ዘግይተህ አይደለም
ዘግይተህ አይደለም እኔ ቸኩዬ ነው
በነጋ በጠባ ስምክን የማማርረው
የሚያስፈልገኝን አንተ ቀድመህ አውቀህ/2/
ሁሉንም በጊዜው ታደርግልኛለህ/2/
መዝጊያ ምታ ይከፈታል
ስትጠይቅ ሁሉ ይሆናል
ብለህ ያልከኝ አለኝ ኪዳን
የማይሻር በየዘመን
ፈቃድህ ይደረግ አምላኬ አንተ ያልከው
አላማህ በእኔ ላይ አምናለሁ ፍቅር ነው
ሰጥተኸኛል ድንቅ ውለታ
ልቤ ረስቶት ያን ስጦታ
ባህር ስትከፍል በአይኔ እያየሁ
እንዳላየ እሆናለሁ
ፈቃድህ ይደረግ አምላኬ አንተ ያልከው
አላማህ በእኔ ላይ አምናለሁ ፍቅር ነው
መመኪያ ነህ ከአባት በላይ
የማትከዳ የማትለይ
ዛሬ ባይሆን ልጠይቀው
ጌታዬ ሆይ ለጥቅሜ ነው
ፈቃድህ ይደረግ አምላኬ አንተ ያልከው
አላማህ በእኔ ላይ አምናለሁ ፍቅር ነው
ትሰማለህ ቸል ሳትል
ትሰጣለህ ሳትከለክል
የማትነፍገው ባለጸጋ
የገዛኸኝ በደም ዋጋ
ፈቃድህ ይደረግ አምላኬ አንተ ያልከው
አላማህ በእኔ ላይ አምናለሁ ፍቅር ነው
ሊቀ ዲያቆናት ነቢዩ ሳሙኤል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ዘግይተህ አይደለም እኔ ቸኩዬ ነው
በነጋ በጠባ ስምክን የማማርረው
የሚያስፈልገኝን አንተ ቀድመህ አውቀህ/2/
ሁሉንም በጊዜው ታደርግልኛለህ/2/
አዝ
መዝጊያ ምታ ይከፈታል
ስትጠይቅ ሁሉ ይሆናል
ብለህ ያልከኝ አለኝ ኪዳን
የማይሻር በየዘመን
ፈቃድህ ይደረግ አምላኬ አንተ ያልከው
አላማህ በእኔ ላይ አምናለሁ ፍቅር ነው
አዝ
ሰጥተኸኛል ድንቅ ውለታ
ልቤ ረስቶት ያን ስጦታ
ባህር ስትከፍል በአይኔ እያየሁ
እንዳላየ እሆናለሁ
ፈቃድህ ይደረግ አምላኬ አንተ ያልከው
አላማህ በእኔ ላይ አምናለሁ ፍቅር ነው
አዝ
መመኪያ ነህ ከአባት በላይ
የማትከዳ የማትለይ
ዛሬ ባይሆን ልጠይቀው
ጌታዬ ሆይ ለጥቅሜ ነው
ፈቃድህ ይደረግ አምላኬ አንተ ያልከው
አላማህ በእኔ ላይ አምናለሁ ፍቅር ነው
አዝ
ትሰማለህ ቸል ሳትል
ትሰጣለህ ሳትከለክል
የማትነፍገው ባለጸጋ
የገዛኸኝ በደም ዋጋ
ፈቃድህ ይደረግ አምላኬ አንተ ያልከው
አላማህ በእኔ ላይ አምናለሁ ፍቅር ነው
ሊቀ ዲያቆናት ነቢዩ ሳሙኤል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️