Репост из: abdu_rheman_aman
ሚስት ከፈለክ ዲን ያላትን ሱኒዋን ቆንጆ ፈልግ!።
-------
በጣም የማምነው ጓደኛዬ መጥፎ ሚስት አግብቶ የሚከተለውን ብሎኛል ይላሉ አል-ኢማሙ አሽ-ሻፊዒይ፦
"تزوجت لأصون ديني ، فذهب ديني
ودين أمي ودين جيراني. "
ዲኔን ለመጠበቅ ብዬ አገባሁኝ: ግን የኔም ዲን የናትም ዲን የጎረቤቴም ዲን ጠፋ!"
[መናቂቡ ሻፊዒይ ሊል በይሀቂይ 2/192]
ልብ በሉ! የራሱም ዲን የእናቱም ዲን የጎረቤቱም ዲን የመበላሸት ትልቁ ምክንያት እርሱ: በስነ-ምግባሯም በዲኗም የወረደቺን ደካማ ሴት በመምረጡ ምክንያት ነው። እናም ሚስት ስፈልጉ ዲን ያላትን ሱኒዏን ቆንጆ ይሁን!!!።
ሚስቱ የናቀቺውና ሁሌም የምታዋረደው የሆነ ግለሰብ ነበር። የሚስቱን ንቀት መቋቃም ሲያቅተው ወደ ሱፍያን ኢብኑ ዑየይናህ ስሞታ ሊያቀርብ መጣና ስሞታውን አቀረበ። ሱፍያን ኢብኑ ዑየይናህም: እርሷን መጀመሪያ የመረጥካት ልቅናን ፈልገህ ነበርዴ? ‹አሉት› ሰውየውም አዎን ልቅናን ፈልጌ ነበር አሏቸው። ሱፍያን ኢብኑ ዑየይናህም የሚከተለውን አሉ ፦
من ذهـب إلى العز ابتلي بالـذل ،
ومن ذهـب إلى المال ابتلي بالفقـر ، و من ذهب إلى الـدين يجمع الله له العز و المال مع الـدين "
ልቅናን ፈልጎ የሄዴ፣ በውርደት ይፈተናል። ገንዘብን ፈልጎ የሄደ በድህነት ይፈተናል። ዲንን ፈልጎ የሄደ ልቅናውንም ገንዘቡንም ከዲኑጋር አሏህ ይሰበስብለታል!።
[ሒልየቱል አውሊያኧ 7/289]
ልብ በሉ!። የዲኗን ጎን ሳታይ ገንዘቧን ብቻ ከሆነ አላማህ አሏህ በድህነት ሊያቆራምዳቹህ ይችላል። ልቅናን ብቻ ፈልገህ ከሆነ አሏህ በውርደት ሊሸብብህ ይችላል። ስለዚህ ዲን ያላትን ጭምቷን ምረጥ!።
✍አብደረህማን አማን
t.me/abdu_rheman_aman