⚘️ዲን እየተማሩ ነውን?
🪴ኢስላም ከማንኛውም ነገር በፊት ዕውቀትን በመገብየት ላይ አደራ ይላል፡፡ ምክንቱም የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዕውቀትን መሰረት ያላደረጉ ከሆነ አላዋቂ ሳሚ ... እንደሚባለው ብሂል ከልማቱ የምንዘፈቅበት አዘቅቱ ያመዝናል፡፡ አንዳንዴም በኛ ሳይገደብ የኛው የጥፋት ረመጥ ይቀጥልና ሌሎችን እኛ የሰመጥንበት አዘቅጥ ውስጥ እንዲዋኙ የጥፋት ጀልባ እና መቅዘፊያ እንድንሆን ያደርገናል፡፡
🪴ቁርአን ስለ እውቀት ፋይዳዎችና ስለ አዋቂዎች ደረጃ ብዙ ይላል። ዓዋቂው አምላካችን ስለ እውቀት ባለቤቶች ከፍ ያለ ደረጃ ዓዋቂዎች በሚገነዘቡት መልኩ እንዲህ ይላል፡-
"يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ" [٥٨:١١]
«አላህ ከናንተ እነዚያ ያመኑትንና እነዚያ ዕውቀት የተሰጡትን በደረጃ ከፍ ያደርጋል» ሙጃደላህ፡11
🪴ታላቁ ሶሃብይና የቁርአን ተፍሲር ዓዋቂ ዓብደላህ ኢብኑ ዓባስ እንዲህ ሲል የአንቀፁን መልዕክት የሚያጠናክር ንግግር አላቸው «የተማሩ ሰዎች ደረጃ ከተራው ሙዕሚን ሰባት መቶ እጥፍ ይበልጣል፡፡ ከአንዱ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ ያለው ርቀት የአምስት መቶ ዓመት ርቀት ይሆናል»
በሌላ የቁርአን አንቀፅ አላህ እንዲህ ይላል፡-
"إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ" [٣٥:٢٨]
«አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው» ፋጢር፡28
🪴መልዕክተኛው (ﷺ) እንዲህ አሉ፤ «ዕውቀትን ቅሰሙ አላህን የምትፈሩት ባወቃችሁት ልክ ነውና»
አዎን! የማያውቁትን አካል እንዴት ተገቢውን ፍራቻ ይፈሩታል?!
🪴አላህ መልዕክተኛው (ﷺ) እንዲጨምርላቸው እንዲጠይቁት ያዘዘው ብቸኛ ነገር ዕውቀት ነው! ከየት አመጣኸው ትይኝ ይሆናልና ማስረጃውን :-
"وَقُل رَّبِّ زِدْنِي عِلْمًا "
«ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትን ጨምርልኝ በል» 20፡114
🪴የትኛውም የዕውቀት ደረጃ ላይ ብንገኝ በአላህ ከታገዝንና ጥረት ካደረግን ብዙ መሻሻል ይቻላልና አሁኑኑ ጥረት ማድረጉን እንጀምር።
🤲አላህ በኢስላማዊ ዕውቀት ወደተሻለ ደረጃ ከፍ እንል አንድ ያግዘን፤ እውቀትን ያግራልን። ልባችንን በቁርአን ያብራልን።
አሚን !
_
@abujunaidposts