አዳነች አቤቤ ከሻለቃ በላይ ከሆኑ የኮማንዶ እዝ አመራሮች ጋር ዝግ ስብሰባ ማካሄዷ ታወቀ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በትናንትናው እለት በአድዋ መታሰቢያ አዳራሽ ከሻለቃ እስከ እዙ መሪ ጀነራል ሹማ አብደታ ድረስ ያሉ የኮማንዶ እዝ ወታደር መሪዎችን ለሚዲያ ዝግ አድርጋ ሰብስባለች፡፡
በዚህ ስብሰባቸውም ጥቂት የደቡብ ተወላጆችና ቀሪዎቹ ሙሉ በሙሉ የኦሮሞ ተወላጆች የሆኑ መኮንኖች ናቸው የተገኙት፡፡
ነገር ግን ከምክትል እዝ አዛዡ አበባው ሰይድ ጀምሮ እስከ ሻለቃ ድረስ ያሉ የአማራ ተወላጆች በዚህ ስብሰባ እንዳይሳተፉ ተደርጓል፡፡
በስብሰባውም ይህ የተመረጠው የኮማንዶ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ ቤት እንደሚሰጠውና በምላሹ የተሰጠውን ትዕዛዝ ሁሉ እንዲፈጽም ግዴታ ተጥሎበታል፡፡
መከላከያ እንደ ተቋም የራሱን ቤት ሰርቶ ለሰራዊቱ የሚያድል ቢሆንም እነ አዳነች አቤቤ ይህን የቤት እደላ እኛ እንፈጽማለን ማለታቸውና በብሄር ለተመረጡ ሰዎች ብቻ ይህን ማድረጋቸው ጉዳዩ ፖለቲካዊ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ተራው ወታደር በጦርነት እየተሰቃየ ደሞዝ እንኳን ባጣበት ወቅት በህዝብ ቁጠባ የተገነባን ቤት እንሰጣችኋለን ማለታቸው የወቅቱ ጫና እንዳስጨነቃቸው ማሳያ ነው ተብሏል፡፡
ከዚህ ቀደም ለሪፐብሊካን ጥበቃ አባላት የመኖሪያ ቤት ሲሰጥ አኩርፎ የነበረው የኮማንዶ እዙ አሁን ላይ “ የምንሰጣችሁን ተልዕኮ በአግባቡ ተወጡ እንጂ ስለ ቤት አያሳስባችሁ” ተብሏል ይላሉ የመረጃ ምንጮች፡፡እየጠነከረ የመጣው የፖለቲካ ውጥረትና በየአቅጣጫው ያለው ውጊያ እነ አዳነች አቤቤን ይህን የኮማንዶ ሃይል እንዲያባብሉ እንዳደረጋቸውም ተጠቁሟል።
ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለአማራ ፋኖ
ንሥር ብሮድካስት መረጃ
ቅዳሜ የካቲት 01 ቀን 2017 ዓ.ም
=====================
ቤተሰብ ይሁኑ! ትግላችን በጋራ!
ትዊተር: x.com/nisirinternati1
ዮቱብ፣ https://youtube.com/@nibcnewsethiopia?si=_LD-OmtO1nJ0RVr2
ቴሌግራም: https://t.me/nisirbroadcasting
ቲክታክ:- tiktok.com/@nisirbroadcas…
ዌብሳይት : nisirbroadcasting.com
WhatsApp: +1 (252) 574‑6084
Telegram: +1 (252) 574‑6084