#ራስን_መግዛት (ክፍል - ፬)
የዕለተ ሰንበት የነፍሰ ስንቃችን እንደቀጠለ ነው
#ዶግማና_ትምህርት
መንፈሳዊው ሰው በዶግማና በትምህርት ላይ ራሱን ይገዛል፡፡ እርሱ አዘውትሮ ስለሚያነብ ወደ አእምሮው የገባውን ማንኛውንም ዓይነት አሳብ ለማስፋፋት አይጣደፍም:: ለምሳሌ፦ ቀስ ብሎ ሊያስተምረው ወይም አሳጥሮ ሊጽፈው ወይም ደግሞ መጽሐፍ አድርጎ ሊያሳትመው ይችላል፡፡ አንድ ሰው አንድን አሳብ ከመስጠቱም ሆነ ከመቀበሉ በፊት ወይም ጉዳዩን ለሌሎች ሕሊና ከማስተዋወቁ በፊት ለረዥም ጊዜ ሊያብላላውና ከገዛ ራሱ ሕሊና ጋር ሊወያይበት ይገባል፡፡
በልብህ ውስጥ ያለው አሳብ በአንተ ቁጥጥር ሥር ነው፡፡ ካወጣኸው ወይም ካስፋፋኸው ግን በሌሎች ሰዎች ቁጥጥር ሥር ነው:: ታላቁ አባት ቅዱስ መቃርስ «ወንድሜ ሆይ! ሰዎች በአንተ ላይ ከመፍረዳቸው በፊት በራስህ ላይ ፍረድ!›› ብሎ መናገሩ ምንኛ ትክክል ነው! ምናልባት ይህንን አባባሉን ያገኘው ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ ሊሆን ይችላል፡፡ «ራሳችንን ብንመረምር ባልተፈረደብንም ነበር . . » 1ኛ ቆሮ. 11፥31። ይህም ማለት መንፈሳዊው ሰው በሌሎች ቁጥጥር ሥር ከመውደቅ ይልቅ ራሱን መቆጣጠር ይመርጣል ማለት ነው፡፡
#ታዛዥነትና_ቃል_መግባት
ራሱ ቃል በመግባት፣ በታዛዥነትና በተሸናፊነት ውስጥ ራሱን ይገዛል፡፡ ምክንያቱም ዛሬ አንዳንድ ሰዎች በነፃነት፣በግል ክብርና በራስ መተማመን ስም ስለ ሥነ ሥርዓት፣ ስለ ወግና ስለ ሕግ ሳይጨነቁ የወደዱትን ስለሚያደርጉ ነው፡፡ በዲሞክራሲ ብናምንም የምናምነው በገደብ ውስጥ ባለ ዲሞክራሲ ነው:: ለዚህ አባባል ወንዝ ጥሩ ምሳሌ ሊሆነን ይችላል፡፡ ወንዝ ከግራና ከቀኙ ባሉት ሁለት ከፍ ያሉ የምድር አካላት ተገድቦ ይፈሳል፡፡ ሰዎች ወንዙን ከሚፈስበት አቅጣጫ በማስቆም ነጻነቱን ሊነፍጉት ባይችሉም አፍሳሹ ወጥቶ የጎርፍ አደጋ እንዳያስከትልና አካባቢውን ረግረግ እንዳያደርግ ግን ሊቆጣጠሩት ይችላሉ፡፡
መንፈሳዊው ሰው ቃሉን ይጠብቃል፤ ግብረገብነትን ያከብራል! ሕግጋትን ያጤናል፡፡ ሌሎች ሰዎችንም እንዲሁ ያከብራል፡፡ ሐዋርያው የተናገረውን ቃል ሳያንገራግር ይቀበላል:: «ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ግብር ለሚገባው ግብርን፣ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፣ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።» ሮሜ 13፥7: የራሱን ምኞትና አስተሳሰብ የሚከተለውና ለሥነ ሥርዓት፣ ለበላዩና ለማንም የማይገዛው ሰው ግን መንፈሳዊ ሰው አይደለም፡፡ እርሱ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ስለማይቀበል ምንም ዓይነት ነገር አይቀበልም።
ታዛዥነትን አስመልክቶ መንፈሳዊው ሰው ራሱን ይገዛል፡፡ እርሱ ለወላጆቹ፣ ለንሥሐ አባቱ፤ ለሥነ ሥርዓት ከመታዘዙም በላይ ለእግዚአብሔርም ፍጹም ታዛዥ ነው:: መታዘዝ ክብሩን እንደማይቀንሰው ይረዳል:: መታዘዝ የትሕትና ምልክት ሲሆን ትሕትና ደግሞ መልካም ባሕርይ ነው፡፡ ለማንም የማይታዘዝ ሰው ሙሉ ለሙሉ የሚታዘዘው ለትዕቢቱና ለአሳቡ መሆኑ እርግጥ ነው፡፡
ይቀጥላል......
አዘጋጅ :-በለጠ ከበደ (የጣፈጡ ልጅ)✍ አላቲኖስ
(#በብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#መንፈሳዊ_ሰው_መጽሐፍ ገጽ 122-128
#በአያሌው_ዘኢየሱስ_የተተረጎመ)
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
(#ብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ)
╔✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_ዕለተ_ሰንበት ❀
╚✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ
የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏
በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot