ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6

" አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን
አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም
ለእግዚአብሔር እልል በሉ።"
(መዝሙረ ዳዊት 47:1)

ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


መልካም ዜና ለአእላፍት ዝማሬ ቤተሰቦች ❤️‍🔥

የአእላፍት ዝማሬ መዝሙሮችን በነፃ የምታገኙበት አዲስ ቻናል ተገኝቷል፣ በቀላሉ ቻናሉን ለማግኘት 👇


ኦርቶዶክስ ኖት 🥰👇




የትኛው ስራዬ

የትኛው ስራዬ ነው የትኛው ህይወቴ❨፪×❩
ሞገስ ሆኖኝ እንጂ እግዚአብሔር አባቴ❨፪×❩

ልጅዋን ትረሳ ዘንድ እናት እንኳን ብትስት
አንተ ግን ወደድከኝ ላትረሳኝ በሞት
በመዳፍህ ቀርፀህ ሁሌ ታየኛለህ
መድሀኒቴ ኢየሱስ በደሌን እረስተህ

ቢምረኝ ነው ቢምረኝ በመቅደሱ ያቆመኝ
ቢያስበኝ ነው ቢያስበኝ በከፍታው ያኖረኝ
        /አዝ = = = = =
የአብርሀምን ምግባር የዮሴፍን እምነት
ፅድቅን ባልኳለው ባላደርግ መቀነት
ማህተቡን ይዣለሁ የደሙን ጠብታ
መድሀኒቴ ኢየሱስ አክብሮኛል ጌታ

ቢምረኝ ነው ቢምረኝ በመቅደሱ ያቆመኝ
ቢያስበኝ ነው ቢያስበኝ በከፍታው ያኖረኝ
        /አዝ = = = = =
እንዳልፈው የረዳኝ የእሳቱን ባህር
ምን ምግባር ኖሮኝ ነው ከፅድቅ የሚቆጠር
የልቤ ኩራት ነው የአይኔ ከፍታ
መድሀኒቴ ኢየሱስ የሠራዊት ጌታ

ቢምረኝ ነው ቢምረኝ በመቅደሱ ያቆመኝ
ቢያስበኝ ነው ቢያስበኝ በከፍታው ያኖረኝ
/አዝ = = = = =
ዘይቱ እንዴት ፈላ በራሴ ያፈሰስከው
ዙፋን ልታወርሰኝ ልቤን የመረጥከው
የኔ የተወደደው ከኤልያም ደም ግባት
መድሀኒቴ ኢየሱስ ሆነኸኝ ነው ውበት
ቢምረኝ ነው ቢምረኝ በመቅደሱ ያቆመኝ
ቢያስበኝ ነው ቢያስበኝ በከፍታው ያኖረኝ❨፪×❩

👉ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

 ╔✞════●◉❖◉●════✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
@enamsgn @enamsgn
@enamsgn @enamsgn
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞════●◉❖◉●════​✞╝
✍ ወድሰኒ


Репост из: ወድሰኒ ​​
የካቲት ፲፯ /17/

በዚች ቀን ከላይኛው ግብጽ ከአክሚም መንደር መነኰስ ሚናስ በሰማዕትነት አረፈ።

ይህም ቅዱስ በአንድ ገዳም ውስጥ እያገለገለና እየተጋደለ ከገዳሙ ደጃፍ ሳይወጣ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ።

እስላሞችም በግብጽ አገር በነገሡ ጊዜ ለእግዚአብሔር ከርሱ ጋር ለዘላለሙ ህልው የሆነ ከባሕርዩ የተወለደ ልጅ የሚሠርፅ መንፈስ ቅዱስም የለውም እንደሚሉ ሰማ ስለዚህም ነገር እጅግ አዘነ።

ከአበ ምኔቱም ቡራኬ ተቀበለ ወደ እስሙናይን ከተማ ወጥቶ ሔደ የእስላሞች ሠራዊት አለቃ በሆነ በመኰንኑ ፊት ቁሞ እንዲህ አለው። እናንተ ለእግዚአብሔር ከባሕርዩ የተወለደ ልጅ እንደሌለው አድርጋችሁ የምትናገሩ እውነት ነውን መኰንኑም አዎን ልጅ አለው ማለትን ከእግዚአብሔር እናርቃለን አለ።

አባ ሚናስም ያለ ልጅ ልታምኑ አይገባም እርሱም ያለ ዘር ያለ ሩካቤ የሆነ ነው ከባሕርዩ ተወለደ እንጂ አለው። መኰንኑም ልጅ አለው ማለት በሕጋችን ክህደት ነው አለ አባ ሚናስም እንዲህ አለው መኰንን ሆይ እወቅ የከበረ ወንጌል በወልድ ያመነ የዘላለም ሕይወት አለው በእግዚአብሔር ልጅ በወልድ ያላመነ ሕይወትን አያይም የእግዚአብሔርቁጣ በላዩ ይወርዳል እንጂ ብሏልና።

ስለዚህም መኰንኑ እጅግ ተቆጣ ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጡ ሥጋውንም በየቊርጥራጭ ቆራርጠው በባሕር እንዲጥሉት አዘዘ ምእመናንም ሥጋውን ወስደው በበጎ አገናነዝ ገንዘው ቀበሩት መታሰቢያውንም አደረጉ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር


ስለ ወደደኝ አዳነኝ

ስለ ወደደኝ አዳነኝ
በቸርነቱ ፈወሰኝ
አቆመኝ ስለ ክብሩ
ከሞት ነጥቆኛል ፍቅሩ

ዘርግቶልኛል እጁን ለህማም
አፍቅሮኛል እስከ ዘለዓለም
ስታወክም ነው ጸጥታዬ
የወደደኝ ቸሩ ጌታዬ
     /አዝ = = = = =
በሞት ጫንቃ ላይ ተረማመድኩኝ
ሰንሰለቴ ተፈቶ ዳንኩኝ
በዝማሬ አፌ ሰልጥኖ
አርፏል ልቤ በእርሱ ተማምኖ
/አዝ = = = = =
ወርዶ ሣምራዊው ከአህያው ላይ
ዘይትን ቀባኝ በቁስሎቼ ላይ
ደግፎኛል በንጹህ ፍቅር
ከፍሎልኛል ሁለቱን ዲናር

👉ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃድቅ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

 ╔✞════●◉❖◉●════✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
@enamsgn @enamsgn
@enamsgn @enamsgn
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞════●◉❖◉●════​✞╝
✍ ወድሰኒ


የካቲት ፮ /6/


በዚችም ቀን ጌታን ሽቱ ለቀባችው ማርያም የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው ። ይችም ቅድስት አስቀድማ ኑሮዋን በዝሙት ያሳለፈች ኃጢአተኛ ነበረች ። እርሷም ጐልማሶችን ወደርሷ ትማርካቸው ዘንድ በየራሱ በሆነ ሽልማትና ጌጥ ትሸለም ነበር።

በአንዲትም ዕለት እንደ ልማድዋ ተሸልማ አጊጣ ሽቱም ተቀብታ ፊቷን በመስታዋት ተመለከተች የጉንጯ ቅላትና ደም ግባቷ የዓይኗም ወገግታና ጥራት ማማሩን አይታ እያደነቀች አንድ ሰዓት ያህል ቆየች ከዚህም በኋላ በጎ ኀሳብ በላይዋ መጣ ሞትንና የዚህን ዓለም ማለፍ አሰበች።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስም ኃጢአተኞችን እንደሚቀበልና ኃጢኣትንም እንደሚአስተሰርይ ሰምታ ገንዘቧን ወስዳ የአልባስጥሮስን ሽቱ ገዝታ በስምዖን ዘለምጽ ቤት ለምሳ ተቀምጦ ሳለ ወደ ጌታችን ሔደች።

ከእግሩ በታችም ሰግዳ ያንን ሽቱ ቀባችው እግሮቹን በዕንባዋ አጠበችውና በራስዋ ጠጉር ወለወለችው ጌታችንም የፍቅርዋን ጽናት አይቶ ኃጢኣቷን በደሏን ተወላት የመንግሥት ወንጌልም በሚሰበክበት ይህን ያደረገችውን እንዲአስቡ አዘዘ ። በረከቷም ከእኛ ጋርይኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር


የፃድቅ ሰው ፀሎት

የፃድቅ ሰው ፀሎት ሀይልን ያደርጋል
ፀሐይን ያቆማል ሙታን ያስነሳል
ከጠላት ዲያቢሎስ ነፍሳትን ይነጥቃል
ባዶውን ማድጋ በዘይት ይሞላል

የኢያሱ ፀሎት ግዳጅን ፈፅሟል
በገባኦት ሰማይ ፀሐይን አቁሟል
ማድጋዋ ሞልቷል በኤልሳ በረከት
ከርሀብ ድናለች ሱናማዊቷ ሴት
         /አዝ = = = = =
ህያው እንድትሆን ጴጥሮስ ፀለየላት
ጣቢታ ተነሳች ሞት ተሸንፎላት
ከሰገነት ወድቆ ቢሞት አውጣኪስ
ህይወት ሰጠው አቅፎ ቅዱስ ጳውሎስ
         /አዝ = = = = =
በስሙ መከራን ለተቀበሉት
ይለምናል ጌታ ስለሰማዕታት
በፃድቅ ስም ውሃ ለመስጠት የተጋ
ያገኛል ከእግዚአብሔር የፃድቁን ዋጋ
   /አዝ = = = = =
ቃልኪዳን ስላለው ከመረጣቸው
ስለማለላቸው በፅኑ መሐላው
ጌታ ስለነርሱ እንደሚማለደን
በመንፈስ ቅዱስ አፍ መፅሐፍ ነገረን

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

 ╔✞════●◉❖◉●════✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
@enamsgn @enamsgn
@enamsgn @enamsgn
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞════●◉❖◉●════​✞╝
✍ ወድሰኒ


Репост из: ወድሰኒ ​​
ልታስበው የሚገባ በመሆኑ ከጾመ ነቢያት ጋር አያይዘን እንድንጾም ሐዋርያት ሰብአ ነነዌ የተነሳሕያን አብነት ናቸውና ሥርዓቱም ጾሙም አይቅር ብለው ቀኖና ሠርተውልናል፡፡ እኛም በጾምና በጸሎት ከፈጣሪያችን ምሕረትና በረከት ለማግኘት ስንል እንጾመዋለን፡፡
በተጨማሪም ይህ ጾም ለዐቢይ ጾም መዘጋጃ በመሆን ያገለግላል፡፡
የነነዌን ሕዝብ በእሳት ከመቃጠል ያዳናቸው አምላክ እኛንም ከገሃነም እሳት ያድነን፡፡ አሜን!  
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ስንክሳር ዘታኅሣሥ 6 ፣ ሰባቱ አጽዋማት ፣ ጾምና ምጽዋት


Репост из: ወድሰኒ ​​
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
          🕯 #ጾመ_ሰብአ_ነነዌ
   ይህ ጾም የነነዌ ሰዎች የጾሙት ሦስቱ ዕለታት ማለትም ሰኞ፣ ማክሰኞና ረቡዕ በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የሚጾም ጾም ነው፡፡ በመባቻ ሐመር የጾሙ ወቅት ከፍና ዝቅ ይላል፤ ማለትም አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል፡፡
   የነነዌ ከተማ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የተመሠረተችና ከጥንት ጀምሮ ጣዖት ይመለክባት የነበረች ጥንታዊት የአሶራውያን ዋና ከተማቸው ነች፡፡ በተጨማሪም በከተማዋ ጣዖት የሚያመልኩና እግዚአብሔርን የሚዘባበቱ ሕዝብና ነገሥታት ነበሩባት፡፡ (ለምሳሌ የንጉሥ ሰናክሬምና የእስራኤል ንጉሥ ሕዝቅያስን ታሪክ 2ኛ ነገ ምዕ 19 ያንብቡ)፡፡
   ይህች ከተማ በዚህ ሁኔታ ቀጥላ በ770 ቅ/ል/ክ የሕዝቡ ኃጢአት ከፈጣሪ ሲደርስ እግዚአብሔር ‹‹ነነዌ በዚህ ሦስት ቀን ትገለበጣለች ብለህ ንገራቸው›› ብሎ ነቢዩ ዮናስን ላከው፡፡ ዮናስ ግን የዋህ ስለነበረ ‹‹አንተ መሐሪ አምላክ ነህና እኔ እናገራለሁ አንተም ትምራቸዋለህ በመጨረሻም እኔ ውሸተኛ እባላለሁና ስለዚህ ወደ ነነዌ ሔጄ አልሰብክም›› በማለት ወደ ተርሴስ ለመሔድ በመርከብ ተሳፈረ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በአውሎና በወጀብ መካከል መንገድ ያለው ፍጥረታቱም ሁሉ የሚታዘዙለት አምላክ መሆኑ ይታወቅ ዘንድ በባሕሩ ላይ ወጀብ አስነሳ፡፡ ዮናስ የተሳፈረበት መርከብም ታወከች፤ በመርከቢቱ የተሳፈሩ ሌሎች ተሳፋሪዎችም ‹‹ከእኛ መካከል በደለኛ ማን ነው?›› ሲባባሉ ዮናስ ግን በመርከቡ አንደኛው ክፍል ገብቶ ተኝቶ ነበር፡፡ እነርሱም ቀስቅሰው ማንነቱን ሲጠይቁት ‹‹እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን የማመልክ ሰው ነኝ፤ በእርሱ ላይ በማመጼ ይህ ሁሉ መከራ በእኔ ምክንያት አግኝቷችኋል፤ ስለዚህ እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› አላቸው፡፡ መርከበኞቹም እውነቱን ለማረጋገጥ እጣ ቢጣጣሉ በተከታታይ ሦስት ጊዜ በዮናስ ላይ ስለወጣ ዮናስን ከመርከባቸው አውጥተው በባሕር ላይ ጣሉት፡፡ ፍጥረታቱ ሁሉ ለእግዚአብሔር ይታዘዙለታልና ትልቅ ዓሣ ዮናስን ውጦ በባሕር ላይ እየተጓዘ በሦስተኛ ቀኑ በባሕር ወደብ ላይ በነበረች በነነዌ ከተማ ተፋው፡፡ ዮናስም ከዓሣው ሆድ ከወጣ በኋላ ስለከተማዋ በጠየቀ ጊዜ ነነዌ መሆኗን ነገሩት፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር በል እንዳለው ‹‹ይህች ከተማ በሦስት ቀን ትገለበጣለች›› ብሎ ሰበከ፤ (ሙሉ ታሪኩን ትንንቢተ ዮናስ አራቱንም ምዕራፎች ያንብቡ)፡፡
   የነነዌ ሰዎች አስቀድሞ በሰናክሬምና በወታደሮቹ ላይ የደረሰውን ጥፋት እና ‹‹ኃይሌ ጉልበቴ አንተ ነህ›› ያለውን ሕዝቅያስን ከነሕዝቡ የመዳኑን ታሪክ ሰምተዋልና እግዚአብሔር ይቅርባይ መሐሪ መሆኑን አምነው ወደ እርሱ ተጠግተው ከአዋቂ እስከ ልጅ ከንጉሥ እስከ አገልጋይ ተስማምተው ጾምን አወጁ፤ በአንድ ልብ በአንድ መንፈስ ሆነውም አለቀሱ፡፡ እግዚአብሔርም መመለሳቸውን ተመልክቶ ይቅር አላቸው፡፡ ዮናስ ግን መደሰት ሲገባው በየዋህነቱ አዘነ፤ ቀድሞውኑ እኔ የተናገርኩት ሳይሆን ቢቀር ውሸተኛ እባላለሁ ብሎ ነበርና፤ (ዮና 4፥1)፡፡
   ይህን ጾም የምንጾምበት ዐቢይ ምክንያት አብርሃም ሶርያዊ ሊቀ ጳጳስ የሠራው ሥርዓት በመሆኑ ነው፡፡ አብርሃም ሶርያዊ ከክርስቲያን ወገን የተወለደና አስቀድሞ ገንዘብ ያለው ነጋዴ ነበር፡፡ እየነገደም ምስር (ግብፅ) አገር ደርሶ በዚያው መኖር ጀመረ፡፡ ለድኆችና ለችግረኞች ርኅራኄን የሚያደርግ በመሆኑና በዚህም ብዙ ትሩፋቶቹ በመገለጣቸው የእስክንድርያ ኤጲስ-ቆጶሳት በፈቃደ እግዚአብሔር በእስክንድርያ ሊቀ-ጵጵስና ሾሙት፡፡ ከዚህ በኋላ ገንዘቡን ለድኆችና ለችግረኞች መጽውቶ የሊቀ-ጵጵስናውን ሥራ መሥራት ጀመረ፡፡ በሹመቱም ወራት ክፉ ልማድን ሁሉ አስወገደ፤ ኤጲስ-ቆጶሳቱንም ስለ ክህነት ሹመት መማለጃ እንዳይቀበሉ አወገዛቸው፤ ውግዘቱንም በሰሙ ጊዜ ሁሉም ፈርተው ክፉ ልማዳቸውን በመተው በደላቸውን ያስተሰርይላቸው ዘንድ ለመኑት፡፡
   እግዚአብሔርን ከማይፈራ አንድ የንጉሥ ጸሐፊ ከሆነ ሰው በስተቀር ሁሉም ግዝቱን አክብረውታል፡፡ አብርሃም ግን ያን ክፉ ሰው ስለ ራሱ ድኅነት ብዙ ጊዜ ቢለምነውም ከክፋቱ አልተመለሰም፡፡ ጻድቁ አብርሃም ማስተማሩንና መገሠጹን ሳይሰለች ለሌሎች ዕንቅፋት እንዳይሆን ወደዚያ ክፉ ሰው ቤት ሄደ፤ ሆኖም ግን ይህ ክፉ ሰው የሊቀ-ጳጳሱን መምጣት በሰማ ጊዜ ደጁን ቢዘጋበትም አብርሃም ደጁን እያንኳኳ ለተወሰነ ሰዓት ቆመ፡፡ ከዚህም በኋላ ‹‹የዚህ ሰው ደም በራሱ ላይ ነው፤ እኔ ከደሙ ንጹሕ ነኝ›› ብሎ የእግሩን ትቢያ አራግፎ ተመለሰ፡፡ ያም ክፉ ሰው በክፉ አሟሟት ሞተ፡፡ ይህን የተመለከቱ ብዙዎችም ንስሐ ገብተዋል፤ (ስንክሳር ዘታኅሣሥ 6)፡፡
   ከዚህም በተጨማሪ በአብርሃም ሶርያዊ የሊቀ-ጵጵስና ዘመን ለምስር (ግብፅ) ንጉሥ የጭፍራ አለቃ የሆነ አንድ አይሁዳዊ ሰው ነበር፡፡ ለዚህም የጭፍራ አለቃ አብሮት ወደ ንጉሥ የሚገባ ሌላ አይሁዳዊ ወዳጅ ነበረው፡፡ ይህ አይሁዳዊ ከጭፍራ አለቃው ጋር ወዳጅ በመሆኑ ከንጉሥ ጋር ይነጋገራል፤ ከንጉሥ ዘንድ ባለሟልነትን ባገኘ ጊዜም ንጉሡን ‹‹ጌታዬ ንጉሥ ሆይ ሊቀ-ጳጳሳት አባ አብርሃምን እንድታስመጣውና በፊትህ እንድከራከረው ተመኝቻለሁ›› አለው፡፡ ንጉሡም ልኮ አባ አብርሃምን አስመጣው፤ ከርሱም ጋር የእስሙናይን ኤጲስ-ቆጶስ አባ ሳዊሮስ ነበረ፡፡ ይህ አይሁዳዊም ከሊቀ-ጳጳሳቱ ጋር ተከራክሮ በመረታቱ ንጉሡ ሊቀ-ጳጳሳቱን አክብሮ በሰላም ወደ ቤታቸው አሰናበታቸው፡፡ የጭፍራ አለቃውና አይሁዳዊ ወዳጁም አፈሩ፡፡ ሆኖም ግን ሊቀ-ጳጳሳቱንና የክርስቲያን ወገኖችን የሚያሸንፉበት ሌላ ነገር መሥራት ጀመሩ፡፡ በአንዲትም ቀን የጭፍራ አለቃው ወደ ንጉሡ ገብቶ ‹‹ጌታዬ ንጉሥ ሆይ የማስረዳህ ነገር አለ፤ እነዚህ ክርስቲያኖች ሃይማኖት የላቸውም፤ ወንጌላቸው፡- የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል ሃይማኖት ካላችሁ ይህን ተራራ ከዚህ ተነቅለህ ወደዚያ ሂድ ብትሉት ይሄዳል የሚሳናችሁ የለም›› ይላልና አለው፡፡ ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ መጠየቅ ሽቶ ሊቀ ጳጳሱን ሲያገኘው ነገሩን ያጣዋል፤ ነገሩ ትዝ ሲለው ሊቀ ጳጳሱን ያጣዋል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ግን እርሱ ባለበት ነገሩ ትዝ ይለውና ‹‹አባቴ የምጠይቅህ ኑሮኝ አንተን ሳገኝህ ነገሩን እየዘነጋሁት ነገሩ ትዝ ሲለኝ አንተን እያጣሁህ ቆየሁ፤ አሁን ግን ነገሩም ትዝ ብሎኛል አንተም መጥተሃል›› አለው፡፡  ከዚያም በወንጌል ‹‹የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም›› (ማቴ 17፥20 ፣ ማቴ 21፥21 ፣ ሉቃ 17፥6) ተብሎ ተጽፏል፤ ወንጌል  እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለህ የምታምን ከሆንህ ይህን ፈጽመህ አሳየን አሉት፡፡ አብርሃም ሶርያዊም ሦስት ቀን እንዲሰጡት ጠይቆ ሦስቱን ቀን በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ተማጸነ፤ ከዚያም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጣለት ጫማ ሰፊ ተብሎ የሚታወቀው ስምዖን ግብጻዊ ጋር እንዲሄድና ከእርሱ ጋር ሆነው አይሁድ ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኙ ነገረችው፡፡ በመጨረሻም በሊቀ ጳጳሱ አስተባባሪነት፣ በስምዖን መሪነት፣ በምእመናን ጸሎትና በእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ 41 ኪራላይሶን አድርሰው ሰግደው ሲነሡ ተራራው ተነሣ፤ በውስጡም ተያዩ፡፡ ተራራውንም አፍልሰው በኢ-አማንያን ፊት ድንቅ ተአምር አሳይተዋል፡፡ ይህ ተአምር የተደረገበት ወቅት ደግሞ ጾመ ነቢያት ከመግባቱ በፊት ስለነበር የተደረገውም ተአምር ቤተ ክርስቲያን ዘወትር


ድንግል እናቴ

ድንግል እናቴ ነይ ድረሽልኝ
ወገን የለኝም ቀርቦ የሚያፅናናኝ
ካጠገቤ ሁኚ እና አለሁ በይኚ

ይቆይልኛል ያልኩት ከእጄ ላይ አልቆ
በሀዘን በሰቆቃ ጉልበቴ ደቆ
በረከት አልባ ሆኜ እንዳልከፋ
ድረሽልኝ እናቴ ነይ የእኔ ተስፋ
      /አዝ = = = = =
ብቸኝነት ክፉ ነው አንገት ያስደፋል
ጭንቀትን አባብሶ ለክፉ ይሰጣል
አንቺ ከጎኔ ካለሽ አልሸነፍም
ለዚህ ዓለም ሞኝነት እጄን አልሰጥም
      /አዝ = = = = =
እንኳን ለደካማው ሰው ለእኔ ለባሪያሽ
ለዓለም ይተርፋል ፀሎት ልመናሽ
በዚያ በፍርድ ሰዓት ጥላ ሁኚኝ
ክፉ ግብሬን መዝኖ እንዳያቀለኝ
   /አዝ = = = = =
እረፍዶብኛል ጉዞው የሠርጉ ቤት
ሙሽራው ሊገባ ነው ሳልይዝ መብራት
አፍጥኚኝ እናት ዓለም ለመልካም ሥራ
የእሳት ሲሳይ እንዳልሆን ድንግል አደራ

👉ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

 ╔✞════●◉❖◉●════✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
@enamsgn @enamsgn
@enamsgn @enamsgn
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞════●◉❖◉●════​✞╝
✍ ወድሰኒ


#አቡነ ተክለ ሃይማኖት

#ጥር 24 የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሐይማኖት ስባረ አጽማቸው ነው፤ በረከታቸው ይደርብን፡፡

የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል፡፡ መዝ 34፣19

አባታችን ኢትዮጵያዊው ፃድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለ22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አሰቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል። ለዓመታት ከቆሙበት ሳይቀመጡ ከፊት ከኋላ ከጐን እና ከጐን ምንም ሳይደገፉ በአንድ ቦታ በመወሰን ለ22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አስቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል። ከዚያም ለ7 ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ፀሎታቸውን ቀጠሉ። ስለ ክብራቸውም ከእግዚአብሔር ክንፍ ተሰጥቷቸዋል። በአጠቃላይ ለ29 ዓመታት በጸሎት ቆይተዋል።

ዕረፍታቸውም በተወለዱ በ99 ዓመት ሲሆን ቀኑም ነሐሴ 24 ቀን ነው።
በዚህም መሠረት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ለዕረፍታቸው በእግዚአብሔር ፊት ለከበረና ብዙ ክብር ለተሰጣቸው አባታችን በየዓመቱ ነሐሴ 24 ቀን በዓለ ዕረፍታቸውን ታህሳስ 24 ቀን በዓለ ልደታቸውን ዛሬ ጥር 24 ደግሞ ስባረ አፅማቸውን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች።የአባታችን የፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጸሎታቸው እና አማላጅነታቸው ቤተክርስቲያናችንን አገራችንን ኢትዮጵያን እና እኛን ህዝቦቿን ከፈተና ይጠብቀን ዘንድ በቃልኪዳናቸው ያስቧት አሜን!!!

የሀዲስ ሐዋርያ ጸሎታቸው፣ቃል ኪዳናቸው፣በረከታቸው፣አማላጅነታቸው አይለየን አሜን፡፡


አንተን ማገልገል

አንተን ማገልገል መባረክ ነው❨፪×❩
ምርጫ ነው ዕጣ ነው
ክብር ነው እድል ነው
አንተን ማገልገል መባረክ ነው

ገና በማለዳ ብላቴና ሳለሁ
የሰማሁት ዜማ ዛሬም በልቤ ነው
የጸናጽሉ ድምጽ የሸተተኝ ዕጣን
ካንተ ጋር አስሮኛል በዝማሬ ኪዳን
       /አዝ = = = = =
አፈር ትቢያ ስሆን ከሁሉ ያነስኩኝ
እንዳገለግልህ በአንተ ተመረጥኩኝ
የአንተ ስምና ክብር በአፌ ላይ አለፈ
በባሪያህ ተጠቅመህ ስንት ሰው አረፈ
       /አዝ = = = = =
ዓለም ሳትወስድብኝ ያንተን ውድ ጸጋ
ለክብርህ እንደዘመርኩ እየመሸ ነጋ
የዜማ ጠጠሬ ያለህ በወንጭፌ
ሺ ጠላት ቢከበኝ ምስጋና ነው ሰልፌ
       /አዝ = = = = =
ተከፍቼ አላውቅም እኔ በአንዳች ነገር
ስምህን አንግቤ ስሄድ አገር ለሀገር
ሰላደረክልኝ ባዕዳነነ ዘመድ
ሞገስ ክብር ሆንከኝ ባለፍኩበት መንገድ
/አዝ = = = = =
ዘመኔ የደስታ የሐሴት ሆነልኝ
ስትረዳኝ ስላየሁ አቤኔዘር አልኩኝ
ስለ እጅህ ስጦታ አሜን ብዬሃለሁ
የስምህ አወዳሽ የልጅ ልጅ አያለሁ

👉ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖
@mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ


✞ ሞትማ_ለመዋቲ_ይገባል ✞

ሞትማ ለመዋቲ ይገባል ይገባል(፪)
የድንግል አሟሟት እጅጉን ይደንቃል(፪)

ለልጇ ስትነግር ሞት እንደምትፈራ(፪)
ወሰዷት በሐሴት መላእክተ ሐራ(፪)
ጭንቀቱ ሳይገጥማት ሳታስብ ድንገት(፪)
እንደ እንቅልፍ ወሰዳት ያመልአከ ሞት፪)

         /አዝ = = = = =

ይገርማል ይደንቃል የድንግል ፍልሰታ(፪)
በምስጋና አረገች ከልጇ ተጠርታ
በይባቤ አረገች ከልጇ ተጠርታ
እያሸበሸቡ መላእክተ ሰማይ(፪)
ወስደው አቀረቧት ከልጇ መንበር ላይ(፪)

/አዝ = = = = =

ሱባኤ እንደገቡ እንደ ሐዋርያት(፪)
እኔም ከቤት ወጣሁ አንቺኑ በመሻት(፪)
ትንሳኤሽን በክብር እንዳሳየሻቸው(፪)
እኔንም ለዚህ አብቂኝ ብርሃንሽን እንዳየው(፪)

👉ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

  ╔✞═════●◉❖◉●════✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
@enamsgn @enamsgn
@enamsgn @enamsgn
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞═════●◉❖◉●════​✞╝
✍ ወድሰኒ


Репост из: ወድሰኒ ​​
🕊 አረበረበ 🕊

የወይን የወይን ሀረግ❨፫×❩
ሙሽሮች ባለማይረግ❨፪×❩
ሚዜዋች ባለማይረግ❨፪×❩
አጃቢው ባለማይረግ❨፪×❩

የወይን የወይን❨፬×❩    የወይን ሀረግ❨፬×❩
ዓረ ንዓ ንዓ❨፪×❩ '' '' ''
ንዓ በሰላም❨፪×❩        ''     ''     ''
ሙሽሮቹን ባርክ         ''     ''     ''
መድሀኒዓለም          ''     ''     ''
የወይን ሀረግ❨፬×❩

የወይን የወይን❨፬×❩     የወይን ሀረግ❨፬×❩
ዓረ ንዒ ንዒ❨፪×❩         ''     ''     ''
ንዒ በሰላም❨፪×❩        ''     ''     ''
የሙሽሮች እናት         ''     ''     ''
ድንግል ማርያም        ''     ''     ''
የወይን ሀረግ❨፬×❩

ሀመልማል❨፪×❩ ሀመልማለ ወርቅ
ልብሱ ሙሽራው ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ሀመልማል❨፪×❩ ሀመልማለ ወርቅ
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ሀመልማል❨፪×❩ ሀመልማለ ወርቅ
ልብሱ ሙሽራው ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ

አብ እሳት ወልድ እሳት መንፈስ ቅዱስ እሳት
ልብሱ ሙሽራው ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
እባክህ ጌታዬ እቺን ቀን ቀድሳት
ልብሱ ሙሽራው ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ     
እንዴት ካህን ይሙት ካህን ይቀበር 
ልብሱ ሙሽራው ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
መፀፀኛው የወርቅ መቋሚያው የብር
ልብሱ ሙሽራው ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ያቺን ይይዝና ቀለም ሲናገር
ልብሱ ሙሽራው ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ይመስላል መላዕኩን በክንፍ የሚበር
ልብሱ ሙሽራው ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
     ሀመልማለ ወርቅ❨፬×❩

አረበረበ ሊቁ ወረበ❨፪×❩
አረበረበ አሸበሸበ ወገዳሙኒ ሊቁ ወረበ❨፪×❩
መራዊ ነገደ ሊዊ❨፪×❩
መራት ነገዳችን ናት❨፪×❩

ሀመልማል❨፪×❩ ሀመልማለ ወርቅ
ልብሱ .... ....

እስኪ በስመአብ ብዬ ልጀምር ፀሎቴን   
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ውዳሴ ውግና የአስርቱ ቃላት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ቀዲው ወገብዋ ንፅህት መቀነት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ገብርኤል በቃሉ እያጫወታት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
እስዋ ዘኾንኪ ናት ፅርሀ ቅድሳት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
አስተምሀ ሰላናኪት ተቋመ ማህቶት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
አንቲ እግዚ አ ኩሉ የሁሉ እመቤት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
በትረ አሮን እጅዋን የምትፈትልበት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ለኪ ይደልዎ እያሉ ገቡ ሊቃውንት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ

አረበረበ ሊቁ ወረበ❨፪×❩
አረበረበ አሸበሸበ ወገዳሙኒ ሊቁ ወረበ❨፪×❩
መራዊ ነገደ ሊዊ❨፪×❩
መራት ነገዳችን ናት❨፪×❩

ሀመልማል❨፪×❩ ሀመልማለ ወርቅ
ልብሱ .... ....

ካህኑም ይላሉ እኛ እንቀድሳት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ንጉሱም ይላሉ እኛ እናንግሳት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ስትወለድ በአልጋ መሬት ሳይነካት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ውሀ ከጭንጫ ላይ የፈለቀላት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
እሳት ከባህር ላይ የነደደላት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ትዳር መንፈሳዊ ይኸው ተሰጣት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
አበ ነፍስ አባትዋ ተክለሀይማኖት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ክርስትና እናትዋ ኪዳነ ምህረት
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
           ሀመልማለ ወርቅ❨፬×❩

አረበረበ ሊቁ ወረበ❨፪×❩
አረበረበ አሸበሸበ ወገዳሙኒ ሊቁ ወረበ❨፪×❩
መራዊ ነገደ ሊዊ❨፪×❩
መራት ነገዳችን ናት❨፪×❩

ሀመልማል❨፪×❩ ሀመልማለ ወርቅ
ልብሱ .... ....

ሀመልማሉን ፈትላ ባገልግል በቅታለች
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ሸማኔ ተወዶ ማርያም ትሰራለች
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
አረ ማርያም ማርያም ደና አርገሽ ስሪው
ልብሱ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
ከቆላ በደጋ ተሰምቷል ዜናው
ልብሷ ሙሽሪት ወርቅ ሀመልማለ ወርቅ
              ሀመልማለ ወርቅ❨፬×❩

አረበረበ ሊቁ ወረበ❨፪×❩
አረበረበ አሸበሸበ ወገዳሙኒ ሊቁ ወረበ❨፪×❩
መራዊ ነገደ ሊዊ❨፪×❩
መራት ነገዳችን ናት❨፪×❩
                                           
👉ዘማሪ ዲ/ን አካል በለጠ


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔✞════●◉❖◉●════✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
@enamsgn @enamsgn
@enamsgn @enamsgn
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞════●◉❖◉●════​✞╝
✍ ወድሰኒ


📌አዲስ የሰርግ መዝሙር
🖋በዲያቆን አካል በለጠ
አረበረበ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
@enamsgn @enamsgn
✍ ወድሰኒ


Репост из: ወድሰኒ ​​
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
           🕯 #ሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስ
   ቂርቆስ ማለት ቀለም ማለት ሲሆን አባቱ ቆዝሞስ እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ ኢየሉጣ ማለት ምልእተ ሃይማኖት ማለት ሲሆን ሀገሯ ሮም ነው፡፡ እለእስክንድሮስ በነገሠ ጊዜ በሃይማኖት ምክንያት በምእመናን ላይ ስደት ደረሰባቸው፤ ኢየሉጣም የሦስት ዓመት ሕፃኑን ቂርቆስን ይዛ ከሮም ወደ ጠርሴስ ተሰደደች፡፡ ንጉሡ ክርስቲያኖችን እያደነ ወደ ሸሹበት ሀገር ደርሶ አገኛቸው፤ ቅድስት ኢየሉጣንም ይዞ ‹‹ሀገርሽ የት ነው? ስምሽ ማን ይባላል? ወገንሽ ማን ነው?›› ብሎ ጠየቃት፡፡ እርሷም ‹‹ስሜ ክርስቲያን ሀገሬ ሮም ነው፤ ከአንተ ሸሽቼ ብመጣ አገኘኸኝን?›› አለችው፡፡ መኰንኑም መልሶ ‹‹ለጣዖት ስገጂ ስምሽን ግለጪ እንዳትሞቺ›› አላት፤ እርሷም ‹‹ሞት የሚሽረው ስሜ ኢየሉጣ ነው›› አለችው፡፡ ‹‹ለአማልክት መሥዋዕት አቅርቢ›› ብሎ ባዘዛት ጊዜ እርሷ ‹‹እውነትን ማወቅ ከፈለክ ወደ መንደር ልከህ የሦስት ዓመት ሕፃን አስመጣና የምናመልከውን እርሱ ይንገረን›› አለችው፡፡
   ንጉሡም ወታደሮችን አስልኮ ቂርቆስን አመጡለት፤ ከዚያም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስን ከሐዲው መኰንን ይዞ ‹‹ስምህ ማነው?›› ብሎ በጠየቀው ጊዜ ‹‹ከንጹሕ ምንጭ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው እናቴ የሰየመችኝ ሞክሼ ስም ቂርቆስ ነው›› በማለት መለሰለት፡፡ መኰንኑም ‹‹ስታድግ ሹመት ሽልማት እሰጥሀለሁ በወርቅ በብር አከብርሃለሁና ለአማልክት ስገድ ክርስቶስን ካድ›› ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን ‹‹የሰይጣን ወዳጅ ለእውነትም ጠላቷ የሆንክ ከእኔ ራቅ›› አለው፡፡ በዚህም መኰንኑ ተቆጥቶ መከራ አበዛበት፤እንደገናም በእናቱና በእርሱ አፍንጫ ጨውና ሰናፍጭ አስጨመረባቸው፡፡ ሕፃኑ ግን በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ስለጠነከረ ‹‹ነገርኽ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ሆነ፤ ከማርና ከስኳርም ለአፌ ጣመኝ›› እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡ መኰንኑ በዚህ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ የብረት ችንካሮችን እንዲሰኩባቸው አደረገ፤ ሆኖም ግን በጌታችን ፈቃድ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ጉዳት አላደረሰባቸውም፡፡
  ከዚያም ወደ ወህኒ ቤት ወሰዷቸው፤ በኋላም በደረቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ስቃያቸውን አራቀላቸው፡፡ የሕፃኑ ምላስ እንዲቆረጥ አዝዞ ቢያስቆርጠውም ክብር ይግባውና ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ ከዚያም በታላቅ ጋን ውኃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውኃ ድምጽ የተነሳ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ አገኛት፤ ሕፃኑም ‹‹እናቴ ጨክኚ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ እኛንም ያድነናል›› እያለ ወደ ፈጣሪው ጸልዮላት ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ ቅዱስ ገብርኤል ውኃውን አቀዝቅዞ አውጥቷቸዋል፤ ይህም የሆነው ሐምሌ 19 ቀን ነው፡፡
   በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚቀዳጅበት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ሁሉ ቃል ኪዳን ሰጥቶት ጥር 15 ቀን ከእናቱ ጋራ አንገቱን ተቆርጦ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል፡፡ በዚህ ዕለትም ብዙ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበርተኞች በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ የሰማዕታቱ በረከት ይደርብን አሜን!
           ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መድበለ ታሪክ ፣ ስንክሳር ዘጥር 15


Репост из: ወድሰኒ ​​
አባታችን አቡነ ዘርአብሩክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::



“ከቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር (የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።”) መዝ.፻፲፭/፻፲፮፡፲፭ (115/116፡15)

የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና።
መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ነው። ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው።
መዝ ፴፫፡፲፭-፲፯ (መዝ.33፡15¬-17)

የጻድቁ አባታችን የአቡነ ዘርዓ ብሩክ አባት እና እናት የተባረኩ ከቅዱሳን ወገን የሚሆኑ ነበሩ። የአባታቸው ስምም ቅዱስ ደመ ክርስቶስ ሲባል እናታቸው ደግሞ ቅድስት ማርያም ሞገሳ ትባላለች። ጻድቁ አባታችን ገና በእናታቸው ማህጸን እያሉ ነበር ብዙ ተአምራት የሚያደርጉት እግዚአብሔር መርጧቸዋልና። በኋላም ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ8ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ ላይ በነሐሴ 27 ጻድቁ አባታችን ተወለዱ። በ40ኛ ቀናቸውም ተጠምቀው በካህናት አፍ "ጸጋ ክርስቶስ" ተባሉ ከዛም ቤተሰቦቻቸው በጥሩ እድገት አሳደጉአቸው። 7 አመትም በሞላቸው ግዜ "በልጅነቴ የዚን ዓለም ክፋቱን እንዳላይ" ብለው ቢጸልዩ ዓይናቸው ታውሯል።
ቤተሰቦቻቸውም ጠቢቡ ሰሎሞን "የእግዚአብሔር ቃል ነውርን ይሸፍናል" እዳለው ትምህርት ሊያስተምሩአቸው አስተማሪ ጋር ቢወስዱአቸው ታመው ተመልሰዋል የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለምና። ነገር ግን የሚያስፈልጋቸውን እውቀት ፈጣሪ አምላክ ራሱ ገልጾላቸዋል:: ክህነትን እስከ ጵጵስና እራሱ መድሃኔ ዓለም ክርስቶስ ሰጥቷቸዋል። 12 አመትም በሞላቸው ግዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ አይናቸው በርቶላቸው ታላላቅ ተጋድሎን ማድረግ ጀመሩ።
በእግዚአብሔር ዘንድ ጵጵስና እንደተሾሙ የሃጥያት ማሰርያን ያስሩና ይፈቱ ዘንድ ጵጵስናን በሾማቸው ግዜ እግዚአብሔር ያወጣላቸው ሁለተኛ ስም "ዘርዓ ብሩክ" ይባል ነበር። 3ኛውም ስማቸው ደግሞ "ጸጋ እየሱስ" ይባላል:: ጻድቁ አባታችን በዚህ አለም በህይወተ ሥጋ ሳሉ አቡቀለምሲስ እንደሚባል እንደ ዮሃንስ ወልደነጎድጉአድ እግዚአብሔር እሱ ወዳለበት ወደ ሰማይ አውጥቶ በገነት መካከል ያኖራቸው ነበር:: እግዚአብሔር አምላክ ለወዳጁ ለብጹዕ አባታችን ዘርዓ ብሩክ በጎ ነገር እንዳደረገለትና ያለ ድምጽ የሰማይ ደጆችን አልፎ የእሳት ባህርን ተሻግሮ ፈራሽ በስባሽ ሲሆን እንደ ህያዋን መላእክት በፍጥነት ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ከአድማስ እስከ አድማስ ይደርስ ዘንድ 12 ክንፍን ሰጣቸው። መላእክትም ለሌሎች ቅዱሳን ያልተሰጠ ይህንን ስልጣን አይተው ለምድራዊ ሰው ይህ ነገር እንዴት ይቻላል? እያሉ አደነቁ።ከዛም በኋላ ጻድቁ አባታችን ከፈጣሪ ዘንድ የመላእክትን አስኬማ፣ የሾህ አክሊል አምሳያ የሆነውን መንፈሳዊ ቆብን,ሰማያዊ ቅናትን እና የደረት ልብስን(ስጋ ማርያም) ተቀብሎ በጾም እና በጸሎት በልመና እና በስግደት እግዚአብሄርን ሲያገለግል ኖረ። ከዛም በላይ ወንጌልን እጅግ ብዙ በማስተማር ደከመ።

ከኢትዮጵያም አልፎ ግብጽ ድረስ ገባ የእስክንድርያውን ሊቀ ጳጳስ አባ ዮሐንስን አገኘውና እርስ በርስ ሰላምታን ተለዋውጠው እጅ ተነሳሱ ከዛም ተመልሶ ወደ ሃገሩ መጣ ከዛም ኢትዮጵያ ውስጥ እየተመላለሰ ወንጌልን አስተማረ እጅግ ስጋን በሚያስጨንቅ ትጋትም የኢትዮጵያን ህዝብ ማርልኝ እያለ እያለቀሰ ይጸልይ ነበር።

አቡነ ዘርዓ ብሩክ "ዓባይ" እና "ግሽ ዓባይ" የሚሉ ስሞች እንዳወጡ አንድ ቀን አባታችን የንጉስ ጭፍሮች ሲያሳድዷቸው ግዮን ደረሱ። እንደደረሱባቸው ሲያውቁ ዳዊታቸውንና ለወንጌል ስብከት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ 7 መጻሕፍት ሁሉ ለግዮን ወንዝ አደራ ሰጡዋት። ከ5 አመት በኋላ ሲመለሱ" ኦ ግዮን ግሥኢ መፃሕፍትየ -- ግዮን ሆይ መጻሕፍቴን ግሺ መልሺልኝ " (ግሽ ዓባይ -- የሚባልም ከዚህ የተነሳ ነው።) ቢሉአት አንድም የውሃ ጠብታ ሳይኖርባት ዳዊታቸውን ብትመልስላቸው ለደቀ መዝሙራቸው ዘሩፋኤል አሳዩት ሁለቱም የእግዚአብሔርን ሥራ አደነቁ። ከዛም በኋላ ግዮንን ባረክዋትና "ይኩን ፈውስ ዓብይ በውስቴትኪ -- በውስጥሽ ታላቅ ድኅነት ይደረግብሽ" አሉ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ መካኖች ይወልዱ፣ ድዉዮች ይድኑ ጀመር "ወእም አሜሃ ተሰምየት ዓባይ ይእቲ ፈለግ -- ከዛ ጊዜ ጀምሮ ይህች ዓባይ ተብላ ተጠራች።" እስካሁንም በዚሁ ስም የሚጠራው ከዚ በመነሳት ነው:: ከዚህም ሌላ ጻድቁ አባታችን በዚሁ ወንዝ አካባቢ ለ 30 አመት ሲጸልዩ ፈጣሪ አምላክ ጸሎታቸውን ሰምቶ እጅግ ልዩ የሆነ ቃል ኪዳን ሰቶአቸዋል።

በስተመጨረሻም የሚያርፉበት እለት በደረሰ ሰአት መልአከ ሞት መቶ እስኪደነግጥ እና ወደ ኋላው እስኪያፈገፍግ ድረስ ነው ነው እግዚአብሔር ጸጋውንና ክብሩን ያበዛላቸው: በስተመጨረሻም ጥር በገባ በ13 ቀን በ482 አመታቸው ስጋቸው ከነፍሳቸው ተለይታ ገነትን ወርሰዋል::

ከጻድቁ አባታችን ከአቡነ ዘርዓብሩክ እግዚአብሔር አምላክ ከበረከታቸው እርዳታቸውን ያሳትፈን

ምንጭ: ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።


ዘወይን

ዘወይን❨፪×❩ቤተ ቃና ዘወይን
ቤተ ቃና ዘወይን❨፪×❩

በቃና መንደር ዘወይን
ሰርግ ተደግሶ ዘወይን
ወይኑ ተሰናድቶ ዘወይን
ዳሱ ተቀድሶ ዘወይን
ዶኪማስም ጠራ ዘወይን
ደቀመዛሙርቱን ዘወይን
ኢየሱስንና ዘወይን
ማርያም እናቱን ዘወይን
     /አዝ = = = = =
ሲበሉ ሲጠጡ ዘወይን
እጅግ ደስ አላቸው ዘወይን
ያ መናኛ ወይን ዘወይን
እየጣፈጣቸው ዘወይን
እልልታውም ደምቋል ዘወይን
ሙሽራውም ኮርቷል ዘወይን
ሰርጉ ለእንግዶቹ ዘወይን
የበቃ መስሎታል ዘወይን
     /አዝ = = = = =
ወይኑ በመካከል ዘወይን
አለቀ ከጋኑ ዘወይን
አፍረው ተደበቁ ዘወይን
አሳላፊው ሁሉ ዘወይን
ማንም ሰው ሳይነግራት ዘወይን
ይህንን ተረድታ ዘወይን
ድንግል ልታማልድ ዘወይን
ሔደች ወደ ጌታ ዘወይን
     /አዝ = = = = =
ጋኖቹን ሙሏቸው ዘወይን
ውሃውን ቀድታችሁ ዘወይን
ብሏችኋል ልጄ ዘወይን
ታዘዙ ታምናችሁ ዘወይን
ገና ስትናገር ዘወይን
አሳላፊዎቹ ዘወይን
አምነው ጓዳ ገቡ ዘወይን
ተሞሉ ጋኖቹ ዘወይን
     /አዝ = = = = =
ማድጋው ሲከፈት ዘወይን
መልካም ወይን ሆነ ዘወይን
የክርስቶስ ክብር ዘወይን
በቤቱ ገነነ ዘወይን
የእመአምላክ ጸሎት ዘወይን
ታሪኩን ቀየረ ዘወይን
መናኛው በሐዲስ ዘወይን
ይኸው ተቀየረ ዘወይን
    /አዝ = = = = =
ዛሬም ለደከሙ ዘወይን
አልጫ ለሆኑ ዘወይን
ለነፍሳቸው ጣፋጭ ዘወይን
አልቆባቸው ወይኑ ዘወይን
ድንግል ትቆማለች ዘወይን
ስለነሱ ተግታ ዘወይን
እንዲጣፍጡላት ዘወይን
ለምና ከጌታ ዘወይን

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

 ╔✞════●◉❖◉●════✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
@enamsgn @enamsgn
@enamsgn @enamsgn
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞════●◉❖◉●════​✞╝
✍ ወድሰኒ


Репост из: ወድሰኒ ​​
የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፫፥፲፫

ስለ ጌታችን ኢየሱስ ጥምቀት

ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ዮሐንስ ግን "እኔ ከአንተ ልጠመቅ እሻለሁ፤ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህን?" ብሎ አይሆንም አለው። ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ "አሁንስ ተው፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናልና" አለው።  ከዚህም በኋላ ተወው።

ጌታችን ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ፥ ወዲያው  ከውኃ ወጣ፤ እነሆ፥ ሰማይም ተከፈተለት፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ አየ፤ እነሆ፥ "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ለመስዋዕትነት የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው" የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።

ሰማይና ምድር ያልፋል ቃሌ ግን አያልፍም አለ ጌታ ለደቀመዛሙርቱ

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ።

Показано 20 последних публикаций.