Репост из: ወድሰኒ
የካቲት ፲፯ /17/
በዚች ቀን ከላይኛው ግብጽ ከአክሚም መንደር መነኰስ ሚናስ በሰማዕትነት አረፈ።
ይህም ቅዱስ በአንድ ገዳም ውስጥ እያገለገለና እየተጋደለ ከገዳሙ ደጃፍ ሳይወጣ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ።
እስላሞችም በግብጽ አገር በነገሡ ጊዜ ለእግዚአብሔር ከርሱ ጋር ለዘላለሙ ህልው የሆነ ከባሕርዩ የተወለደ ልጅ የሚሠርፅ መንፈስ ቅዱስም የለውም እንደሚሉ ሰማ ስለዚህም ነገር እጅግ አዘነ።
ከአበ ምኔቱም ቡራኬ ተቀበለ ወደ እስሙናይን ከተማ ወጥቶ ሔደ የእስላሞች ሠራዊት አለቃ በሆነ በመኰንኑ ፊት ቁሞ እንዲህ አለው። እናንተ ለእግዚአብሔር ከባሕርዩ የተወለደ ልጅ እንደሌለው አድርጋችሁ የምትናገሩ እውነት ነውን መኰንኑም አዎን ልጅ አለው ማለትን ከእግዚአብሔር እናርቃለን አለ።
አባ ሚናስም ያለ ልጅ ልታምኑ አይገባም እርሱም ያለ ዘር ያለ ሩካቤ የሆነ ነው ከባሕርዩ ተወለደ እንጂ አለው። መኰንኑም ልጅ አለው ማለት በሕጋችን ክህደት ነው አለ አባ ሚናስም እንዲህ አለው መኰንን ሆይ እወቅ የከበረ ወንጌል በወልድ ያመነ የዘላለም ሕይወት አለው በእግዚአብሔር ልጅ በወልድ ያላመነ ሕይወትን አያይም የእግዚአብሔርቁጣ በላዩ ይወርዳል እንጂ ብሏልና።
ስለዚህም መኰንኑ እጅግ ተቆጣ ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጡ ሥጋውንም በየቊርጥራጭ ቆራርጠው በባሕር እንዲጥሉት አዘዘ ምእመናንም ሥጋውን ወስደው በበጎ አገናነዝ ገንዘው ቀበሩት መታሰቢያውንም አደረጉ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር