“የአማራ ክልሉን የሰብዓዊ ጥሰት አለም አቀፉ ማህበረሰብ በዝምታ ማለፍ የለበትም” -አምንስቲ ኢንተርናሽናል መግለጫ!
የኢትዮጵያ መንግሥት በአማራ ክልል ሰዎችን በመደዳ ማሰሩንና የመብት ጥሰት ማድረሱን ዓለም አቀፉ ማሕበረሠብ በዝምታ አልፎታል በማለት አምንስቲ ኢንተርናሽናል ቅሬታዉን አስታወቀ።
ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግሥት በአማራ ክልል በሺሕ የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን በመደዳና በጅምላ ማሰር የጀመረዉ ባለፈዉ መስከረም ነዉ። እስራቱ የተጀመረበትን አራተኛ ወር ምክንያት በማድረግ የአምስንቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅና የደቡባዊ አፍሪቃ ኃላፊ ትጌሬ ቻጉታሕ በሰጡት አስተያየት «አማራ ክልል በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች በመደዳና በጅምላ ሲታሰሩ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ዝም ማለቱ ከማሳፈር በላይ ነዉ።» ብለዋል።
በጅምላና በመደዳ የታሰሩት ሰዎች እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች፣ ዓለም አቀፍና የአፍሪቃ የመብት ተሟጋች አካላት ተፅዕኖ የማድረግ አቅማቸዉን እንዲጠቀሙም ኃላፊዉ ጠይቀዋል። ቻጉታሕ እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግስት የሕግ-ሥርዓትን አሁንም እየጣሰ ነዉ።
ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ «የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብቶች ቀዉስን» እይቶ እንዳላየ ማለፍ የለበትም ብለዋልም።«ክስ ሳይመሰረትባቸዉና ሳይፈረድባቸዉ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን ለወራት ማሰር« የአምንስቲ ኢንተርናሽና ባለሥልጣን እንዳሉት «የሕግ ጥሰት ብቻ ሳይሆን ግልፅ የሰብአዊ መብት ጥሰትም ነዉ» ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣናት በሐገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የሲቢክ ማሕበራትን ማገዳቸዉንም ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ተቃዉሟል። አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ጦር ኃይልና የአማራ ክልል ፀጥታ አስከባሪዎች በሺሕ የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ነዋሪዎችን እያሰሩ ወደተለያዩ አራት ማጎሪያ ማዕከላት መላክ የጀመሩት መስከረም 28 ቀን 2024 ነበር።
ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለአማራ ፋኖ
ንሥር ብሮድካስት መረጃ
ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም
=====================
ቤተሰብ ይሁኑ! ትግላችን በጋራ!
ትዊተር: x.com/nisirinternati1
ዮቱብ፣ https://youtube.com/@nibcnewsethiopia?si=_LD-OmtO1nJ0RVr2
ቴሌግራም: https://t.me/nisirbroadcasting
ቲክታክ:- tiktok.com/@nisirbroadcas…
ዌብሳይት : nisirbroadcasting.com
WhatsApp: +1 (252) 574‑6084
Telegram: +1 (252) 574‑6084