Репост из: ወድሰኒ
የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፫፥፲፫
ስለ ጌታችን ኢየሱስ ጥምቀት
ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ዮሐንስ ግን "እኔ ከአንተ ልጠመቅ እሻለሁ፤ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህን?" ብሎ አይሆንም አለው። ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ "አሁንስ ተው፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናልና" አለው። ከዚህም በኋላ ተወው።
ጌታችን ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ፥ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆ፥ ሰማይም ተከፈተለት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ አየ፤ እነሆ፥ "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ለመስዋዕትነት የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው" የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።
ሰማይና ምድር ያልፋል ቃሌ ግን አያልፍም አለ ጌታ ለደቀመዛሙርቱ
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ።