ጥር ፲፪ /12/
በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችንና ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በሆነች በቃና በሠርግ ቤት የሠራው የተአምራቱ መታሰቢያ ይደረግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሠሩ።
ቅዱስ ወንጌል እንደ ተናገረ ይህች የተአምራቱ መጀመሪያ ናት ውኃውን ለውጦ መዓዛው የሚጥም ጣፋጭ ወይን አድርጎታልና።
በዚህም አሳዳሪው ምስክር ሆነ ሙሽራውን በጠራው ጊዜ ሰው ሁሉ መልካሙን ጠጅ አስቀድሞ ያጠጣል ከሰከሩም በኋላ ዝቅተኛውን ያጠጣል። አንተ ግን የተሻለውን ጠጅ ወደ ኋላ አቆይተህ አጠጣህ አለው ። ጌትነቱንም ገለጠ ደቀ መዛሙርቱም አመኑበት።
ለርሱም ከቸር አባቱ መሐሪና ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
አምላከ ቅዱሳን ወይነ ቃና ፍቅሩን ያሳድርብን። ከድንግል እናቱ ምልጃና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን። አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️