የለቅሶ ቤት ንፍሮ
ከቀብር መልስ እጅህን ታጥበህ ተስተናግደህ ታውቃለህ? ንፍሮስ ቀምሰህ ታውቃለህ? ንፍሮውን ስትበላ እኔ እንደማደርገው ሽንብራ ሽንብራውን ለቅመህ በልተህ ስንዴውን ለሌላ ሰው ትመርቃለህ ወይስ ሁለቱንም ትበላለህ? በሆድህ "ለምንድን ነው ግን ጨዉን የሚያሳንሱት" እያልክ ተመራምረህ ይሆን?
እኔ ደግሞ ዛሬ ከቀብር መልስ ካልጠፋ እህል ስንዴ ለምን እንደሚቀርብ ልነግርህ ነው። ነገሩ ባሕል ብቻ ሳይሆን ሃይማኖትም ነው። ቀብረን ከተመለስን በኁዋላ ስንዴ ስንበላ የንፍሮውን ጣዕም ማሰላሰል ትተን ይህንን የጌታችን ቃል እናስታውስ :-
''እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች" ዮሐ 12:24
ከቀብር መልስ በንፍሮ መልክ የምንበላው ስንዴ ኀዘንተኞችን የሚያጽናና ትልቅ መልእክት ይዟል። ክርስቶስ ስንዴ የሚያፈራው ሞቶ በምድር ሲቀበር ነው ብሎ ስንዴን ለእኛ ሞትና ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎታል። ቀብረህ ስትመለስ በእጅህ የዘገንከው ስንዴ ቀብረኸው የመጣኸው ወንድምህ ትንሣኤ እንዳለው እየነገረ ያጽናናሃል። በምድር የወደቀ ስንዴን ያልረሳ አምላክ የሞተውን አይረሳም።
ቀብረነው መጣን ብለህ አትዘን፤ ዘርተኸው እንደመጣህ አስብ፤ በመዋረድ ብትዘራውም በክብር ይነሣል፤ በድካም ብትዘራውም በኃይል ይነሣል፤ ለመበስበስ ብትዘራውም ባለመበስበስ ይነሣል ይልሃል ሐዋርያው (1ቆሮ 15:42-43)
ነፍሳችን ከሥጋችን በተለየች ጊዜ በምድር አስከሬናችን ይቀራል። አስከሬን (በግሪክ ስክሪኒዉም) ኮሮጆ መያዣ ማኅደር ማለት ነው። "ንዒ ማርያም ለእግዚአብሔር አስከሬኑ" "የእግዚአብሔር ማደሪያው ማርያም ሆይ ነይ" እንዲል። የነፍሳችን ማደሪያ የሆነው ሥጋ ከአዳሪዋ ነፍስ ሲለይ አስከሬን (ማደሪያ) የነፍስ ሳጥን የሚል ስም ይሠጠዋል። ሬሳ የሚለው ቃል የበሰበሰ ነገርን ያሳያል።
ምሥራቃውያኑ የቡድሃና ሂንዱ ተከታዮች ሥጋን የነፍስ እስር ቤት አድርገው ስለሚያምኑ ሥጋ ሲቃጠል ነፍስ ነፃ ይወጣል ብለው አስከሬን ያቃጥላሉ። በዳግም ሥጋዌ (reincarnation) የሚያምኑ በመሆናቸውም አንድ ሰው ድጋሚ ሲፈጠር የተሻለ አካል ይዞ እንዲወለድ አሮጌው ሥጋው መቃጠል አለበት ብለው ያስተምራሉ።
እኛ ግን እንቀብራለን እንጂ በፍጹም አስከሬን አናቃጥልም። የሚቀበር ነገር ዋጋ ያለውና በኁዋላ የሚፈለግ ነገር ነው። ገንዘብ የምትቀብረው ሌላ ጊዜ ልታወጣው ካሰብክ ነው። የምታቃጥለው ግን የማትፈልገውን ነው። የምንቀበረው እንደምንወጣ ስለምናምን ነው። የመለከት ድምፅ ሰምተን እንደምንነሣ ተስፋ ስላለን ምንም ብንሞትም በተስፋ እንቀበራለን። እንደምንበቅል ተስፋ አድርገን እንዘራለን። ሌላው ቢቀር በእሳት ተቃጥለን ብንሞት እንኳን አመዱን እና የከሰለውን አጥንትም ቢሆን በተስፋ እንቀብረዋለን።
''የሙታንን መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን!"
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ የግዮን ወንዝ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️