✨የጌታ ልደት✨
🪔🪔🪔🪔
🗓የጌታ ልደት ክርስቲያናዊ ክብረ በዓል
🪔🪔🪔🪔
🗓የጌታ ልደት ክርስቲያናዊ ክብረ በዓል
ከጾም መጨረሻ በኋላ የሚመጣ መልካም ቃላትና በጎ ፈቃድን የምንለዋወጥበት ቀን ብቻ አይደለም፡፡ነገር ግን እውነተኛ በዓል ከደስታውና ከአከባበሩ ጋር በዓሉን ተከትሎ የሚመጣ መልካም ነገርና ጥበብን ሁሉ የምንማርበት ነው፡፡ለመሆኑ ከበዓላት የምንማረው በጎ ነገር ምንድን ነው? ፩.ትህትና✍️ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳካከ
ከገና በዓል የምንማረው ታላቅ ነገር ትህትና ነው፡፡ጌታችን በቤተልሔም ይሁዳ በከብቶች በረት በመወለዱ ምሳሌውን ትቶልናል፡፡ጌታችን ሲወለድ ብዙ አጀብና ክብር አልነበረም፡፡ወደ ዓለም ሲመጣ ለሁሉም እየታየ በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ላይ ተቀምጦ ለዓለሙ ሁሉ እያወጀ መሆን ይገባው ነበር፡፡ነገር ግን ለውጫዊ ዕይታ ትኩረት አልሰጠም፡፡በቀዝቃዛ ወራት በብርድ ቀን በሌሊት ማንም ትኩረት ሊሰጥ በማይችለው በከብቶች ግርግም ተወለደ፡፡የሚለብሰው በቂ ልብስ አልነበረውም፡፡ የጌታ በከብቶች በረት መወለድ ትህትናን የምንማርበት ትልቁ ትምህርት ቤት ነው፡፡ትሕትናው ባይኖር ኖሮ ይህ በዓል ሰማያዊ መንፈሳዊ የሆነ ምስጢሩ ባልተገለጠ ነበር፡፡የጌታን ትሕትና ገንዘብ ለማድረግ ሞክር፡፡ በሥጋዌው ራሱን ዝቅ አደረገ የባሪያ መልክ ይዞ በሰው አምሳል ተገለጸ፡፡/ፊል 2፡8/፡፡ትሕትናን ከጥልቁ እንፈልገው እንዴት እንደምንጠቀም እንወቅበት መድኃኒታችን በሥጋዌው ያደረገው ይኼንን ነው፡፡ ፪.የዋኅነት
ከልደት በዓል የምንመለከተው ጌታ ፈቃዱን የገለጸው ለተወሰኑ ወገኖች ነው፡፡ሌሎች ምንም እንኳን በሥልጣን ከፍ ከፍ ያሉ ቢሆኑም አልተመረጡም፡፡ለምሳሌ ጌታ ልደቱን የገለጸው ለእረኞች ነው፡፡ሌሎች ጸሐፍት፣ ፈሪሳውያን ካህናትና ሽማግሌዎች ይህንን መልካም ዜና አላዩም፡፡ምክንያቱም የእግዚአብሔር ምሥጢር የሚገለጸው ልበ ንጹሐን ለሆኑ ወገኖች ስለሆነ ነው፡፡ሰብዓ ሰገልና እረኞች የሰሙትን ነገር አመኑ፡፡የዋኻንም ነበሩ፡፡ ታላላቅ ሰዎች እንዲህ ያለ የተዘጋጀና የዋኅ የሆነ ልብ አልነበራቸውም፡፡ ሄሮድስ ይሄንን ሁኔታ በሰማ ጊዜ ውሸትንና ምክንያትን በመፈለግ ለሥልጣኔ ባላንጣ ነው ብሎ ስላሰበ የማሳደድ ዕቅድን አወጣ፡፡ታዲያ እኛ ከየትኛው ወገን ነን ክርስቶስን በየውኀት ከሚቀበሉት ወይስ ከሚያሳድዱት?
ቅድስት ድንግል ማርያም የዋኅ ልብ የነበራት ነበረች፡፡ስለ እርሷ ከጌታ የተነገረላትን አመነች፡፡ድንግል ሳለች ልጅ እንደምትወልድ አመነች፡፡ዮሴፍ በሕልም የጌታ መልአክ የነገረውን ነገር አመነ፡፡እራሳችንን እንዲህ ብለን እንጠይቅ ‹‹የምንመላለሰው በየዋኅ ልብ ነውን? ወይንስ የተወሳሰበና የሚጠራጠር ልብ ነው ያለን? መልሱን ለእናንተ ትተናል፡፡ እኛ ግን እንደ እርግብ የዋሓን ሁኑ የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እናስታውስዎት፡፡