Фильтр публикаций


ቀናት ሁሉ ረመዷን ቢሆኑ እንዴት ደስ ይላሉ መሠላችሁ !
እርካታ ፣ እርጋታ፣ ሰላም፣ ደስታ

ረመዷንን የሠጠኸን ጌታ ወላሂ ብዙ ነገር ሠጠኸን።

https://t.me/MuhammedSeidAbx


ሓጃዬ ወጥቷል በረካ ሁኑ። ከሁለት ሰዓት በላይ ፈተና ላይ ነበርኩ። የዶክትሬት /ፒ ኤች ዲ ትምህርቴን ዛሬ ጨረስኩ።

አልሐምዱ ሊላህ

https://t.me/MuhammedSeidAbx


ትንሽ ሐጃ ገጥሞኝ ነው በዱዓችሁ። አላህ መልካሙን እንዲወፍቀኝ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx


ረመዷን -3
****
ቀንና ሌሊቱን ጭምር ለፆመኞች ማፍጠሪያ በማዘጋጀት ተጠምደው የታላቁን ፆም ድባብ፣ ጣእምና እርካታ ለማጣጣም ጊዜ እንዳጡ ረመዷን የሚወጣባቸው ሁሉ ትልቅ ምንዳ ይገባቸዋል ።
አላህ ጀዛቸውን አብዝቶ ይክፈልልን።

https://t.me/MuhammedSeidAbx


ረመዷን -2
***
ረመዷን ገባ ማለት የጀነት በር ተከፈተ ማለት ነው። ከኛ የሚጠበቀው ጀነት የሚጠበቀው ጀነት የሚያስገቡ የአምልኮ ተግባራትና መልካም ሥራዎች ላይ የሙጥኝ ማለት ነው። ጀነትን እያሰቡ መፆም ።

አላህ ከጀነት ሰዎች ያድርገን።

https://t.me/MuhammedSeidAbx


ረመዷን አንድ ብለን በሱሑር ጀምረናል ።
አሏህ ይቀበለን።

https://t.me/MuhammedSeidAbx


መላው ዘመድ ወዳጅ።
እንኳን አደረሣችሁ።
የኸይር፣ የበረካ፣ የችሮታ ወር ይሁንልን ።
ረመዷን ነገ ቅዳሜ 1 ይላል ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx


"ቅርብ ነኝ ለምኑኝ።" ብሎን የለም ወይ? ለምን እሩቅ እንደሆነ አድርጋችሁ ታስቡታላችሁ?


ሸዕባን 26

ለረመዷን 3 ወይ 4 ቀን ቀረው።
ረመዷን ቅዳሜ ወይ እሁድ ይገባል።
አንመረቅንም ወይ
ለቤተሰብ ሀዲያና የአስቤዛ አንልክም።
ዐፈውታ አንጠያየቅም ወይ።
ረመዷንን እንደ ታላቅ እንግዳ ወጥተን አንቀበልም ወይ።
ተደዋውለን እንኳን አደረሰህ፣ አደረሰሽ፣ አደረሳችሁ አንባባልም ወይ

አልሐምዱ ሊላህ ለዚህ ቀን ያደረስከን ጌታ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx




ትልቅ ኪሣራ ውስጥ ያለ ሰው ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ ?

ከአላህ እዝነት ተስፋ የሚቆርጥ ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx


Репост из: Nejashi Printing Press
የሰይደና ዑሥማን ተቀማጭ ሒሳብ
*******
ሙስሊሞች በስደት መዲና ከደረሱ በኋላ የመዲና ነዋሪ ቁጥሩ ጨመረ፡፡ ቁጥራቸው ብቻ ሳይሆን የዉሃ ፍጆታቸዉም ጨመረ፡፡ የሩማን የጉድጓድ ዉሃ በመዲና ዉስጥ ከሚገኙ የጉድጓድ ዉሃዎች መካከል ትልቁ ሲሆን ባለቤትነቱም የአንድ ይሁዲ ነበር፡፡ ይሁዲው እያንዳንዷን ጠብታ ዉሃ የሚሸጥ ስግብግብ ነው፡፡
ዑሥማን ረ.ዐ ሁኔታዉን ባዩ ጊዜ በቀጥታ ይሁዲው ዘንድ በመሄድ ጉድጓዱን እንዲሸጥለት ጠየቁት፡፡ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡
ዑሥማን ሌላ ሀሳብ በማቅረብ ግማሹን ማለትም አንድ ቀን ለሱ አንድ ቀን ለሳቸው በሚሆን መልኩ እንዲሸጥላቸዉ ጠየቁት፤ ተስማማ፡፡ ሰውዬው ይህን ያደረገው ዑሥማን ሀብታም ነጋዴ በመሆናቸው ዋጋ ጨምረው ሙሉዉን ይገዙኛል ብሎ ስላሰበ ነበር፡፡ ግና በሚገርም ሁኔታ የምንጩ ዉሃ እየቀነሰ ሄዶ ሊጠፋ ሁሉ ተቃረበ፡፡ ለካስ ዑሥማን የራሣቸዉን ድርሻ ለሌሎች ተጠቃሚዎች በነፃ ስለለቀቁ ነበር ያ ሊሆን የቻለው፡፡ ሰዎች በዑሥማን ተራ ሄደው ከምንጩ ይቀዳሉ፤ በአይሁዱ ቀን ግን አንዳቸዉም አይሄዱም፡፡ ስለዚህ አይሁዱ ገቢ አጣ፡፡ በዚህን ጊዜ ኪሳራ ዉስጥ እንደገባ ተሰማው፡፡ ድርሻዉንም ሊሸጥለት ተስማማና በሀያ ሺህ ድርሀም ገዙት፡፡ ዑሥማን ምንጩን ሰዎች እንዲጠቀሙበት ለአላህ ሲል ሠጠ፡፡
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አንድ ሶሐባ መጣና የገዛበትን እጥፍ ከፍሎት እንዲሸጥለት ጠየቀው፡፡ “ከዚያ በላይ ተሠጥቶኛል” አሉት ዑሥማን፡፡ “ሦስት እጥፍ ልክፈልህ” አላቸው፡፡ “ከዚያም በላይ ተሠጥቶኛል፡፡” አሉት፡፡ እስከ ዘጠኝ እጥፍ ቢሠጣቸዉም ከዚያ በላይ ተሠጥቶኛል ብለው እንቢ አሉ ዑሥማን፡፡ አይሁዱ በመገረም መዲና ዉስጥ እኔ ከሠጠሁህ በላይ ማነው ሊሠጥህ የሚችል! አላቸው፡፡
ዑሥማንም “አላህ አሥር ዕጥፍ ሠጥቶኛል፡፡” አሉት፡፡

ዑሥማን ይህን ምንጭ የአላህን ዉዴታ ሽተው ከ1400 ዓመታት በፊት ለሙስሊሞች ጥቅም ለገሱ፡፡ ከጊዜ በኋላ ደግሞ በዙርያው ተምር ተተከለ፡፡ በየጊዜው የተለዋወጡ ሙስሊም መንግሥታት ለምንጩና ለተምሩ እንክብካቤ እያደረጉ ትልቅ እርሻ ሆነ፡፡

ከዚያ ምንጭ የበቀለው ተምር ይሸጥና ገቢው ለወላጅ አጥ ሕፃናት እንክብካቤ ይዉላል፤ ሌላው ደግሞ የአውቃፍ ሚኒስቴር በሚያስተዳድረው በዑሥማን ሥም በተከፈተ ሂሳብ ዉስጥ ይቀመጣል፡፡ በዚህ መልኩ የዑሥማን ምንጭ ገቢ እያደገ ሄደ፡፡ በርሱ ገንዘብም በሐረም ዙርያ ቦታ ተገዛና ለእንግዳ ማረፊያ የሚሆኑ ቤቶች ተገነቡ፡፡ ቤቶቹም ትልቅ ገቢ የሚያስገኙ ሆኑ፡፡

ዑሥማን በዚህ መልኩ ባንክ ዉጥ ሂሳብ አላቸው፡፡ በሕይወት ባይኖሩም ከ14 ምዕተ ዓመታት በፊት ከአላህ ጋር የተጀመረ ንግዳቸው ቀጥሏል ፡፡ ምንዳቸው ምን ያህል በዝቶ ይሆን !!
ከሞት በኋላ የሚጠቅም ቀጣይ ሰደቃ ማለት ይኸው ነው!!

https://t.me/NejashiPP


አልሐምዱ ሊላህ ባለፉት ቀናት ብቻ ከ500 በላይ ቁርአን መሰብሰብ ችያለሁ ። "የዐርሽ ጥላ ጀማዓ" ትልቁን እገዛ አድርጎልናል 100 ቁርአን። ይበልጥ የተቸገሩ መስጂዶችንም እያጠናሁ የሠጣችሁኝን አማና ለማድረስ ሞክሬያለሁ ። እቀጥላለሁም። አላህ ይቀበላችሁ። ለሙታኖቻችን ቀጣይ ሶደቃ ያድርገው። በሕይወት ያሉትንም ምንዳቸውን ያብዛልን ። ጀዛኩመሏሁ ኸይራ።
የዘንድሮ ሩጫዬ ለጊዜው በዚሁ ይብቃ። ለከርሞ ያድርሰን። ቁርአን በረመዷንም ከረመዷን ውጭ ከሚወዱት አብዝተው ከሚያነቡትም ያድርገን። አሚን።

https://t.me/MuhammedSeidAbx




አንድ ሰው የሌለውን ነገር እሱ አጠገብ አለማውራትህ ለሰውዬው መልካም ከመዋል ይቆጠራል ያሉ ደጋጎች አሉ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx






አላህን ብቻ ያዙ።

አላህን ብቻ ከያዘ ሰው ጋር ገጥሞ ያሸነፈ አንድም የለም።

ሶባሐል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx


እጅግ የቅርቤ ነው ብለህ በምትተማመነው ሰው ጭምር ልትከዳ ትችላለህ ።

ከኔ ውጭ አንድንም ሰው ማመን የለባችሁም የሚል ይመስላል የነፍሳችን ጌታ።

እደሩልኝ።



https://t.me/MuhammedSeidAbx


ሆድ ሲብሰኝ ሶለዋት ነው የሚቀናኝ

ሙስጦፋ ነቢ ዐለይከ ሰላሙ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

Показано 20 последних публикаций.