#ለ_ፈ_ገ_ግ_ታ
ፈገግታ😊😊 ሱና ነው !
ስለሆነም እስኪ ለፈገግታ ይችን ፅሑፍ እንጋብዛችሁ ።
🌺🌺አስገራሚ ትህትና🌸🌸
በአንድ ወቅት አንድ ሰው ከአንድ ነጋዴ ጋር ይጓዛል። ይህ ሰው እስኪደክመው ድረስ በጉዞው ላይ የሚያስፈልጉ ስራዎችን በሙሉ ይከውናል።
ምግብ 🍳በማዘጋጀት የጉዞ ጓደኛውን ይመግባል። ከጉዞ እየተመለሱ እያለ ምግባቸውን ለማብሰል አንድ ቦታ ላይ አረፉ።
አንደኛው እግሩን ዘርግቶ ተኛ 😴። ሌላኛው ጭነቱን አወረደ ለጓደኛውም "እኔ ስጋ🍖🍗🍗🍗 እስክቆራርጥ ተነሳና እንጨት ሰብስብ" አለው "ወላሂ ረጅም መንገድ መጓዙ አድክሞኛል" በማለት መለሰለት። ራሱ እንጨት ሰበሰበና "እሺ እንጨት አቀጣጥል🔥🔥" አለው። "ወደ እሳት ስቀርብ ጪሱ ያፍነኛል" አለ።
ራሱ አቀጣጠለና "ስጋውን በመቁረጥ አግዘኝ" ሲል አዘዘው።" እጄን ቢላዋ 🍴ሊቆርጠኝ ስለሚችል ይቅርብኝ" በማለት መለሰለት። ሰውዬው ራሱ ቆራረጠና "እሺ ስጋውን መጥበሻው ላይ አድርገህ አብስል🥘 ?"
"ምግቡ እስኪበስል ድረስ ቁጭ ብሎ መጠበቅ እጅግ በጣም አድካሚ ነገር ነው ይለፈኝ" አለ ራሱ አበሰለና በጣም ደክሞት ስለነበር ጋደም አለና "ሡፍራውን አንጥፈህ ምግቡን በሳህን አድርገህ አቅርብ🍽" ሲል ጠየቀው
"እኔ በጣም ደክሞኛል አሁን ይህን የምሰራበት ምንም አቅም የለኝም " አለው።
ሠውዬው ተነሳና ምግቡን🍛 አቀረበ። "እሺ ተነስተህ መብላት ትችላለህ?"ብሎ ሲጠይቀው
ምን ቢል ጥሩ ነው ??
"ወላሂ ሁሉንም ነገር እንቢ ማለት በጣም አሳፈረኝ።" እስኪ አሁን እንኳን እሺ ልበልህ አለና ተነስቶ መብላት ጀመረ
منقول