የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የስራ ሀላፊ የነበሩት ግለሰብ በኬንያ አየር መንገድ የካርጎ ማናጀር ሆነው ተቀጠሩ
- የኬንያ አየር መንገድ ልምድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን እያፈላለገ በከፍተኛ ደሞዝ እየቀጠረ ነው
(መሠረት ሚድያ)- የኬንያ አየር መንገድ (ኬንያ ኤርዌይስ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት (ካርጎ) እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የነበሩትን አቶ ፍፁም አባዲን መቅጠሩ ተሰማ።
ኬንያ ኤርዌይስ አቶ ፍፁምን የካርጎ ክፍል ዳይሬክተር አድርጎ ከትናንት የካቲት 24/2017 ዓ/ም ጀምሮ በሃላፊነት እንደሾማቸው የመሠረት ሚድያ ምንጮች ጠቁመዋል።
አቶ ፍፁም በኢቪዬሽን ኢንደስትሪ ውስጥ ከ23 አመት በላይ የዘለቀ የስራ ልምድ ያላቸው ሲሆን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በካርጎ አገልግሎት ዘርፍ በርካታ እውቀት እንዳላቸው ይነገርላቸዋል።
በተለይ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው በከፍኛ ደረጃ በተጎዳበት ወቅት እና የኢትዮጵያ አየር መንገድም የመንገደኞች በረራ በተቀዛቀዘበት ወቅት ማኔጅመንቱ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የካርጎ ክፍሉ ከፍተኛ እንስቃሴ በማድረግ አየር መንገዱን ከኪሳራ መታደጉ ይታወሳል።
በዚህ አስቸጋሪ ወቅት አቶ ፍፁም የስራ ባልደረቦቻቸውን በማስተባበር ቀን ከሌሊት በመስራት ብቃታቸውን እንዳስመሰከሩ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።
አቶ ፍፁም በትምህርት ዝግጅታቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን ከአሜሪካው ኒው ሃምፕሻየር ዩኒቨርስቲ እና ከእንግሊዙ ኦፕን ዩኒቨርስቲ ሁለት የማስተርስ ዲግሪ ወስደዋል።
አቶ ፍፁም የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከለቀቁ በኋላ ኑሮዋቸውን ከቤተሰባቸው ጋር በአሜሪካ አድርገው የነበረ ሲሆን በቅርብ ቀን ግን ወደ ኬንያ፣ ናይሮቢ እንደሚያቀኑ ታውቋል።
ግለሰቡ በትግራይ ጦርነት ወቅት በአንዳንድ አክቲቪስቶች ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶባቸው የነበረ ሲሆን ይህ ስም የማጠልሸት ዘመቻ በተመሳሳይ የደረሰባቸው የአየር መንገዱ የቀድሞ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንዲሁ በተመሳሳይ ስራቸውን በመቀየር ለግዙፉ ደልታ አየር መንገድ በአማካሪነት መስራት መጀመራቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተፎካካሪ የሆነው ኬንያ ኤርዌይስ ልምድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን እያፈላለገ በከፍተኛ ደሞዝ እየቀጠረ እንደሆነ ምንጮች ለመሠረት ሚዲያ ገልፀዋል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia