ተቸግሬ ባሳብ ተከፍቼ
ተጠምጄ ባሳብ ቀረሁ ተረስቼ
አስታማሚ አጥቼ
በቁሜ ስሰቃይ ያልጠየቀኝ
ስሞት ቢያለቅስልኝ
ካፈር አያድነኝ ዕንባው ስንቅ አይሆነኝ
አንጀቴን ዳብሶ ካላዳነ ይቅርብኝ ሰው ከጨከነ
የሰው ልጅ ለሰው ካላዘነ የሚያስብ ምን ፍጡር ሆነ
በቁሜ ያረዳኝ በህይወት ዘመኔ
ተካፋይ ያልሆነኝ ለጭንቅ ለሀዘኔ
ስሞት ቢያለቅስልኝ ምን ይጠቅማል ለኔ
መከራዬ በዝቶ ስታረዝ ስቸገር
መፈጠር ሲያስጠላኝ ጉልበቴ እየዛለ
ማልቀስና መርዳት ማዘን ያኔ ነበር
ጓደኛና ዘመድ ምነው አልጠየቀኝ
አካሌ ገርጥቶ ከስቼ እያየኝ
ምንድነው ዋይ ዋይታ ምንድነው እዬዬ
ከሞትኩኝ በኋላ ከዚች ዓለም
በራብና በጥም ነብሴ ስትቀጣ
አንገቴን ቀናርጎ ውሃ የሚያጠጣ
ከንፈርን የሚያርስ እንዴት ዘመድ ልጣ
በቁሜ እንደመትኩኝ እንደ ተቀበርኩኝ
የሰው ያለህ እያልኩ ደራሽ እንዳጣሁኝ
እስትንፋሴ ቆመች ወይ ዘመድ እንዳልኩኝ
የወንድሙን ሀዘን ያብሯደጉን እንባ
እንደጤዛ ረግጦ ሆዱን ሲያስከፋው
ወይ መወለድ ቋንቋው ሚስጥራዊው ትርጉም
ጭካኔም ወርሶታል በኗል እንደ ጉም
በኗል እንደ ጉም
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏
ተጠምጄ ባሳብ ቀረሁ ተረስቼ
አስታማሚ አጥቼ
በቁሜ ስሰቃይ ያልጠየቀኝ
ስሞት ቢያለቅስልኝ
ካፈር አያድነኝ ዕንባው ስንቅ አይሆነኝ
አንጀቴን ዳብሶ ካላዳነ ይቅርብኝ ሰው ከጨከነ
የሰው ልጅ ለሰው ካላዘነ የሚያስብ ምን ፍጡር ሆነ
በቁሜ ያረዳኝ በህይወት ዘመኔ
ተካፋይ ያልሆነኝ ለጭንቅ ለሀዘኔ
ስሞት ቢያለቅስልኝ ምን ይጠቅማል ለኔ
መከራዬ በዝቶ ስታረዝ ስቸገር
መፈጠር ሲያስጠላኝ ጉልበቴ እየዛለ
ማልቀስና መርዳት ማዘን ያኔ ነበር
ጓደኛና ዘመድ ምነው አልጠየቀኝ
አካሌ ገርጥቶ ከስቼ እያየኝ
ምንድነው ዋይ ዋይታ ምንድነው እዬዬ
ከሞትኩኝ በኋላ ከዚች ዓለም
በራብና በጥም ነብሴ ስትቀጣ
አንገቴን ቀናርጎ ውሃ የሚያጠጣ
ከንፈርን የሚያርስ እንዴት ዘመድ ልጣ
በቁሜ እንደመትኩኝ እንደ ተቀበርኩኝ
የሰው ያለህ እያልኩ ደራሽ እንዳጣሁኝ
እስትንፋሴ ቆመች ወይ ዘመድ እንዳልኩኝ
የወንድሙን ሀዘን ያብሯደጉን እንባ
እንደጤዛ ረግጦ ሆዱን ሲያስከፋው
ወይ መወለድ ቋንቋው ሚስጥራዊው ትርጉም
ጭካኔም ወርሶታል በኗል እንደ ጉም
በኗል እንደ ጉም
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏