ከአማራ ፋኖ በጎጃም 2ኛ ክፍለጦር ደጋ ዳሞት ብርጌድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ እንደህዝብ ከገባበት ሁለንተናዊ የህልውና አዳጋ ለመውጣት ሲል ከአገዛዙ ሀይል ጋር እልህ አስጨራሽ የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ይገኛል።በዚህ መራር የትጥቅ ትግል ሒደት ውስጥ እንደድርጅትና እንደህዝብ በርካታ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ድሎችን አስመዝግበናል ።
ከነዚህ አንፀባራቂ ድሎች ከተገኘባቸው ቀጠናዎች መካከል አንዱና ዋነኛዉ ምናልባትም ግንባር ቀደሙ በደሙ ቀለምነት በአጥንቱ ብዕርነት የዚህን ሸማቂ ትውልድ ታሪክ እየከተበ የሚገኘው የደጋ ዳሞት ብርጌድ ነው። ባለፉት አንድ አመት ከሰባት ወር ገደማ ባሉት ጊዚያት ውስጥ ደጋዳሞትና የአካባቢው ማህበረሰብ የትግሉ ደጋፊ ከመሆን በዘለለ የትግሉ መሪ በመሆን ጭምር ለሌሎች ቀጠናዎች አርአያ ሆኖ አሳይቷል።
ለዚህም የደጋዳሞት ብርጌድ በተዋረድ ለሚያስተላልፋቸው ትዕዛዞችና መመሪያዎች ማህበረሰባችን ቅን ምላሽ በመስጠት በምዕላትም በስፋትም ተግባራዊ ማድረጉ ብቻ ለአብነት የሚጠቀስ ነው።
ስለሆነም ለአለፉት ሁለት ወራት ገደማ ማለትም ከህዳር 30 /2017 ዓ/ም እስከ ጥር30/2017 ዓ /ም ድረስ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ገደብ መነሳቱን እየገለፅን ዛሬ ማለትም ጥር 30/2017 ዓ/ም የአማራ ፋኖ በጎጃም 2ኛ ክፍለጦር ደጋ ዳሞት ብርጌድ ስራ አስፈፃሚ አባላት ጥልቅ ውይይትና ግምገማ በማድረግ የሚከተሉትን ውሳኔዎች ማስተላለፉን ለማሳወቅ እንወዳለን።
1,ለአለፉት ሁለት ወራት የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ተረጋግቶና አስቦ ወታደራዊ ዕቅዶችን እንዳያወጣና ለጠላት ሰራዊት ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠር በማሰብ በፈረስቤት ከተማ ውስጥ ከተለዩ ተቋማት ውጭ የሚገኙ ማነኛውም የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ ሆኖ እንዲቆዩ በወሰነው ውሳኔ መሰረት ጀግናውና ትዛዝ ዐክባሪው ማህበረሰባችን መመሪያውን ተቀብሎ የአላንዳች መሸራረፍ ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል።
የደጋዳሞት ብርጌድ ስራ አስፈፃሚ አባላትም የአዋጁን ተፈፃሚነትና የአስገኘውን ውጤት በጥልቅ በመገምገም ከዛሬ ማለትም ከጥር30/2017 ዓ/ም ጀምሮ ሁሉም የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተለመደውን አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ ወስኗል።
2,አዕምሯቸውን ለከርሳቸው ህሊናቸውን ለኪሳቸው ለአከራዩ ባንዳዎች በሙሉ:_ አገዛዙን በካድሬነት ለማገልገል ተስማምታችሁ የሹመት ደብዳቤ የተቀበላችሁ ካድሬዎች፣
ሚሊሻ፣ አድማ በታኝ፣ፖሊስ እንዲሁም ደግሞ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የጠላትን እኩይ ሴራ ተረድታችሁ በወገናችሁ ላይ ላለመተኮስ ከልባችሁ አምናችሁ ከጠላት የስምሪት ቀጠና ባጭር ጊዜ ውስጥ በመውጣት የወገን ሀይልን ብትቀላቀሉ የትኛውንም አይነት አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት እንደማይደርስባችሁ ለማሣወቅ እንወዳለን።
ይህንን ትዕዛዝ ተላልፎ በተገኘ ማነኛውም ግለሰብ ላይ የተለመደና የምታውቁትን አይነት እርምጃ ከመውሰድ ወደሗላ እንደማንል ለማሳሰብ እንወዳለን
በመጨረሻም በደጋ ዳሞት ወረዳ ስር ለምትገኙ ማነኛውም የጦር መሳሪያ ባለቤት ለሆናችሁ መንግስት ሰራተኞች በሙሉ:- የአገዛዙ ሀይል በአውደ ውጊያ ውሎዎች ላይ የተማረኩበትን መሳሪያዎች ለማካካስ ሲል የተመዘገበ የጦር መሳሪያ ያላቸውን መንግስት ሰራተኞች ደመወዝ በመከልከል መሳሪያቸውን ካላስገቡ በስተቀር ደመወዝ እንደማይከፈላቸው መመሪያ አውርዷል።
ይህን መመሪያ ተከትሎ መሳሪያውን ለጠላት በሚያስረክብ ማነኛውም ግለሰብ ላይ አስፈላጊውን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
አዲስ ትውድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ
🗣የአማራ ፋኖ በጎጃም 2ኛ ክፍለጦር ደጋ ዳሞት ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ክፍል!