Репост из: Taha Ahmed
በዓረፋ ቀን ልንተገብራቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባራት የትኞቹ ናቸው?
ኢብኑ ረጀብ ለጣኢፉ አል-መዓሪፍ በተባለው ኪታባቸው ላይ የጠቀሱትን እና ሌሎችም ዑለማዎች ከጠቆሟቸው ነጥቦች ከዋና ዋናዎቹ የተወሰኑትን በአጭሩ እንመልከት:‐
ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ:- “በዓረፋ እለት ከእሳት ነፃ መውጣቱን እና ለወንጀሎቹ ምህረትን የሚፈልግ ሰው ለዚያ ሰበብ የሚሆኑ ነገሮችን መፈፀም ይኖርበታል:: ከነዚያ ሰበቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:-
1️⃣ የዓረፋን ቀን መፆም:-
አቡ–ቀታዳ ረዲየላሁ ዓንሁ እንዳስተላለፉት:‐«የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ እለተ ዓረፋ ጾም ተጠየቁ፤ እሳቸውም "ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ" አሉ።» (ሙስሊም ዘግበውታል)
2️⃣ መላ አካላትን አላህ ከከለከላቸው ነገሮች ማራቅ በተለይ ፈፅሞ አላህ ምህረት ከማያድርግለት ወንጀል በእሱ ላይ ማጋራት (ሺርክ) እራሱን መጠበቅ ይኖርበታል::
3️⃣ የተውሂድ መገለጫ የሆነውን እና የአላህን አጋር የሌለው ብቸኛ አምላክነት እንዲሁም በሁሉ ነገር ላይ ቻይነት የሚያረጋግጠውን “ላ ኢላሃ ኢለላሁ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሀምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢ ቀዲር ” የሚለውን ዚክር ማብዛት:: ይህ ዚክር በእለቱ አላህን ከምናወድስባቸው ቃላት የተሻለውና ምርጡ እንደሆነ መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ ዓረፋ ቀን ዱዓእ በተናገሩበት ወቅት እንዲህ ሲሉ አሳውቀዋል:– "እኔና ከኔ በፊት የመጡት ነብያት ከተናገርነው ንግግር ሁሉ በላጩ ይህ ነው።"
4️⃣ አላህን ምህረት እንዲያደርግለት እና ከእሳት ነፃ ከሚወጡት ባሮቹ እንዲያደርገው አብዝቶ መለመን:: የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:- “ከዓረፋ ቀን የበለጠ አላህ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም::” (ሙስሊም ዘግበውታል)
በተጨማሪም ዱዓእ ተቀባይነት ሊያገኝበት ከሚችልባቸው ቀናት መካከል አንዱ እና ልዩ ቀን ነው:: መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ በማለት የዓረፋ ቀን ዱዓእ ገልፀዋል:- “ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓእ ነው::” ስለሆነም በዚህ ቀን ለራሳችን፣ ለወላጆቻችን፣ ለልጆቻችን፣ ለባለቤቶቻችን፣ ለቅርብ ዘመዶቻችን፣ በኛ ላይ ሀቅ ላላቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ሁሉ በርትተን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል።
5⃣ በአጠቃላይ በተሰማራንበት ቦታ ሁሉ በቻልነው አቅም መልካም ነገሮችን ከማድረግ እንዲሁም አላህን ከማውሳት ልንሳነፍ አይገባም:: በተለይ ከሰላት በኋላ ተክቢራ ማድረግ ከዛሬው እለት ፈጅር ሰላት የሚጀምር መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም:: ይህም ማለት ተክቢራ ማድረጉ ዛሬ የተጀመረው ከአምስቱ ግዴታ ሰላቶች በኋላ የተገደበ (ሙቀየድ) በመባል የሚታወቀው ነው እንጂ ከዚያ ውጪ ያልተገደበ (ሙጥለቅ) በመባል የሚታወቀው የተክቢራ አይነት እስከ አያመ-አተሽሪቅ ማብቂያ ማለትም የአስራ ሶስተኛው ቀን ፀሀይ እስከትጠልቅ ድረስ ይቀጥላል::
አላህ በመልካም ስራ ላይ ያበረታን እንዲሁም ይቀበለን!
✍️ ጣሀ አህመድ
🌐 htt rel='nofollow'>ps://t.me/tahaahmed9