አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ። እንዴት ናቹ ያ ጀመዓ
እኛ የኑር አህለል ኸይር አባላት ከዚህ ቀደም ቡታጀራ ውስጥ የተለያዩ ስራዎች በመስራት እንታወቃለን። ከተማ አስተዳደሩ እና ሴቶች ወጣቶች እና ህፃናት የድጋፍ ደብዳቤ ሰጥተውን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን።
.............
እስከዛሬ እየሰራንበት የምንገኘው የተቸገሩ ሰዎችን ህፃናትን እና ቤተሰቦችን መደገፍ ነው። በቀጣይም ልንሰራው ያሰብነው ለ ኢድ ልብስ የሌላቸው እና ጎዳና የሚኖሩ የተቸገሩ ሰዎችን ማልበስ። በተጨማሪም የተቸገሩ እና የታመሙ ሰዎችን እየዞርን ዚያራ በማድረግ ያማረ እና ደስ የሚል ኢድ ለማሳለፍ አስበናል። ይህም የሚሆነው በናንተ ድጋፍ እና እገዛ ነው ። የገንዘብ እና የልብስ መሰባሰብ ስራወን የቻላችሁ እንድትቀላቀሉን እንጠይቃለን። ገንዘብ ያለው በገንዘቡ ካልሆነም እቤታችሁ የማይለበስ እና ዝም ብሎ የተቀመጠ ልብስ ካለ ያላችሁበት መጥተን እንቀበላለን። እናም በዱዓቹ አግዙን የተማሪዎች ስብስብ ስለሆነ ስንጠፋ ስለ ምትጠይቁን እንዲሁም ስለ ምታበረታቱን
እናመስግናችኋለን🙏🙏
" በመስጠት እና የተቸገሩን ሰዎች በመርዳት የሚገኘውን ደስታ እንድትካፈሉን እንጠይቃለን"
እኛን ማገዝ የምትፈልጉ ሰዎች አድሚኖችን መናገር ትችላላችሁ።
በስልክ ደውላቹ መጠየቅ ትችላላችሁ።
0939325168 siti
0941020251 eman
0976649353 hayat
ኑር አህለል ኸይር ጀመዓ ✍
t.me/nurahlelkeyrjemea