ሥርዓተ ቅዳሴ
ቅዳሴ ማለት ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን አመሰገነ፣ ባረከ፣ አከበረ፣ ለየ፣ ለእግዚአብሔር መርጦ ሰጠ ማለት ነው። ሥርዓት ማለት ደግሞ ሠርዐ፡ ሠራ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው። ትርጉሙ ሕግ: ደንብ አሠራር ማለት ነው። በአንድ ላይ አድርገን ስናነበው የምሥጋና ሥርዓት ማለት ነው የሚመሰገነው ደግሞ እግዚአብሔር ነው።
ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡
ቅዳሴ፡-
• በሰማይ የሚገኘውን ሥርዓት በምድር መተግበር ነው።
• ቅዱስ ቁርባን የሚቀርብበት እግዚአብሔርን የምናመልክበት ሥርዓት ነው።
• በደስታ የምናከናውነው እግዚአብሔርን የምናመልክበት ጸሎት ነው።
• ቅዳሴ አባቶች ካህናት እና ምእመናን ያሳተፈ የምሥጋና ሥርዓት ነው። ስለዚህ ዘወትር ለቅዳሴና ለመንፈሳዊ ትምህርት ትኩረት ልትሰጡ ይገባል።
ጳጳሳት፣ ቀሳውስት፣ ዲቆናት በመቀደስ ምእመናን ደግሞ በማስቀደስ ይሳተፋሉ ከሁሉ በላይ አምላካችን የሚገኝበት እመቤታችን ቅድስት ማርያም የምትገኝበት መላእክት የሚገኙበት ሁሉም ቅዱሳን እንደተሰጣቸው ክብር የሚገኙበት ጸሎት ነው ስለዚህ ስናስቀድስ ብዙ በረከት እናገኝበታለን።
በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ መሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው?
አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ፤ በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ተሟልተው ይገኙበታል። እዚህንም 5ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡
1. የቁርባን መስዋዕት፡-
በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ጸሎት ነው። ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል።
2. የከንፈር መስዋዕት፡-
ካህኑ፣ ዲያቆኑና ሕዝቡ በመቀባበል በአንድነት ምስጋና ለፈጣሪያቸው የሚያቀርቡበት የከንፈራችን ፍሬ የሚሰዋበት የፀሎት ክፍል ፀሎተ ቅዳሴ ነው፡፡
3. የመብራት መስዋዕት፡-
በቅዳሴ ጊዜ የሚበራው ጧፍ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የሚሠጥ የመብራት መስዋዕት ነው፡፡ ምሳሌነቱም የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ይህውም ጌታችን ጨለማ ለሆነ ዓለም ብርሃን ሆኖ ብርሃንን ሊያበራ ወደ ዓለም መቷልና ነው፡፡
4. የዕጣን መስዋዕት፡-
የዕጣን ጸሎት ካህኑ ብቻ የሚያጥነው ሲሆን ይህውም በማዕጠንቱ አማካኝነት ቅዱሱን እጣን በመንበሩ፣ በቅዱሳን ስዕላቱ፣ በሕዝቡ መካከል ያጥናል። ይህውም የሕዝቡን ፀሎት ወደላይ ወደ ሥላሴ መንበር ይዞ ይወጣል።
በሰማይም ያሉ ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሥላሴን መንበር እንደሚያጥኑ ሁሉ በምድርም ያለው ካህን የሰማያዊው ምሳሌ ነውና በምድር ያለውን መንበር በማጠን ለእግዚአብሔር የዕጣን መስዋዕት ያቀርባል፡፡
5. የሰውነት መስዋዕትነት፡-
በቅዳሴ ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ሙሉውን ማለት ይቻላል በመቆም የሚፀለይ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በመሐል 2 ጊዜያት ብቻ የስገዱ ትዕዛዝ ሲተላለፍ ሕዝቡ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪው አዞሮ እራሱን አዋርዶ ይሰግዳል። በእግዚአብሔር ፊት መቆምም ሆነ መስገድ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ የሰውነት መሥዋዕት ነው፡፡
ይህ የጸሎት ክፍል (ቅዳሴ) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፦
1. የዝግጅት ክፍል
2. የንባብና የትምህርት ክፍል
3. ፍሬ ቅዳሴ፦ ፍሬ ቅዳሴያት እንደየበዓሉ ይለዋወጣተሉ ብዛታቸውም ፲፬ (14) ናቸው። እነዚህም፡-
3.1. ቅዳሴ ዘሐዋርያት
3.2. ቅዳሴ እግዚእ
3.3. ቅዳሴ ማርያም
3.4. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ
3.5. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
3.6. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
3.7. ቅዳሴ ባስልዮስ
3.8. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
3.9. ጎርጎርዮስ ካልእ
3.10. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
3.11. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
3.12. ቅዳሴ ዘቄርሎስ
3.13. ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ
3.14. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ
- የጌታችን በዓል ከሆነ (ቅዳሴ እግዚእ)
-የጌታችን ምጽአት፣ ጳጉሜ እሑድ ቀን ከዋለች ሰንበት (ቅዳሴ አትናቴዎስ)
-የእመቤታችን በዓል ከሆነ ቅዳሴ ማርያም (ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ)
-የመላእክትና የሐዋርያት በዓል ከሆነ (ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)
-ከዘመነ ልደት እስከ ዘመነ ግዝረት (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ካልዕ)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️