፌስቡክ ገፁ "የግለሰቧ የአየር መንገድ ግቢ ውስጥ የልደት ምስል ቀረጻ ከተቋሙ አመራሮች እውቅና ውጭ የተደረገ ነው" ማለቱ ግርታን ፈጥሯል።
በተጨማሪም የፎቶ ፕሮርግራሙ የግል የልደት ፕሮግራም መሆኑን አርቲስቷ በሶሻል ሚድያ ገጿ ላይ የገለፀች ቢሆንም ይህ በምን መልኩ ለአየር መንገዱ በማስታወቂያነት እንደሚጠቅም ግልፅ አልሆነም።
ተቋሙ ለፎቶ ፕሮግራሙ ከአርቲስቷ ገንዘብ አለመቀበሉን እና ምንም አይነት ውል እንደሌለው በመግለጫው ላይ ገልፆ ነበር።
በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ድርጊቱን ከአየር የበረራ ክልል ደህንነት ጋር በማንሳት ጥያቄ ሲያቀርቡ ሌሎች ደግሞ በምን መስፈርት አንድ ግለሰብ የግል ልደት ከፍ ያለ ደህንነት በሚያስፈልገው አውሮፕላን ላይ ዲኮር በመስራት ተከበረ የሚል ጥያቄ አንስተዋል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ክስተቱ ለአየር መንገዱ ጥሩ ማስታወቂያነት ውሏል ብለው ሀሳብ የሰጡም አልጠፉም።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia