😳 ውሸት እና ተንኮል 🙄!
ውሸትና ተንኮል ፣ ጓደኞች ነበሩ ፣
እውነትን ለማጥፋት ፣ እንዲህ ተማከሩ።
እውነት የተባለው ፣ ይሄ ጠላታችን ፣
መጥፋት አለበት ፣ ጭራሽ ከዓለማችን።
እኛ እየተጠላን ፣ እሱ እየተወደደ ፣
ብዙ ጊዜ አለፈ ፣ ዘመንም ነጎደ።
የኛ ብቻ ይሁን ፣ መላው ሀገር ምድሩ ፣
ውሸትና ተንኮል ፣ እንዲህ ተማከሩ ።
ከዕለታት በአንዱ ቀን ፣ ተንኮል እያደባ ፣
ከውሸት ጋር ሆኖ ፣ ከእውነት ቤት ገባ ።
እውነት ከጓደኞቹ ፣ ሠላምና ፍቅር ፣
በደስታ በሀሴት ፣ ይጫወቱ ነበር ።
ተንኮልም በድንገት ፣ እውነትን ተማታ ፣
ፍቅርም አዘነ ፣ ሠላምም ተቆጣ ።
ውሸት ብቅ አለና ፣ ከተደበቀበት ፣
ከተንኮል ጋር ሆኖ ፣ እውነትን ገደሉት ።
ሠላምና ፍቅር ፣ እጅግ እያዘኑ ፣
እንቅበረው ዘንድ ፣ ስጡን አስከሬኑን ።
ብለው ተማጸኑ ፣ ውሸትን በእምባ ፣
እውነት ተቀበረ ከመቃብር ገባ ።
ዓለምን የመግዛት ፣ ብርቱ ዓላማችው ፣
ውሸትና ተንኮል ፣ ሞላ የልባቸው ።
አንድ ቀን ፣ አቶ ውሸት ተነስቶ በጧት ፣
የሰፈሩን ሰዎች ፣ ደስታ ሲመለከት ።
ተጠራጠረና ፣ ወደ ቀብሩ ሮጠ ፣
ልክ እንደደረሰ ፣ በጣም ደነገጠ ።
እውነት ተፈልጎ ፣ መቃብሩ ሲታይ ፣
ምንም ነገር የለም ፣ አንዳችም የሚታይ።
አወይ ልፋታችን ፣ ተንኮል መጥተህ ብታይ ፣
እውነት ከቶ አልሞተም ፣ ዓርጎ ነው ሰማይ ።
እውነትና ዘይት ምንግዜም ከላይ ናቸው ::
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇
@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊