"በረት ኪሩቤል እንደሚሸከሙት ዙፋን ሆነ ፤ ስፍራውም እንደ ጽርሐ አርያም፤ ድንግል እንደ አብ ሆነች አንድ ልጅም በጎል ተጥሎ በጨርቅ ተጠቅሎ ተገኘ፡፡" አርጋኖን ዘሰኑይ
ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የጌታችንን መወለድ በመጽሐፈ አርጋኖን መጽሐፉ ላይ እንዲህ ሲል በማድነቅ ይናገራል...
"እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ምን ያህል ጸጋ ክብር ሰጠ፡፡ እግዚአብሔር ከሰው ልጅ ተወለደ፤ ከእርሱ ልደትም ጋር ከማይተባበሩ ሦስት ልደታት ልዩ የሆነ ልደትን ተወለደ፡፡ እኔም ዐውቄ አደነቅሁ፡፡ በእርሱ ልደት እንጂ በሦስቱ የበጎ ዕረፍት አላገኘሁም፡፡
አዳም ከሕቱም ምድር የተወለደ በተፈጥሮ ነው፡፡ እኔን ግን የጠቀመኝ የለም፡፡ ሔዋንም ከአዳም ግራ ጐን ተወለደች እርሷም በተፈጥሮ ነው፡፡ ለኔ ግን የጠቀመችኝ የለም፡፡ ቃየልም እንደ ሰው ሁሉ በዘር በሩካቤ ተወለደ የጠቀመኝ የረባኝ የለም፡፡ ስንኳን እኔን እራሱንም አልጠቀመም፡፡ እሊህ ሦስቱ ልደታትም ለማንም ለማን አይረቡም አይጠቅሙም፡፡
ክርስቶስ ግን ያለዘር ያለሩካቤ ከድንግል ተወለደ ለሁሉ የሚረባ የሚጠቅም ሆነ፡፡ ለዚህ ልደት መስገድ መገዛት ይገባል፡፡ ክብር ምስጋና ለዚህ ልደት ይገባል ጌትነትና ገናንነት ኀያልነት፣ አዚዝነት፣ እልልታ፣ ግርግታ ለዚህ ልደት ይገባል፡፡
የሔዋን ደኅንነቷ እመቤታችን ሆይ የድንግልናሽ ኃይል እጅግ የሚያስደንቅ ዕጹብ ነው፡፡ የአዳምን መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያጠፋሽለት እመቤታችን ሆይ የማይመረመር ረቂቅ ምሥጢር ባንቺ ተደረገ፡፡ እሳትና ውሀም ባንድነት ተስማምተው መኖራቸው እጅግ ድንቅ ነው የሚያስፈራውንም የአንበሳ ደቦል ፀዓዳ በግዕት በክንዷ መታቀፏ እጅግ ድንቅ ነው፡፡
ከድንግልም ብላቴና ጡቶች ወተት መፍሰስ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ በበረትም ለድኆች ልጅ የሰማይ ሠራዊት መስገድ እጅግ ድንቅ ነው፤ ዓለምን ሁሉ የመላ አምላክም ከበረት ተጥሎ በጨርቅ ተጠቅሎ መገኘቱ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ በረት ከጽርሐ አርያም ቁመት ረዘመ ከሰማይም ዳርቻ ሰፋ፡፡ ሕዝቅኤል ካየው ሠረገላ ዳንኤልም ካየው ኪሩባዊ ዙፋን በረት በለጠ፡፡ ይኽውም አደፍ ጉድፍ ሳይኖርበት ንጽሕት የወለደችው ንጹሕ በግ ነው፡፡ በረት ለንጹሑ መሥዋዕት ሽታ መሰብሰቢያ ሆነ፡፡
በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች እመቤታችን የተመረጠች ድንግል የሰማዩን ሠራዊት አሰገደቻቸው፡፡ የዓለም ጌጽ ሽልማት የሁሉ አባት የሚሆን መላእክትን የፈጠረ ጌታ ከርሷ ተወልዷልና፡፡ በረት ተመሰገነ ምድርን በውሃ ላይ ያጸናት እርሱ ስለተጠጋባት ድንግልም የመላእክትን አለቆች ገዛቻቸው በኪሩቤል ላይ የሚቀመጥ እሱ በማኅፀኗ ስላደረ፡፡ በረት ኪሩቤል እንደሚሸከሙት ዙፋን ሆነ ስፍራውም እንደ ጽርሐ አርያም፤ ድንግል እንደ አብ ሆነች አንድ ልጅም በጎል ተጥሎ በጨርቅ ተጠቅሎ ተገኘ፡፡ ዮሴፍና ሰሎሜ በወዲህና በወዲያ ላምና አህያም በወዲህና በወዲያ በበረቱ ጐንና ጐን በአራቱ ማዕዘን በዙፋኑ ቀኝና ግራ በጐንና በጐኑ አራቱ እንስሶች እንዳሉ፡፡ የሰማይ ሥርዓት በምድር ላይ ተሠራ፡፡ ቤተልሔም ሰማይን መሰለች ስለ ፀሐይም በቅዱሳን ላይ የሚያበራ ለዘወትርም ጨለማ የማይቃወመው ኅልፈት ጥፋትም የሌለበት ዕውነተኛ ፀሐይ በውስጧ ተገኘ፡፡ የብርሃኑም ክበብ መምላትና መጉደልን ስለሚያፈራርቅ በጨረቃ ፈንታ በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች የድንግልናዋም ምስጋና በሁሉ የመላ ነው፡፡ ለዘወትርም የማይጐድል እመቤታችን የተመረፀች ድንግል ማርያም ተገኘች ስለ ከዋክብትም መላእክተ ብርሃን ታዩ፡፡..."
ወደዚህ ማኀበር አንድነት እንኖር ዘንድ ማን በከፈለን ከመላእክት ጋር እንድናመሰግን ከአዋላጅቱም ጋር እንድናደንቅ ከእረኞችም ጋር እንድናገለግል፡፡ በረቱንም እጅ እንነሣ ዘንድ ማን በከፈለን የሙታን ሕይወት የኃጥአንም ንጸሕና የቅቡፃን ተስፋ የተጨነቁትንም የሚያድን ጌታ ወደተቀመጠበት፡፡ አሁንም ያን ጊዜ በዕብራይስጥ ማሪሃም ከተባለች ከተመረጠች ድንግል ማርያም ጋራ ያን ጊዜ ካሉት አናንስም ሀሳባችንንም ከዚያ እንዳለን አድርገናልና፡፡
በስጋ አልነበርንም በመንፈስ ግን አለን፡፡ ባነዋወር አልነበርንም በሃይማኖት ግን አለን በገጽ አልነበርንም በማመን ግን አለን፡፡
ሳንኖር እራሳችንን እንዳለን ያደረግን እኛ የተመሰገንን ነን ጌታችን በወንጌል እንደተናገረ እንዲህ ሲል ሳያዩኝ የሚያምኑብኝ ግን የተመሰገኑ ናቸው፡፡ እኛ ባሪያዎችህ ስለሃይማኖታችን የተመሰገንን ነን፡፡ ስለ ዕውነታችን አይደለም ስለ መረዳታችንም የተመሰገንን ነን፡፡ ስለ ንጽህናችንም አይደለም በእግዚአብሔር ስም ስለ አመንን የተመሰገንን ነን፡፡ በእናቱም ጸሎት ስለ አመንን ንዑድ ክቡር ነን፡፡
እንኳን ለዚህ ጥበብ ፍልስፍና : አንክሮ ለሚገባው : እጅግ ዕፁብ ድንቅ ለሆነ የአምላክ ሰው መሆን ሥጋን መልበስ ዕለት በሰላም አደረሳችሁ!!!
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo