ሕዳር ፮ /6/
በዚችም ቀን የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ፊልክስ አረፈ።
የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ክርስቲያኖች ናቸው የቤተክርስቲያንንም ትምህርት አስተማሩት የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት አንስጣስ ዮስም ዲቁና ሾመው ደግሞ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ዮስጦስም ጠባዩን የጽድቁንና፤ የትሩፋቱን ደግነት አይቶ ቅስና ሾመው።
ትሩስ ቄሣርም ከሞተ በኋላ ቴዎድሮስ ቄሣር ነገሠ ። እርሱም በምእመናን ላይ ታላቅ መከራ አምጥቶ ጭንቅ ፣ በሆኑ ሥቃዮች አሠቃያቸው ። ብዙዎችም በእርሱ እጅ በሰማዕትነት ሞቱ። ይህም አባት ከዚህ ከሀዲ ታላቅ መከራና ኀዘን ደረሰበት። ወደ እግዚአብሔርም ልመናውን ተቀብሎ ከሀዲውን በሁለተኛ ዘመነ መንግሥቱ አጠፋው።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መፅጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️