ጻድቅ መሆንን የሚሻ ቢኖር የሚወደውን ነገር ለእግዚአብሔር ብሎ ይተወው...
#በእግዚአብሔር የተመረጠ ለእስራኤል ለበጎ የነገሠ #ዳዊት በዕድሜው ፍጻሜ አካባቢ ዓዶላም በሚባል ዋሻ ውስጥ ተቀምጦ በነበረበት ጊዜ፤ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በእርሱ አቅራቢያ በቤተልሔም በሚገኝ ራፋይም በሚባል ሸለቆ ሰፍሮ ሳለ፤
#ዳዊት፦ "በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተልሔም ምንጭ ውኃ ማን ባጠጣኝ? ብሎ ተመኘ።" የዳዊት ሦስት ኃያላን የሚባሉ #አዲኖን፡ #ኢያቡስቴ እና #ኤልያናን የማን ጌታ በጥም ይሞታል ብለው የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ቀድደው አልፈው ሄዱ፥ በበሩም አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፥ ይዘውም ለዳዊት አመጡለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣ አልወደደም፥ ነገር ግን ለእግዚአብሔር አፍስሶ፦ "አቤቱ፥ ይህን አደርግ ዘንድ ከእኔ ይራቅ፤ በነፍሳቸው ደፍረው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን?" ብሎ ይጠጣ ዘንድ አልወደደም። ሦስቱ ኃያላን ያደረጉትም ይህ ነው። ( 2ኛ ሳሙኤል 23 )
አቤቱ ጸጋህ በዝቶብኛልና ያዝልኝ ብሎ እስከመጸለይ እስኪደርስ እግዚአብሔር ጸጋን ያበዛለት ቅዱስ ኤፍሬም በዕለተ ሐሙስ ውዳሴ ማርያም ላይ ይህን የቅዱስ ዳዊት ታሪክ ከሰማዕታት ሕይወት ጋር አያይዞ ይተረጉመዋል፤
"ጻድቅ ዳዊት ጨክነው ሰውነታቸውን ስለ እርሱ ለጦርነት ለሞት አሳልፈው እንደ ሰጡ ባየ ጊዜ ያን ውሃ አፈሰሰ ከእርሱም አልጠጣም። ከዚህ በኋላ ለዘለዓለም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ደማቸውንም ስለእግዚአብሔር አፈሰሱ ስለመንግስተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ እንደ ይቅርታህ ብዛት ይቅር በለን።"
አባቶቻችን በውዳሴ ማርያም ትርጓሜያቸው ደግሞ እንዲህ አድርገው እንደወርቅ አንከብለው እንደሸማ ጠቅልለው ይገልጹታል..
እስራኤል ማለት ሕዝበ #እግዚአብሔር ማለት ነው፤ "እስራኤል ብሂል ሕሊና ዘይሬእዮ #ለእግዚአብሔር ፣ ነጻሪ ከሃሊ ምስለ አምላኩ፤" እንዲል፤ እስራኤል ማለት #እግዚአብሔርን በሕሊናው የሚያይ የሚያስብ አስተዋይ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆነ ማለት ነው፤"
ዳዊት ለእስራኤል እንደነገሠ ሁሉ በፍጥረቱ ሁሉ የሰለጠነም #አዳም ፍትወታት ፣ እኩያት ፣ ኃጣውእ በጸላትነት በተነሱበት ጊዜ #ከእመቤታችን ከነሳው #ከክርስቶስ ስጋ የተገኘ ማየ ገቦን ይጠጣ ዘንድ ወደደ፤ የትሩፋት አበጋዞች የሚባሉት #ሃይማኖት ፣ #ትውክልት ፣ #ተፋቅሮ (እምነት ፣ ተስፋ ፣ ፍቅር) ፈጥነው ተነሱ፤ በአጋንንት ከተማ ተዋጉለት ይጠጣ ዘንድ የወደደውን ማየ ገቦ አመጡለት፤ አዳም አድነኝ መልሰኝ አለ እንጂ ሙትልኝ ተሰቀልልኝ አላለም ፤ ለአዳም ቤዛ ሊሆን #ሃይማኖት #ትውክልት #ተፋቅሮ ጌታን ለሞት አሳልፈው እንደሰጡት ባየ ጊዜ ክርስቲያን የሆነው አንዱም አንዱ በሰማዕትነት ደሙን ያፈሳል ሆነ ፤ በራሱ ደም የዳነ አይደለም፤ ከጽድቅ ገብቶ ተቆጠረለት እንጂ፤ "ዳዊትም ያን ውሃ አፈሰሰ ከእርሱም አልጠጣም። ከዚህ በኋላ ለዘለዓለም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።" እንደተባለ።
"ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ደማቸውንም #ስለእግዚአብሔር አፈሰሱ ስለመንግስተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ እንደ ይቅርታህ ብዛት ይቅር በለን።"
♦️በጥም ውስጥ የነበረ ዳዊት ጣዕመ ማይን እንደናቀ፤ ሦስቱ የዳዊት ኃያላን አዲኖን፡ ኢያቡስቴ እና ኤልያናን ነፍሳቸውን እስከ መስጠት ጣዕመ ዓለምን እንደናቁ #ሰማዕታትም እንደቸርነትህ ማረን እያሉ ጣዕመ ዓለምን ናቁ።
♦️ሦስቱ የዳዊት ኃያላን ለዳዊት ውኃን ለማምጣት ደማቸውን እንዳፈሰሱ #ሰማዕታትም ለእግዚአብሔር ሲሉ እንደቸርነትህ ማረን እያሉ ደማቸውን አፈሰሱ፤
♦️ሦስቱ የዳዊት ኃያላን ስለዳዊት ብለው መራራ ሞትን እንደታገሡ ፤ ዳዊት የዉሃ ጥምን እንደታገሠ ፤ #ሰማዕታትም እንደቸርነትህ ማረን እያሉ መራራ ሞትን ታገሡ፤
እኛስ እንደሰማዕታት ከዐላውያን ነገሥታት ፣ መኳንንት ገብተን መከራውን ታግሰን፤ መከራውን ተቀብለን መዳን አይቻለንምና
እኛስ እንደ ምዕመናን ከፍትወታት ከእኩያት ከኃጣውእ ጋር ተዋግተን ድል ነስተን መዳን አይቻለንምና #እግዚአብሔር ሆይ እንደቸርነትህ መጠን ማረን እንደ ቸርነትህ ብዛት ይቅር በለን፤
ዳዊት ጻድቅ መባሉ ፤ ሰማዕታት ጻድቃን መባላቸው የሚወዱትን ነገር ለእግዚአብሔር ብለው መተዋቸው ነው ፤ እኛም በሕይወታችን ውስጥ ያሉ #ለእግዚአብሔር ብለን ልንተዋቸው የሚገቡን ምን ያህል ነገሮች አሉን?
እናም ጻድቅ መሆንን የሚሻ ቢኖር የሚወደውን ነገር #ለእግዚአብሔር ብሎ ይተወው...
" ሰአሊ ለነ ቅድስት ፤ ቅድስት ሆይ ለምኝልን
#እመቤታችን #ቅዱስ_ኤፍሬምን አመስግነኝ ብትለው ወደሌላ ለምን ሄደ ቢሉ... ወደ ሌላ መሄዱም አይደለም፤ ዳዊት አባቷ ነውና፤ መንግስተ ሰማያትም ሆኖ የሚወረሰው #ጌታችን #ከእመቤታችን የነሳው ስጋ ከዳዊት የተገኘ ነውና፤
መንግስተ ሰማያት ከሚባል ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ስርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን።
ቀዳሚት ሰንበት
ታኅሳስ 5 2017
5 ኪሎ
አዲስ አበባ
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖